2018-01-29 15:57:00

ር. ሊ. ጳ. ፍራንቸስኮ "ኢየሱስ በቃል እና በተግባር የተገለጠ ኃያል የሆነ ነቢይ new" ማለታቸው ተገልጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሮም ከተማ ውስጥ በሚገኘው ሳናታ ማሪያ ማጆሬ ባዚሊካ በመገኘት መስዋዕተ ቅዳሴን ካሳረጉ በኃላ ወደ ቫቲካን ተመልሰው ልማዳዊ በሆነ መልኩ እርሳቸው ዘወትር እሁድ እለት በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመስርተው አስተንትኖ እንደ ሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን የእዚህ መርሃ ግብር አንዱ አካል በሆነው በትላንትናው እለት ያደርጉት አስተንትኖ በላቲን ስርዓተ አምላኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት በእለቱ ከማርቆስ ወንጌል 1፡21-28 ተወስዶ በተነበበው እና ኢየሱስ ርኩስ መንፈስ ማስወጣቱን እና እንደ  ባሥልጣን ሕዝቡን ማስተማሩን በሚገጽ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተመስርተው ባደርጉት አስተንትኖ እንደ ገለጹት ኢየሱስ  ኃይሉን በቃላት እና በተግባር ገልጾ እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

የእዚን ዘገባ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡራን እና ክቡራት አድምጮቻችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በእለቱ ቅዱስ ወንጌላ ላይ ተመርኩዘው ያደርጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

ተወዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አረፈዳችሁ

የእዚህ እሑድ ቅዱስ ወንጌል (ማርቆስ 1: 21-28) "የቅፍርናሆም ቀን" ተብሎ ሚጠራው ሰፊው ትረካ አንድ ክፍል ነው። በእዚሁ በዛሬው የወንጌል ትረካ ውስጥ ማዕከላዊ የነበረው ክስተት ኢየሱስ በቃል እና በተግባር የተገለጠ ኃያል የሆነ ነቢይ እንደ ሆነ አድርጎ በመግልጽ ያቀርበዋል። ኢየሱስም ወዲያው በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገብቶ ማስተማር ጀመረ። እንደ ባለ ሥልጣን በማስተማሩ ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ፣ ምክንያቱም እነርሱ የለመዱት ዓይነት ቃላትን ተጠቅሞ ሳይሆን ለየት ባለ ሁኔታ በማስተማሩ ሕዝቡ ተገረመ። የሕግ ጸሐፍት ምንም እንኳን ሕዝቡን ያስተምሩ የነበረ ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን እንደ ኢየሱስ በታላቅ ስልጣን አላስተማሩዋቸውም ነበር። ነገር ግን ኢየሱስ ሕዝቡን እንደ ባልስልጣን ሆኖ በማስተማር፣ ከእዚህ ቀደም የራቸውን አስተምህሮ ብቻ ሲያደርጉ እንደ ነበረ ሰዎች ሳይሆን  ከእግዚኣብሔር የተላከ መሆኑን ለሕዝቡ ገለጸ።

ሕዝቡ በሙሉ በመገረም፣ይህ ነገር ምንድን ነው? ሥልጣን ያለው አዲስ ትምህርት መሆኑ ነው”  በማለት ስለእርሱ መሰከሩ። በተመሳሳይ መልኩም ኢየሱስ በተግባር ኃይሉን አሳይቱዋል። በእዚያን ጊዜ በምኵራባቸው ውስጥ የነበረ ርኩስ መንፈስ ያደረበት አንድ ሰው እንዲህ በማለት ጮኸ፤ “የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፤ ከኛ ምን ትሻለህ? ልታጠፋን መጣህን? እኔ ማን እንደሆንህ ዐውቃለሁ፤ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱስ ነህ!” አለው። ስይጣን ዛሬ እውነቱን ተናገረ። ኢየሱስ የመጣው ሰይጣንን ልያጠፋ የእርሱንም ምንግሥት ሊደምስስ፣ ሰይጣንን ልያሸንፍ ነው።

ይህ ርኩስ መንፈስ የኢየሱስን ኃይል እና ቅድስና ያውቅ ነበር። ኢየሱስም፣ “ጸጥ በል፤ ከእርሱም ውጣ!” ብሎ ገሠጸው። ርኩሱም መንፈስ ሰውየውን በኀይል ካንፈራገጠው በኋላ እየጮኸ ወጣ። ይለናል የዛሬው ወንጌል።

ይህ ሁኔታ ታዲያ በእዚያ የነበረ ሕዝብ እንዲገረም እና በፍርሃት ተውጦ  “ይህ ነገር ምንድን ነው? ሥልጣን ያለው አዲስ ትምህርት መሆኑ ነው! ርኩሳን መናፍስትን እንኳ ያዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታል!” እያሉ እርስ በርስ ተጠያየቁ። ኢየሱስ ያሳየው ታላቅ ኃይል የእርሱን ስልጣን በሚገባ አሳይቱዋል። እርሱ በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባርም አስይቱዋል። በዚህ መንገድ የእግዚአብሔርን እቅድ በቃላት እና በኃይል ገለጸ።

እንዲያውም በወንጌል ውስጥ ኢየሱስ በምድራዊ ተልእኮው፣ በመስበክም ሆነ፣ ቁጥር ስፍር የሌላቸውን ሰዎች በመፈወስ፣ ከችግራቸው እንዲላቀቁ በማድረግ፣ ለኃጢአተኞች ርኅራኄን በማሳየት እግዚኣብሔርን ገልጹዋል።

ኢየሱስ በንግግሩ እና በተግባሩ ኃይሉን አሳይቶናል። ኢየሱስ የእኛን መንገዶች የሚያበራ፣ ፈተናዎችን እና ችግሮቻችንን እንድንቋቋም ጥንካሬን የሚሰጠን ጌታ ነው። ይህን እጅግ በጣም ኃይለኛ እና በጣም ጥሩ የሆነ አምላክን በማግኘታችን እኛ ምን ያህል ታላቅ ጸጋ እንዳለን አስብ! በተለይም ችግር ሲያጋጥመን መንገዱን የሚያሳየን እና የሚንከባከበን በተለይም ደግሞ በችግር ውስጥ በምንገባበት ወቅት አስተማሪያችን እና ጉዳኛችንም ጭምር ነው።

ማዳመጥ እንችል ዘንድ የምታስተምረን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በአከባቢያችን እና በውስጣችን የሚነገሩ መልእክቶችን ማዳመጥ እንችል ዘንድ እንድትረዳን፣ በተለይም ደግሞ በጣም አስፈላጊ የሆነውን ለሕይወታችን ትርጉም የሚሰጠውን እና ከማንኛውም ባርነት ነጻ የሚያወጣንን የአዳኛችንን ድምጽ መሰማት እንችል ዘንድ ትርዳን።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ይህ ቀደም ሲል ያስነበብናችሁ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትንው እለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው ያደርጉትን አስተንትኖ ነበር። አብራችሁን በመሆን ሳላዳመጣችሁን ከልብ እናመሰግናለን።

ይህ በእንዲህ እንዳለ  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ አስተንትኖ ካደረጉ በኃላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ማኅፀን ሥጋ ለብሶ ሰው በሆነበት ወቅት የተከሰተውን ክንዋኔ የምያስታውሰውን፣ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከተለመዱ ጸሎቶች አንዱ እና ዋንኛው የሆነውን የብስራተ ግብሬል ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኃላ እንደ ተለመደው ለዓለማችን ሕዝቦች አጭር መልእክት አስተላለፈዋል። በትላንትናው እለት ባስተላለፉት መልእክት በቅርብ ጊዜ በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ በካቡል በአሸባሪዎች በተቃጣው ሁለት ጥቃት 103 ሰዎች ማለፋቸውን ጠቁመው ይህንን ኢሰባዊ የሆነ ተግባር በከፍተኛ ሁኔታ ከወገዙ በኃላ የሚመለከታቸው አካላት ይህ አሰቃቂ የአሸባሪዎች ጥቃት የብዙ ንጹሐን የሆኑ ሰዎችን ነብስ እየቀጠፈ በመሆኑ የተነሳ ማብቂያ ያገኝ ዘንድ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ ካደርጉ በኃላ ቡራኬን ከሰጡ በኃላ የኣለት ዝግጅት ተጠናቁዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.