Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስና የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ

ር. ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ያደርጉት ንግግር

ር. ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ጋር በተገናኙበት ወቅት - ANSA

24/01/2018 15:05

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ወይም ደግሞ አሁንም በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ (እንደ አየሩ ሁኔታ ማለት ነው) ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ምያደርጉ ይታወቃል። በእዚሁ መርሃ- ግብር መሰረት በዛሬው እለት በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ያደርጉት የጠቅላላ አስተምህሮ እንደ ተለመደው ከእዚህ በፊት በመስዋዕተ ቅዳሴ አምልኮ ዙሪያ በተከታታይ ያደርጉት በነበረው አስተምህሮ ፈንታ፣ ባለፈው ሳምንት ማለትም ከጥር 7-14/2018 ዓ.ም. በቅደም ተከተል በቺሊ እና በፔሩ አድርገውት የነበረውን 22ኛው ሐዋሪያዊ ጉብኝት አጠቃላይ ይዘት በመዳሰስ ያደርጉትን ንግግር ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተጉመነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን ።

የእዚህን ዝግጅት ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በቺሊ እና በፔሩ አድርጌው የነበረውን ሐዋሪያዊ ጉብኝቴን አጠናቅቄ ከሁለት ቀናት በፊት ወደ እዚህ ተመልሻለሁ። ሁሉም ነገር በመልካም ሁኔታ በመጠናቀቁ እግዚኣብሔርን ለማመስገን እወዳለሁ፣ በእዚያ ምድር የሚገኙ የእግዚኣብሔር ሕዝቦች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ አይቻለሁ፣ በእነዚያ ሀገራት እየመጣ ያለውን መኅበራዊ እድገት በእዚህ አጋጣሚ ለማበረታታት እወዳለሁ።  በእነዚያ ሀገራት ለሚገኙ የስቪክ ማለስልጣናት እና ለወንድሞቼ ብጹዕን ጳጳሳት የእነርሱም ተባባሪ የነበሩ ሰዎች ሁሉ በፍጥነት እና በፍቅር ስለደረጉኝ መልካም አቀባበል በድጋሚ ለማመስገን እወዳለሁ።

በቅድሚያ በቺሊ እንደ ደረስኩኝ በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ብዙ ተቃውሞ ተደርጎ ነበር። እናም ይህ ተቃውሞ ጉብኝቴ የበለጠ ጉልህ እና ሕያው እንዲሆን አድርጎታል፣ ለሁሉ ሰዎችሰላሜን እስጣችኃለሁየሚለውን የኢየሱስን ቃል በድጋሚ ለማስተጋባት እፈልጋለሁ። ይህሰላሜን እስጣችኃለሁየሚለው ቃል ኢየሱስ ለደቀ-መዛሙርቱ ያቀረበላቸው ሰላምታ ሲሆን እኛም በእየለቱ በምናደርገው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ የምንደግመው ቃል ነው። የኢየሱስን ሞትና ትንሳኤ ለሚያምኑ ሰዎች ብቻ ነው ይህ የሰላም ጸጋ የሚሰጠው።

በሀገሪቷ ከሚገኙ የፖሌቲካ ኃይሎች፣ ባለስልጣናት እና የስቪክ ማሕበረሰቦች ጋር በተገናኘውበት ወቅት በቺሊ እየታየ ያለው የዲሞክራሲ ስርዓት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላቸውን አስተዋጾ እዲያደርጉ አበረታትቻቸዋለሁ፣ በእዚህም የተጠናከረ እና ሁሉንም ያሳተፈ ስርዓት እንዲገነቡም መክሪያለሁ። በእዚህም አግባብ ይህንን አጠናክረው ይቀጥሉ ዘንድ የምያስችላቸውን የማዳመጥ ዘዴን እንዲከተሉ አመላክቻለሁ፣ በተለይም ደግሞ ድኽ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን፣ ወጣቶችንየእድሜ ባለጸጋ የሆኑ ሰዎችን፣ ስደተኞችን እንዲሁም መልካ ምድራቸውንም ሳይቀር እንዲያዳምጡ መክሬን አስተላልፍያለሁ።

በቺሊ ባሳረግኩት የመጀመሪያው መስዋዕተ ቅዳሴለሰላም እና ለፍትህ” በሚል የጸሎት ሐሳብ እንድይዝ በማድረግ ኢየሱስ በተራራ ላይ የሰበከውን ስብከት (ማቴ. 5) በመጠቀምሰላምን የሚያወርዱ ብፁዓን ናቸው፤የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉና” (ማቴ 59) የምለውን በተለየ ሁኔታ ለመግልጽ ሞክሬ ነበር።

ይህንን የተራራው ላይ ስብከት ሁላችንም የጠበቀ ቅርበትን በመፍጠር፣ ካለን በማጋራት፣ በክርስቶስ ምሕረት እና ጸጋ በመበረታታት በአብያተክርስቲያናት እና በህብረተሰቡ ውስጥ በጥልቀት እንዲሰርጽ መመስከር ይኖርብናል። 

ይህንንም የጠበቀ ቅርበት በቃላት ብቻ ሳይሆን በተግባር ለማሳየት በቺሊ ዋና ከተማ በሳንቲያጎ የሚገኘውን የሴቶች ማረምያ ቤት ጎብኝቼ ነበር። በእዚያ የነበሩ በርካታ ወጣት ሴቶች፣ እናቶች እንዳንዶቹም ልጆቻችውን በእጆቻቸው አቅፈው ይዘው ነበር። እነዚህ ሴቶች ምንም እንኳን በማረሚያ ቤት ውስጥ ያሉ ቢሆኑም በፊታቸው ገጽታ ላይ ከፍተኛ የተፋ ምልክት ይታይበት ነበር። ይህንን የእስር ጊዜያቸውን አጠናቀው ማኅበርሰቡን በሚቀላቀሉበት ወቅት ራሳቸውን ከማኅበረሰቡ ጋር በሚገባ ማዋሀድ እንደ ሚኖርባቸው መክሬን ለግሻለሁ።

በቺል ከሚኖሩ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት፣ ካህናት ገዳማዊያን/ገዳማዊያት ጋር ሁሌቴ ተገናኝቼ ነበር ሁለቱም ግንኙነቶች በጣም ኃይለኛ የነበሩ፣ በዛ ሀገር ውስጥ በቤተክርስቲያኗ ምክንያት የቆሰሉ አንድአንድ ሰዎች ሁኔታ በማንሳት ቤተክርስቲያኑዋን የበለጠ ፍሬያማ ለማድርግ በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ተወያይተናል። በእዚህም መሰረት በእዚያው የሚገኙ ወንድሞቼን፣ ማንኛውንም ዓይነት በሕጻንት ላይ የሚደርሰውን ወሲባዊ ጥቃት፣ በእግዚኣብሔር በመታመን ማስወገድ እንደ ሚገባ በጥብቅ አሳስቤ ነበር።

በቺሊ በሚገኙ የተለያዩ ግዛቶች ውስጥ ተገኝቼ (በደቡብ እና በሰሜን የቺሊ ግዛቶች ማለት ነው) ሁለት መስዋዕተ ቅዳሴን አሳርጌ ነበር። በቀዳሚነት አራዎቺያኒያ በሚባለው በደቡባዊ የቺሊ ግዛት ተገኚቼ ኢዶስ ማፑኬ የሚባሉ ሕዝቦች በሚኖሩበት ሥፍራ ያደርኩት መስዋዕተ ቅዳሴ ሲሆን በእዚያም በተገኘውበት ወቅት የሕዝቡን ደስታ እና እንዲሁም ሐዘናቸውን እና ስቃያቸውንም ሳይቀር ለመረዳት ችያለሁ። በእዚያ አከባቢ በተለያዩ ምክንያቶች የተነሰ የሚከሰቱ በርካታ ውጥረቶች እና ግጭቶች ተወግደው በምትኩ ሰላም እና አንድነት እንዲፈጠር መልእክቴን አስተላልፍያለሁ። በቀጣይነት በሴሜናዊው የቺል ግዛት ባሳረኩት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ኢኪኬ በሚባል አከባቢ በሚገኘው ባሕር እና በረሃማ ቦታን በምያዋስን ሥፍራ ላይ የነበረ ሲሆን በእዚያም በነበረኝ ቆይታ የሕዝቡን መነፈሳዊነት ለመረዳት ችያለሁ።

በመቀጠልም በቺሊ ዋና ከተማ በሳንቲያጎ በሚገኘው ጳጳሳዊ ዩንቬርሲቲ ውስጥ ከሚማሩ ወጣት ተማሪዎች ጋር ተገናኝቼ የነበረ ሲሆን አሁኑ ወቅት የሚታየውን በቀጣዩ ትውልድ ሕይወት ላይ የተደቀነውን ለሕይወት ትርጉም ያለመስጠት መንፈስ”  እንዲወገድ የበኩላቸውን አስተዋጾ ያደርጉ ዘንድ መክሪያለሁ። በወቅቱ ለእነዚህ ወጣት ተማሪዎች ክርስቶስ በእኔ ቦታ ቢሆን ምን ያደርግ ነበር?” የሚለውን የቅዱስ አልበርቶ ሁርታዶ ቃላትን ተጠቅሜ ጥያቄ አቅርቤላቸው ነበር። ይህ የካቶሊክ ዩንቬርስቲ ለወጣት ተማሪዎቹ የተቀናጀ ማኅበራዊ እድገት ልያስገኝ ወይም ልያመጣ የሚችል የሕነጻ ትምህርት ለተማሪዎች መስጠት እንዳለበት፣ በተለይም ደግም በማኅበረሰቡ ውስጥ በልዩነት ውስጥ ሕበረትን መፍጠር፣ ማንኛውም ዓይነት ግጭት በመሳሪያ ሳይሆን በውይይት መፈታት አለበት የሚለውን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አስተምህሮን ለተማሪዎች ማስተማር እና ወጣት ተማሪዎችም በእዚሁ አግባብ ታንጸው እንዲያድጉ ማድረግ እንደ ሚገባም ማሳሰቢያ ስጥቼ ነበር።

በቀጣይነት በፔሩ ያደርኩት ሐዋሪያዊ ጉብኝት ሕብረት እና ተስፋ የሚል መሪ ቃል ያነገበ ነበር። ሕበርት ማለት ሁሉንም ነገር ወጥ ማድርግ ማለት አይደለም፣ ነገር ግን ከታሪክ እና ከባሕሎቻችን የወረስናቸውን የተለያዩ መልካም የሆኑ እሴቶችን በማጣመር በልዩነት ውስጥ ሕበረት መፍጠር ማለት ነው። በፔሩ በኩል በሚገኘው የአማዞን ደን አከባቢ ከሚኖሩ ሰዎች ጋር በተገናኘውበት ወቅት ይህንን ሐሳብ በድጋሚ አስተጋብቻለሁ። በመቀጠልም በእዚያው አከባቢ የሚገኘውን ፑሄርቶ ማልዶናልዶ የተባለውን ስፍራ እና ትንሹ ልዑል በመባል የምታወቀውን የሕጻናት ማሳደጊያ ጣቢያ በጎበኘውበት ወቅት ሁላችንም በጋራ በአዲስ መልክ እየተንሰራፉ ለምገኙት ቅኝ ግዛት ሥር የሚከቱትን  “የኢኮኖሚ እና የርዮተ ዓለም ጽንሰ ሐሳቦችንሁላችንም በጋራ በመቃወም አንቀበልም ብለን ነበር።

በፔሩ ከነበሩ የፖሌቲካ ኃይሎች እና የመንግሥት ባለስልጣናት ጋር ቆይታ አድርጌ ነበር። በፔሩ የሚታየውን የሀገር ወዳድ ስሜት፣ የባሕል እና የእዚያን ሀገር ሕዝቦች መንፈሳዊነትን በማድነቅ ንግግር አድርጌ የነበረ ሲሆን ይህንን የሀገሪቷ ሁኔታ አደጋ ልይ የሚጥሉ  ሁለት እሳት የሆኑ እውነታን ያዘሉ ሐሳቦችን አንስቼ ነበር። እነዚህም በቅድሚያ ስነ-ምህዳራዊ እና ማህበራዊ ገጽታ ያላቸው ችግሮች ሲሆኑ በመቀጠል ደግሞ ሙስና ይገኝበታል። እነዚህ ሁለት አደገኛ የሆኑ ነገሮች ከሚያስከትሉት አደጋ ማንም ሰው ማምለጥ እንደ ማይችል ገልጬ የነበረ ሲሆን፣ እነዚህን አደገኛ የሆኑ ነገሮችን የመዋጋት ኃላፊነት የሁሉም ሊሆን እንደ ሚገባ ገልጫለው።

በመቀጠልም በፔሩ መስዋዕተ ቅዳሴን አድርጌ ነበር። በእዚያም ከበርካታ ምዕመናን ጋር ተገኛኝቼ ደስታቸውን ተካፍያለሁ። በእዚያ ከምገኙ ብጹዕን ጳጳሳት፣ ካህናት እና ገዳማዊያን/ገዳማዊያት ጋር ተግናኝቼ ተወያይቼ ነበር። በእዚያ የሚገኙ ብጹዕን ጳጳሳት በሀገሪቷ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ተንሰራፍቶ የሚገኘውን ሙስና ቤተክርስትያን በተቀናጀ መልኩ ከምዕመናን ጋር በመሆን መዋጋት እንደ ሚኖርባት፣ ሙስና ሊቀረፍ የሚችል ችግር በመሆኑ የተነሳ መዋጋት እንደ ሚገባ ገልጨላቸው ነበር።

በፔሩ ከምገኙ ወጣቶች ጋር በተገናኘውበት ወቅት የቅዱስሳንን ፈለገ መከተል እንደ ሚገባ፣ ራሳቸውን ከክርስቶስ ጋር ማቀራረብ እንደሚገባቸው ተናግሬ የነበረ ሲሆን፣ በተለይም ኢየሱስ ያሳየንን አብነት መከተል እንደ ሚገባ እና በተሰፋ መጓዝ እንደ ሚኖርባቸው ተናግሬ ነበር። በመጨረሻው ቀነ እለተ ሰንበት ላይ በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት የተነበበው ቅዱስ ወንጌል ““ጊዜው ደርሶአል፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለች፤ ንስሓ ግቡ፤ በወንጌልም እመኑ” ብሎ እንደ ሚያሳስበው የኢየሱስን ቃል በምልአት በመቀበል ደስተኛ ሕይወት መኖር እንደ ሚገባቸው ተናግሬ ነበር።

 

24/01/2018 15:05