Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ ምጣኔ ሃብትና ፖሎቲካ

የኤኮኖሚን አለመመጣን ማስወገድ የሚቻለው ፍትሃዊ የሆነ የሃብት ክፍፍል ሲኖር ነው ተባለ

የኤኮኖሚን አለመመጣን ማስወገድ የሚቻለው ፍትሃዊ የሆነ የሃብት ክፍፍል ሲኖር ነው ተባለ። - AFP

25/01/2018 16:36

የኤኮኖሚን አለመመጣን ማስወገድ የሚቻለው ፍትሃዊ የሆነ የሃብት ክፍፍል ሲኖር ነው ተባለ።

በዓለማችን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አለመመጣጠን በከፍተኛ ደረጃ ቀጥሏል ያሉት በኢጣሊያ የኦክስፋም ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑትን ሮበርቶ ባርቤሪ፣ በስዊዘርላንድ በመካሄድ ላይ ባለው ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ ፎረም ላይ ባቀረቡት ሪፖርታቸው ገልጸዋል።

 

በስዊዘርላንድ በመካሄድ ላይ ያለው የኦክስፋም ዓለም አቀፍ ጉባኤ በሪፖርቱ እንደገለጸው፣ ባለፈው የጎርጎሮሳዊያኑ ዓመት ከዓለም ከተሰበሰበው ሃብት መካከል ሰማንያ ሁለት ፔርሰንቱ ለአንድ በመቶ ለሚሆን ሕዝብ ብቻ እንዲከፋፈል ተደርጓል።     

በካፒታል ላይ ያለው ገቢ በጣም ከፍተኛ የሆነው ሥራ የሚከናወንበት፣ ይህም ደግሞ ለሃብት ዕድገት መንገድ ስለሚያመቻች፣ ተጠቃሚ የሚሆኑትም በኤኮኖሚው ገበያ ውስጥ መሳተፍ ወደሚችሉ እና በኤኮኖሚ የበለጸጉ አገሮች ዘንድ ነው ብለዋል። በዚህ ሁኔታ የሃብት ክፍፍሉ በሚታይበት ጊዜ ከዓለም ምርት ወይም ሃብት አንድ በመቶ ብቻ ለግማሽ የዓለም ድሃ ሕዝቦች ይህም ማለት ለሦስት ነጥብ ሰባት ሚሊያርድ ስዎች መካከል እንዲከፋፈል ተደርጓል።

በኢጣሊያ የኦክስፋም ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ሮበርቶ ባርቢየሪ በማብራሪያቸው እንደገለጹት በዓለማችን በቀን ከሁለት ዶላር ያነሰ ገቢ ያላቸው ሰዎች ቁጥር ጥቂት ስለሆነ ድህነት የቀነስ ቢመስልም በሌላ ወገን በቀን ከሁለት ዶላር እስከ አሥር ዶላር ገቢ ያላቸው ሰዎች ቁጥር ከዓለም ሕዝብ መካከል ሃምሳ ስድስት በመቶ በመሆኑ ይህ በግልጽ እንደሚያመለክተው የዓለም ሃብት ክፍፍል በሕዝቦች ዘንድ የተመጣጠነ ባለመሆኑ ችግሩን ማስወገዱ የማይቻል እየሆነ መጥቷል ብለዋል።

ሮበርቶ ባርቢየሪ አሁን ያለውን የሥራ ዕድልን ሁኔታ አስመልክተው ባሰሙት ንግግራቸው በዓለማችን በርካታ ሕዝብ አስቸጋሪና ከባድ እንዲሁም አደገኛ፣ ክፍያውም በጣም አነስተኛ በሆኑ የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ሲሆን በተለይ ሴቶች የሚሰማሩበት የሥራ ዘርፍ እጅግ አስቸጋኣሪና ከባድ ነው ብለዋል። ለእነዚህ ሠራተኞች ታዲያ በጣም አነስተኛ ደሞዝ በመክፈል ከፍተኛ ትርፍ የሚሰበስቡትና ሃብት የሚያካብቱት በቁጥር ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው ብለዋል። ሮበርቶ ባርቢየሪ ባማከልም ዓለም አቀፍ የንግድ ትስስርንም ያየን እንደሆነ ታላልቅ ኩባንያዎች ሠራተኞቻቸውን በመበዝበዝ የሚያገኙትን ትርፍ መልሰው ራሳቸውን ብቻ ለማሳደግ ይጥራሉ ብለዋል።

በእስያ አህጉር ጨርቃጨርቅ የሚያመርቱ አገሮችን ያየን እንደሆነ ቀጥረው ከሚያሠሯቸው ሰራተኞቻቸው ከግማሽ በላይ በጣም ዝቅተኛ ደሞዝ እንደሚከፈላቸው ታውቋል። ኦክስፋም ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ ሴቶች በጣም ዝቅተኛ ደሞዝ የሚከፈላቸው ሲሆን፣ አሰሪዎቹ  ይህንን ጥሩ አጋጣሚ ለመጠቀም ብለው በዓለም ሥራ ላይ ከተሰማሩት ዘጠኝ ሚሊያርድ ሰዎች መካከል አስር በመቶ ብቻ ወንዶች እንደሆኑ ታውቋል።

በኢጣሊያ የኦክስፋም ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑትን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ስለ ሰብዓዊ ክብር የተናገሩት በስዊዘርላንድ በመከናወን ላይ ባለው የኤኮኖሚ ፎረም ላይ በመጥቀስ፣ የዓለም መሪዎች፣ ትላልቅ ኩባንያዎች፣ መንግሥታት፣ የሲቪል ማህበራትና ሕዝባዊ ተቋማት በሙሉ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን መልዕክት ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት እንደሚያደርጉ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። ሮበርቶ ባርቢየሪ በማከልም የግል ጥቅምን ብቻ ማሳደድ፣ ሃብትን በጋራ ለመከፋፈል ጥረት ካልተደረገ በቀር በዓለማችን ፍትሃዊ የሆነ የኤኮኖሚ ክፍፍልና ሰብዓዊ መብትም ሊከበር አይችልም ብለዋል። የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስን መልዕክት የጠቀሱት ሮበርቶ ባርቢየሪ ሰው ሰራሽ አእምሮና የቴክኖሎጂ እድገቶች ለሰዎች አገልግሎት እና ለጋራ ጥቅም መዋል እንዳለባቸው አሳስበዋል። ቴክኖሎጂዎች የሰዎች የሥራ ዉጤቶች ሆነው ለሰዎች አገልግሎት ካልዋሉ ይህም ሰብዓዊ ክብርን ያላገናዘበ ካልሆነ፣ ሮበርቶ ባርቢየሪ እንደገለጹት ወደፊትም ቢሆን ለሰው ልጆች ክብር ቅድሚያ ካልተሰጠና ሰዎች በሥራ ለሚያፈሱት ጉልበት ተመጣጣኝ ደሞዝ ካልተከፈለ በቀር በዓለማችን ውስጥ ተመጣጣኝ የሆነ የሃብት ክፍፍል እና እኩልነት ሊመጣ አይችልም ብለዋል።

25/01/2018 16:36