Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ስብከቶች

ር. ሊ. ጳ. ፍራንቸስኮ "“በማሪያም ውስጥ መጠጊያ እናገኛለን፣ ጸሎታችንም በፍጹም በከንቱ አይቀርም" ማለታቸው ተገልጸ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ በስናታ ማሪያ ማጆረ መሳዋዕተ ቅዳኤን ባሳረጉበት ወቅት - ANSA

29/01/2018 16:15

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሮም ከተማ ውስጥ በሚገኘው እና እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ18ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ግንባታው እንደ ተጠናቀቀ በሚነገርለት፣ በውሮፓ ውስጥ ከሚገኙ በማሪያም ስም ከተሰየሙ የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያንት መካከል በትልቅነቱ በሚታወቀው ሳናታ ማሪያ ማጆሬ በሚባለው ባዚልካ  በትላንትናው እለት ማለትም በጥር 20/2010 ዓ.ም. ተገኘተው መስዋዕተ ቅዳሴን ማስረጋቸው ተገለጸ። ቅዱስነታቸው ለየት ባለ ሁኔታ በእዚሁ በሳናታ ማሪያ ማጆሬ ባዚሊካ በመገኘት መስዋዕተ ቅዳሴን ያሳረጉት ምክንያት ባላቲን ቋንቋ “Salus Populi Romani” በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም የሮም ከተማ ሕዝቦች አዳኝ ወይም ጠባቂ በመባል የምታወቀው እና በአብዛኞቹ  የሮም ከተማ ነዋሪዎች ከፍተኛ ክብር የሚሰጠው፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ሕጻኑን ኢየሱስን በእጆቹዋ ላይ አቅፋ መያዙዋን የሚያሳየው ምስል ከቆይታ የተነሳ በማርጀቱ፣ ይህ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ሕጻኑን ኢየሱስን አቅፋ መያዟን የሚያመላክተው ምስል እደሳት የሚያስፍልገው ስለነበረ፣ በቫቲካን ሙዝዬም አማካይነት ጥናትዊነቱን በጠበቀ መልኩ በባለሙያዎች እደሳታ ተደርጎለት ወደ ነበረበት ወደ ሳናታ ማሪያ ማጆሬ” በተመለሰበት ወቅት ለእዚህ ቅዱስ ለሆነ ምስል አክብሮት ለመስጠት፣ በተዘጋጀው የመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ላይ ለመሳተፍ ቅዱስነታቸው በእዚያው መገኘታቸው የታወቀ ሲሆን እርሳቸው ለእዚህ ቅዱስ ምስል ያላቸውን አክብሮት ለመግለጽ ከእዚህ ቀደም ለ59 ጊዜያት ያህል ወደ ሳንታ ማሪያ ማጆሬ” አቅንተው የነበረ ሲሆን በትላትናው እለት ደግሞ በእርሳቸው መሪነት ባሳረጉት መሳዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ተስፋችን ተመልሶ እንዲያለመልም የሚያደገው የምንጠቀምባቸው የቴክኖሎጂ ወጤቶች ወይም የምንወጥናቸው ስንጽሰ ሐሳቦች ሳይሆኑ፣ “በውዥንብር ጎርፍ ውስጥ በምንገባበት ወቅት ተስፋ የምትሆነን እመቤታችን ቅድስ ድንግል ማሪያም ናት” ማለታቸው ታውቁዋል።

የእዚህን ዘገባ ቡሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

“በማሪያም ውስጥ መጠጊያ እናገኛለን፣ ጸሎታችንም በፍጹም በከንቱ አይቀርም፣ አንድ ሕጻን ልጅ በእናቱ እቅፍ ውስጥ መግባት እንደ ሚፈልግ ሁሉ እኛም በእርሷ እቅፍ ውስጥ መኖራችን ደስታን ይሰጠናል” በማለት ጨምረው ተናግረዋል።

“ማሪያም ባለችበት ቦታ ሁሉ ፍርሃት በፍጹም ሊያሸንፈን አይችልም”፣ በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እናታችን የሆነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ከማንኛውም ክፉ ከሆኑ ነገሮች ትጠብቀናለች፣ ትከላከልናለች ብለዋል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ባልችበት ቤት ሁሉ ሰይጣን በፍጹም ወደ እዚያ ሊገባ አይችልም ያሉት ቅዱስነታቸው ማሪያም ባለችበት ቦታ ሁሉ የሚያስጨንቁን እና የሚያሸብሩን ነገሮች በፍጹም ሊኖሩ አይችሉም ፍርሃት እና ጭንቀት ሕይወታችንን ሊያሸንፉ በፍጹም አይችሉም ብለዋል።

በእዚህም መሰረት ተክኖሎጂ ወይም የራሳችን ጽንሰ ሐሳቦች የእኛን ተስፋ መልሰው እንዲያለመልም ማድረግ በፍጹም እንደ ማይችሉ የገለጹት ቅዱስነታቸው ነገር ግን ተስፋችን በድጋሜ እንዲለመልም ማድረግ የሚችለው የማሪያም የፊት ገጽታ ብቻ ነው፣ በጭንቀት ጎርፍ ውስጥ በምንገባበት ወቅት በእርግጠኛነት ልትረዳን የምትችለው እርሷ ብቻ እንደ ሆነች ከገለጹ በኃላ በእየለቱ ማሪያም በልባችን እና በሕይወታችንም ውስጥ ሳይቀር ትገባ ዘንድ ልንጋብዛት የገባል ብለዋል።

እናት በሌለችበት ቦታ ሁሉ እምነታችን አደጋ ላይ እንደ ሚወድቅ በመግለጽ ስበከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እናት አማራጭ ሳትሆን የግድ የምታስፈልግ ናት፣ እርሷን መውደድ ማለት መቀኘት ማለትም አይደለም፣ "እንዴት መኖር እንደሚገባን ማወቅ ማለት ነው" ምክንያቱም "ያለ እናት እኛን ልጆች መሆን በፍጹም አንችልም፣ ለእዚህም ነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በነበረበት ወቅት ለዩሐንስ “እቺውና እናትህ” ብሎ በአደራ የሰጠውም በእዚሁ ምክንያት ነው ብለዋል።

ይህንንም በተመለከተ የሚከተለውን ብለዋል በእናት ጉዳይ ላይ ገለልተኛ መሆን ወይም ደግሞ ከእናት መለየት በፍጹም አንችልም፣ ይህንን ብናደርግ ግን ልጆች የምሆን ሕልውናችንን እና ማንነታችንን እናጣለን፣ ሐሳባዊ በሆነ መልኩ፣ በተለያዩ ዝግጅቶች በተወጠረ መልኩ፣ ያለ ምንም እምነት፣ ያለ ርህራኄ እና የለ መልካም ልብ የምንኖር ክርስቲያኖች እንሆናለን። ነገር ግን ያለ ልብ በፍጹም ልናፈቅር አንችልም፣ እምነታችንም በአንድ ወቅት የተጻፈ ውብ የሆነ ታሪክ ሆኖ ብቻ ይቀጥላል” ማለታቸውም ታውቁዋል።

በማሪያም እቅፍ ውስጥ መሰብሰብ እንደ ሚያስፈልግ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የክርስትና እምነት ተከታይ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ከመጀመሪያው ጀምሮ ችግሮች ውስጥ በሚገቡባቸው ወቅቶች ሁሉ ወደ ማሪያም መሄድ እንደ ሚገባቸው ተረድተው የነበረ መሆኑን በመጥቀስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በችግር ውስጥ የሚገኙ ድኸ የሆኑ ሰዎች ችግራቸውን ለመቋቋም ያስችላቸው ዘንድ በአንድ ስፍራ እንደ ሚሰበሰቡ ሁሉ እኛም በችግራችን ወቅት በእናታችን ጉያ መሸሸግ ይኖርብናል ብለዋል።

በሕይወት ጉዞ ውስጥ ሕይወታችን መከራና ችግር ውስጥ በምትገባበት ወቅት ማሪያምን ብንማጸናት፣ ማሪያም በፍጥነት ታማልደናለች በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እርሷ ለጭቀቶቻችን ትኩረት ስለምትሰጥ፣ በሕይወታችንን ውስጥ ለሚገጥሙን ማንኛቸውም መገራገጮችን በትኩረት ስለምትመለከት በፍጹም አትዘገይም፣ በፍጹም አታሳፍረንም ካሉ በኃላ ይህንንም በይበልጥ ለማስረዳት በማሰብ “በሆስፒታል ውስጥ ሆኖ የሚሰቃየውን የልጅዋ ሥቃይ የምታይ አንድ እናት እንደ ማያስችላት እና እርሷም ከልጇ ጋር አብራ እንደ ምትሰቃይ ሁሉ እናታችን የሆነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያምም መከራና ችግሮች ውስጥ በምንገባባቸው ወቅቶች ሁሉ ከእኛ ጋር እንደ ምትሰቃይ በንጽጽር ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

“ሰለዚህም አሉ ቅዱስነታቸው” በስብከታቸው ማብቂያ ላይ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ሕጻኑን ኢየሱስን በእጆቹዋ ላይ አቅፋ መያዙዋን ወደ የሚያሳየው ምስል እጃቸው በመጠቆም  “ስለእዚህ ወደ እርሷ በጥልቀት እንመልከት፣ የጥንት የኤፌሶን ክርስቲያኖች ለማሪያም ሰላምታን እንዳቀረቡላት እኛም እመቤታችንን ሰላም እንበላት ካሉ በኃላ የእግዚኣብሔር እናት ሆይ ለምኝልን የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር ከደገሙ በኃላ ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

Noti 2

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሮም ከተማ ውስጥ በሚገኘው ሳናታ ማሪያ ማጆሬ ባዚሊካ በመገኘት መስዋዕተ ቅዳሴን ካሳረጉ በኃላ ወደ ቫቲካን ተመልሰው ልማዳዊ በሆነ መልኩ እርሳቸው ዘወትር ረቡዕ እና እሁድ እለት በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመስርተው አስተንትኖ አድርገው እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደሩት አስተንትኖ በእለቱ በላቲን ስርዓተ አምላኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት በእለቱ ከማርቆስ ወንጌል 1፡21-28 ተወስዶ በተነበበው እና ኢየሱስ ርኩስ መንፈስ ማስወጣቱን እና እንደ  ባሥልጣን ሕዝቡን ያስተምር እንደ ነበረ በሚገጽ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተመስርተው ባደርጉት አስተንትኖ እንደ ገለጹት ኢየሱስ  ኃይሉን በቃላት እና በተግባር ገልጾ እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል። ክቡራን እና ክቡራት አድምጮቻችን ርዕሰሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በእለቱ ቅዱስ ወንጌላ ላይ ተመስርተው ያደርጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉ ከወዲሁ እናግብዛለን።

የተወዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አረፈዳችሁ

የዚህ እሑድ ቅዱስ ወንጌል (ማርቆስ 1: 21-28) "የቅፍርናሆም ቀን" ተብሎ ሚጠራው ሰፊው ትረካ አንድ ክፍል ነው። በእዚሁ በዛሬው የወንጌል ትረካ ውስጥ ማእከላዊው ክስተት ኢየሱስ በቃል እና በተግባር የተገለጣ ኃያል የሆነ ነቢይ እንደ ሆነ አድርጎ በመግልጽ ያቀርበዋል። ኢየሱስም ወዲያው በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገብቶ ማስተማር ጀመረ። እንደ ባለ ሥልጣን በማስተማሩ ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ፣ ምክንያቱም እነርሱ የለመዱት ዓይነት ቅላትን ተጠቅሞ ሳይሆን ለያት ባለ ሁኔታ በማስተማሩ ሕዝቡ ተገረመ። የሕግ ጸሐፍት ምንም እንኳን ሕዝቡን ያስተምሩ የነበረ ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን እንደ ኢየሱስ በታላቅ ስልጣን አላስተማሩዋቸውም ነበር። ነገር ግን ኢየሱስ ሕዝቡን እንደ ባልስልጣን ሆኖ በማስተማር፣ ከእዚህ ቀደም የራቸውን አስተምህሮ ብቻ ሲያደርጉ እንደ ነበረ ሰዎች ሳይሆን  ከእግዛኢብሔር የተላከ መሆኑን ለሕዝቡ ገለጸ።

ሕዝቡ በሙሉ በመገረም፣ “ይህ ነገር ምንድን ነው? ሥልጣን ያለው አዲስ ትምህርት መሆኑ ነው  በማለት ስለእርሱ መሰከሩ።

በተመሳሳይ መልኩም ኢየሱ በተግባር ኃይሉን አሳይቱዋል። ዚያን ጊዜ በምኵራባቸው ውስጥ የነበረ ርኩስ መንፈስ ያደረበት አንድ ሰው እንዲህ በማለት ጮኸ፤ “የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፤ ከኛ ምን ትሻለህ? ልታጠፋን መጣህን? እኔ ማን እንደሆንህ ዐውቃለሁ፤ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱስ ነህ!” አለው። ስይጣን ዛሬ እውነቱን ተናገረ። ኢየሱስ የመጣው ሰይታንን ልያጠፋ ነው፣ የእርሱንም ምንግሥት ሊደምስስ ነው፣ ሰይጣንን ልያሸንፍ ነው።

ይህ ርኩስ መንፈስ የኢየሱስን ኃይል እና ቅድስና ይውቅ ነበር። ኢየሱስም፣ “ጸጥ በል፤ ከእርሱም ውጣ!” ብሎ ገሠጸው።ርኩሱም መንፈስ ሰውየውን በኀይል ካንፈራገጠው በኋላ እየጮኸ ወጣ። ይለናል የዛሬው ወንጌል።

ይህ ሁኔታ ታዲያ በእዚያ የነበረ ሕዝብ እንዲገረም እና በፍርሃት ተውጦ  “ይህ ነገር ምንድን ነው? ሥልጣን ያለው አዲስ ትምህርት መሆኑ ነው! ርኩሳን መናፍስትን እንኳ ያዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታል!” እያሉ እርስ በርስ ተጠያየቁ። ኢየሱስ ያሳየው ታላቅ ኃይል የእርሱን ስልጣን በሚገባ አሳይቱዋል። እርሱ በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባርም አስይቱዋል። በዚህ መንገድ የእግዚአብሔርን እቅድ በቃላት እና በኃይል ገለጸ።

እንዲያውም በወንጌል ውስጥ ኢየሱስ በምድራዊ ተልእኮው፣ በመስበክም ሆነ ቁጥር ስፍር የሌላቸውን ሰዎች በመፈወስ፣ ከችግራቸው እንዲላቀቁ በማድረግ፣ ለኃጢአተኞች ርኅራኄን በማሳየት የእግዛኢብሔርን ገልጹዋል።

ኢየሱስ በንግግሩ እና በተግባሩ ኃይሉን አሳይቶናል። ኢየሱስ የእኛን መንገዶቻችንን የሚያበራ፣ ፈተናዎችን እና ችግሮቻችንን እንድንቋቋም ጥንካሬን የሚሰጠን ጌታ ነው። ይህን እጅግ በጣም ኃይለኛ እና በጣም ጥሩ የሆነ አምላክን በማግኘታችን እኛ ምን ያህል ታላቅ ጸጋ እንዳለን አስብ! በተለይም ችግር ሲያጋጥመን መንገዱን የሚያሳየን እና የሚንከባከበን በተለይም ደግሞ በችግር ውስጥ በምንገባበት ወቅት አስተማሪያችን እና ጉዳኛችንም ጭምር ነው።

ማዳመጥ እንችል ዘንድ የምታስተምረን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በአከባቢያችን እና በውስጣችን የሚነገሩ መልእክቶችን ማዳመጥ እንችል ዘንድ እንድትረዳን፣ በተለይም ደግሞ በጣም አስፈላጊ የሆነውን ለሕይወታችን ትርጉም የሚሰጠውን እና ከማንኛውም ባርነት ነጻ የሚያወጣንን የአዳኛችንን ድምጽ መሰማት እንችል ዘንድ ትርዳን።

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ይህ ቀደም ሲል ያስደመጥናችሁ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትንው እለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እን ኣየሀገር ጎብኚዎች በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው ያደርጉትን አስተንትኖ ነበር። አብራችሁን በመሆን ሳላዳመጣችሁን ከልብ እናመሰግናለን።

ይህ በእንዲህ እናዳለ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ አስተንትኖ ካደረጉ በኃላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ማኅፀን ሥጋ ለብሶ ሰው በሆነበት ወቅት የተከሰተውን ክንዋኔ የምያስታውሰውን፣ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከተለመዱ ጸሎቶች አንዱ እና ዋንኛው የሆነውን የብስራተ ግብሬል ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኃላ እንደ ተለመደው ለዓለማችን ሕዝቦች አጭር መልእክት አስተላለፈዋል።

 

29/01/2018 16:15