2018-01-23 10:10:00

የርዕሰ ሊቃን ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የፔሩ አድርገውት የነበረው 22ኛው ሐዋሪያዊ ጠቅላላ ሁኔታ በአጭሩ


የርዕሰ ሊቃን ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የፔሩ አድርገውት የነበረው 22ኛው ሐዋሪያዊ ጠቅላላ ሁኔታ በአጭሩ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ  በፔሩ አድርገው የነበረው 22ኛው ሐዋሪያዊ ጉብኝት በፔሩ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የተደረገ ሦስተኛው ሐዋሪያዊ ጉብኝት ሲሆን ከእዚህ ቀደም 1985 እና 1988 በቅደም ተከተል በወቅቱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነበሩት በዩሐንስ ጳውሎስ 2ኛ ከተደረገው ሐዋሪያዊ ጉብኝት በመቀጠል ይህ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በፔሩ ያደረጉት ሐዋሪያዊ ጉብኝት በአንድ የካቶሊክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በፔሩ የተደረገ ሦስተኛው ሐዋሪያዊ ጉብኝት ነው።

ከጥር 10-13/2010 ዓ.ም. በፔሩ በነበራቸው ቆያት የተለያዩ ስፍራዎችን መጎብኘታቸው ይታወቃል። በእዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው በቅድሚያ በፔሩ የነበራቸውን ቆይታ የጀመሩት በፔሩ በሚገኘውና ስፋት ባለው በአማዞን ደን ውስጥ የሚገኘውን ሕዝብ ጎብኝተዋል። ወደ አካባቢው ሲሄዱ የመጀመሪያው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው ተብሏል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮ በተያዘላቸው ቀጠሮ መሠረት በሥፍራው በመገኘት ከአካባቢው ሕዝብና ተወካዮች ጋር በመገናኘት የሚከተለውን ንግግር አድርገው ነበር . . .

“የአማዞን መሬት ለያዘው ሰፊ የተፈጥሮ ሃብት እና ሕዝብ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። ከአመታት ወዲህ የአማዞን ሕዝብ ሸክም ከባድ እየሆነ መምጣቱ የሚታይ ነው። ወደዚህ ሥፍራ እንድመጣ ከገፋፉኝ ምክንያቶች አንዱም ይህ ስለሆነ ሸክማችሁን ለመጋራት፣ ችግራችሁን በማዳመጥ፣ በአካባቢያችሁ፣ በሕይወታችሁና በባሕላችሁ ላይ የሚመጣውን ጥቃት ከመላዋ ቤተክስቲያን ጋር ሆነን ለመመከት ያለኝን ልባዊ ፍላጎቴን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። በአማዞን ሕዝብ ታሪክ ውስጥ፣ ሕዝቡ የዛሬን ያህል የከፋ ጊዜ ገጥሞት አያውቅም። የአማዞን ግዛት በተለያዩ አቅጣጫዎች ጥቃት እየደረሰበት እንደሆነ ይስተዋላል።

የአማዞን መሬት የያዘውን በርካታ የተፈጥሮ ሃብት ነዳጅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ፣ ወርቅ እና ዛፎችም ላይ ብዙዎች እጃቸውን አስገብተዋል። የቦታውን ሕዝቦች ሕይወት ያላገናዘበ የመንግሥት የተፈጥሮ ጥበቃ ፖሊሲዎች በነዋሪው ላይ ችግር እያስከተለ ይገኛል” ማለታቸው ያታወሳል።

ቅዱስነታቸው በእዚያ አከባቢ ያደረጉት ሐዋሪያዊ ጉብኝት በእዚያ አካባቢ የሚኖሩ የአማዞን ሕዝቦች ለብዙ አመታት ያህል ተገለው የኖሩ፣ እንዲሁም በከፍተኛ የድኽነት አረንቋ ስር የሚገኙ፣ በአከባቢያቸው የሚገኘው እና ለብዙ ሺ አመታት ለእነዚህ ለአማዞን ሕዝቦች እና ለዘርማንዘራቸው በመጠለያነት፣ የምግብ ምንጭ በመሆን በአጠቃላይ የሕይወታቸው ሕልውና የሆነው የአማዞን ጥቅጥቅ ደን በሕገወጥ እና ሕጋዊ በሆነ መንገድ እየተጨፈጨፈ ለተወሰኑ ሰዎች ክፍተኛ የገንዝብ ማግኛ ምንጭ ቢሆንም እነዚህ የአማዞን ሕዝቦች ግን በከፍተኛ የድኽነት አርቋ ሥር ሰልሚገኙ፣ የመኖር ሕልዋናቸው አደጋ ላይ በመውደቁም ጭምር እና እንዲሁም የአማዞን ደን “የዓለማችን ሳንባ” በመባል የሚታወቅ በመሆኑ የእዚህ ደን አደጋ ላይ መውደቅ የአማዞን ሕዝቦች የመኖር ሕልውናቸውን አደጋ ላይ የሚጥል ነገር ብቻ ሳይሆን የዓለም ሕዝቦች ሁሉ የመኖር ያለመኖር ሕልዋናቸው እና ዋስትናቸው በመሆኑ ጭምር ቅዱስነታቸው በአከባቢው የሚያደርጉት ጉብኝት የእነዚህ ጭቁን ሕዝቦች ችግር ለዓለም ቅልጭ አድርገው በማሳየት እና በማጋለጥ “የጋራ መኖሪያ ቤታችንን እንከባከብ” በማለት መፍትሄ ያስገኛል የሚል እንድምታን በቅድሚያ ያዘለ ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በፔሩ የሚያደርጉትን 22ኛው ሐዋሪያዊ ጉብኝት በመቀጠል ከአማዞን ደን አከባቢ ከሚኖሩ ሕዝቦች ጋር ከነበራቸው ቆይታ በኃላ በፔሩ ቡሄርቶ ማልዶናልዶ በሚባል ሀገረ ስብከት ውስጥ የሚገኘውን እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር 1980 ዓ.ም. የተቁቋመውን እና በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሥር የሚተዳደረውን የተክኖሎጂ፣ የህክምና፣ የእርሻ እና የሀገር አስጎብኝ ተማሪዎች የሚሰለጥኑንበት ተቋም ውስጥ በትላንትናው እለት ተገኝተው ንግግር ማድረጋቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በፔሩ የሚያደርጉትን 22ኛው ሐዋሪያዊ ጉብኝት በመቀጠል በፔሩ ቡሄርቶ ማልዶናልዶ በሚባል ሀገረ ስብከት ውስጥ የሚገኘውን ሆጋር ወደ ሚባለው የወላጅ አልባ ሕጻናት ማሳደጊያ ጣቢያ አቅንተው ነበር።

ሆጋር የወላጅ አልባ ሕጻናት ማሳደጊያ ጣቢያ ትንሹ ልዑል” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን 40 የሚሆኑ ወላጅ አልባ ሕጻናት የሚኖሩበት ማዕከል ሲሆን እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1996 ዓ.ም. አባ ዛቬር አርበት በተባሉ አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካህን የተቋቋም የሕጻናት ማሳደጊያ መዕከል ነው።

ቅዱስነታቸው በእዚያ በተገኙበት ወቅት ለተደረገላቸው አቀባበል ከፍተኛ ምስጋና አቅርበው እንደ ነበረ መግለጻችን የሚታወቅ ሲሆም በተለይም ደግሞ በእዚያ የሚገኙ ታዳጊ ሕጻናት ላቀረቡላቸው ዝማሬ ከፍተኛ የሆነ አድናቆታቸውን ገልጸው እንደ ነበረ ይታወሳል። በወቅቱም ቅዱስነታቸው“እናንተ ሕጻናት የማሕበረሰቡ ክቡር የሆናችሁ ሐብት ናችሁ” ካሉ በኃላ ከእናንተ በእድሜ የሚብልጡ ጎልማሶች ለእናንተ እንክብካቤ ማድረግ ሲገባቸው ባለማድረጋቸው ይቅርታን እጠይቃችኃለሁ” ማለታቸውን መዘገባችን ያትወሳል።

ቅዱስነታቸው በመቀጠል በጥር 12/2010 ዓ.ም. በፔሩ የሰዓት አቆጣጠር 10፡45 ደቂቃል ላይ በሀገሪቷ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት በመገኘት የሀግሪቷ ርዕሰ ብሔር ፔድሮ ፓውሎ፣ የተለያዩ ባለስልጣናት እና የተለያዩ ሀገራት ተወካዮች በተገኙበት ንግግር ማድረጋቸው ይታወሳል።

ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደርጉትን ንግግር የጅመሩት “በእዚህ ታሪካዊ በሆነ ሕንጻ ውስጥ በመገኘቴ እና በፔሩ ምድር እንድገኝ እድል የሰጠኝን እግዚኣብሔርን በድጋሜ ማመስገን እወዳለሁ፣ ካሉ በኃላ “ይህንን 22ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝት በፔሩ እንዳደርግ የገበዙኝን እና በፔሩ ሕዝቦች ስም ሆነው እንኳን ደሕና መጣህ በማለት የተቀበሉኝን የሀገሪቷን ርዕሰ ብሔር ፐድሮ ፓውሎን ማመስገን እፈልጋልው ብለው ነበር።

ይህ አሁን በፔሩ እያደርኩት የምገኘው 22ኛው ሐዋሪያዊ ጉብኝት በቅድሚያ የጀመርኩ በአማዞን ደን አከባቢ የሚገኙትን ሕዝቦች በመጎብኝት እንደ ነበረ በማስታወስ ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም በዓለም ውስጥ ከሚገኙ ደኖች ሁሉ በስፋቱ በጣም ሰፊ የሆነ፣ የተለያዩ መዐድናትን እን የተፍጥሮ ሐብት የበለጸገ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ የተለያየ ዓይነት ስነ-ፍጥረታት የሚገኙበት፣ ጥብቅ የሆነ የተፍትሮ ስነ-ምዳር በሰፊው የሚታይበት በአጠቃላይ “የዓለማችን ሳንባ” መሆኑን በንግግራቸው ወቅት የገለጹት ቅዱስነታቸው ጥበቃ እና እንክብካቤ እንዲደረግለት የተማጽኖ ድምጻቸውን አስተግባተዋል።

በፔሩ የተለያዩ ዓይነት የማሕበረሰብ ክፍሎች እንደ ሚገኙ፣ የተለያዩ ዓይነት ቋንቋዎች እንደ ሚነገሩበት፣ የተለያዩ ዓይነት ባሕሎች በአንድ ላይ አጣምሮ የያዘ ሀገር መሆኑን ገልጸው ይህም ልዩነት ለሀገሪቷ ውበት እንደ ሆነም ቅዱስነታቸው በንግግራቸው ከገለጹ በኃላ መንግስት ይህ ውብ የሆነ ባሕል እና አንድነት ተጠብቆ እንዲሄድ፣ ፍትሃዊ የሐብት ክፍፍል በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል በኩልነት እንዲሰራጭ፣ የሕዝቡ አንድነት ተጠብቆ እንዲቀጥል የበኩሉን ክፍተኛ ድርሻ እንዲጫወቱ አደራ ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በወቅቱ በንግግራቸው በሀገሪቷ ስለሚገኙ ወጣቶች ማንሳታቸውም ተገልጹዋል። ወጣቶች የመኅበርሰቡ “ውድ እና ወሳኝ የሆኑ ስጦታዎች መሆናቸውን” በንግግራቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው ወጣቶች ሕልማቸውን እውን እንዲያደርጉ መሰረታዊ ነገሮች እንዲሟሉላቸው መንግሥት የበኩሉን ድርሻ መጫወት ይኖርበታል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በፔሩ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት የሀገሪቷ ርዕሰ ብሔር፣ የተለያዩ ባለስልጣናት እን የተለያዩ ሀገራት ተወካዮች በተገኙበት ባደርጉት ንግግር በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ላይ ስለተደቀነው የኒዩክለር ኃይል ስጋት በዓለማችን መደቀኑን ሳይጠቁሙ አላለፉም። ቅዱስነታቸው ይህንን አስመልክተው በወቅቱ እንደ ተናገሩት “የሰው ልጅ በራሱ ላይ ይህንን የመሰለ ኃይል ከቶ ያልነበረው ቢሆንም በተለይ ደግሞ አሁን ያለውን የኃይል አጠቃቀም ስናሰላስል የሰው ልጅ ይህንን በማስተዋል ስለ መጠቀሙ ማረጋገጫ ምስጠት ያስቸግራል” በማለት ላውዳቶ ሲ “ውዳሴ ለአንተ ይሁን” በሚል አርእስት ካሳተሙት ሐዋሪያው መልእክት በመጥቀስ መናገራቸው ተገልጹዋል።

ለአማዞን ሕዝቦች እንክብካቤ እንዲደረግ፣ የአማዞን ጥቅጥቅ ደን የዓለማችን ሳንባ በመሆኑ የተነሳ ከተደቀነበት ሰው ሰራሽ አደጋ መታደግ እንደ ሚገባ፣ የሕግ የበላይነት በሀገሪቷ እንዲሰፍን፣ ለሴቶች መብት መቆም እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው በንግግራቸው የጠቀሱ ሲሆን በተለይም ደግሞ ሀግሪቷን እንዲሁም በአጠቃላይ መላውን የላቲን አሜሪካ ሀገራት እድገት ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ድኽንት ማቅ ውስጥ እየዘፈቀ የሚገኘውን  ሙስና መወጋት እንደ ሚያስፈልግ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው ሙስና በተቀናጀ መልኩ ከተዋጋነው ሊሸንፍ የሚችል እና የሚቀረፍ ችግር መሆኑንም ጭምረው የገለጹት ቅዱስነታቸው በእዚህ ረገድ የመንግስት ባለስልጣናት እና የሐይማኖት ተቋማት ሳይቀር ተቀናጅተው መሥራት እንደ ሚገባቸው ቅዱስነታቸው አበክረው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በፔሩ አድርገው የነበረውን 22ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ቀጥለው ባልፈው ቅዳሜ እለት በፔሩ የሰዓት አቆጣጠር ረፋዱ ላይ ከቀኑ 4 አከባቢ ማለት ነው ሳንታ ማሪያ ደል ቼሎ በሚባል ሥፍራ ተገኝተው በፔሩ ያደርጉትን 22ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ማብቂያ በማስመልከት መስዋዕተ ቅዳሴን ማሳረጋቸው ለመረዳት ተችሉዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ በእርሳቸው መሪነት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ላይ የጠፋውን የወንድማማችነት መንፈስ መልሶ እንዲያንሰራራ የሚያደርገውን ተስፋችንን ለማለምለም፣ በዓለማችን ላይ የተደቀነውን የጦር መሳሪያ ለማጋበስ የሚደርገው እሽቅድድም በሰላማዊ መንገድ ይቀለበስ ዘንድ፣ ዓለማችን ስጋት ላይ የጣላትን የሸባሪዎች አደጋ በሰላማዊ መንገድ ለመለወጥ ይቻል ዘንድ ኢየሱስ አሁኑም በየከተሞቻችን ጎዳናዎች ላይ እየተዘዋወረ ሰላሙን እንድንጎናጸፍ ያደርገናል” ማለታቸው ታውቁዋል።

ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደርጉት ስብከት በእለቱ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የስርዐተ-አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት በእለቱ በቅዳሚነት በተነበበው እና ከትንቢተ ዩንስ ከምዕራፍ 3፡1-5 ላይ ተወስዶ በተነበበው የእግዚኣብሔር ቃል ላይ” የእግዚአብሔርም ቃል ለሁለተኛ ጊዜ እንዲህ ሲል ወደ ዮናስ መጣ፤“ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሄደህ የምነግርህን መልእክት ስበክላት።”ዮናስም የእግዚአብሔርን ቃል ታዘዘ፤ ወደ ነነዌም ሄደ” በሚለው የእግዚኣቤሔር ቃል ላይ ተመርኩዘወ ባደርጉት ስብከት እንደ ገለጹት “ይህንንም መንገድ በመከተል ኢየሱስ ወደ ገሊላ ክፍል ሀገር ሂዶ በእዚያው መልካሙን ዜና እንደ ሰበከ” ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

አሁንም ቢሆን እኛ በምንኖርባቸው ከተሞች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች “በኢፍታዊ ተግባራት የተነሳ በክፍተኛ ሁኔታ የሚሰቃዩ እና ለመደበቅ እና ለመጥፋት የሚዳዳቸው ብዙ ሰዎች እንዳሉ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው አሁንም ቢሆን በተመሳሳይ መልኩ እኛ በምንኖርባቸው አከባቢዎች በየመንገዱ ጠርዞች ላይ የሚኖሩ፣ በየከተሞቻችን ጥጋጥጎች ላይ በብርድ እና በውርጭ እየተሰቃዩ የሚኖሩ በአጠቃላይ አንድ የሰው ልጅ ሊኖረው ከሚያስፈልገው ደረጃ በጣም ዝቅ ባለ ሁኔታ የሚኖሩ በእዚህም ምክንያት የሚሰቃዩ በርካታ የሆኑ ሰዎች እንደ ሚገኙ ቅዱስነታቸው ገለጸው በተለይም ደግም በእዚህ ዓይነቱ ሁኔታ የሚሰቃዩ ሕጻናትን እና ወጣቶችን ማየት በጣም የሚያሳዝን እንደ ሆነ ገልጸዋል።

በእለቱ ከማርቆስ ወንጌል 1፡14-20 ተወስዶ በተነበበው ምንባብ ላይ ተመስርተው ኢየሱስ ቅዱስ ወንጌልን ለመስበክ ወደ ገሊላ መሄዱን በማስታወስ ስበከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ የመጥመቁ ዩሐንስን መታሰር በሰማበት ወቅት በእርሱ ላይ የተፈጸመውን ኢፍታዊ ተግባር ለመቃወም ወደ ገሊላ በመሄድ በገሊላ መንገዶች ላይ እይተዘዋወረ የተስፋ ዘር ይዘራ እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

ኢየሱስ  ደቀ-መዛሙርቱን በመያዝ በየከተሞቹ ውስጥ የሚፈጸመውን ግፍ እና በደል እንዲረዱት በማድረግ እግዚኣብሔርን እና ባልንጀራን መወደድ አስፈላጊ መሆኑን በሚገባ ይረዱት ዘንድ ከእርሱ ጋር አብረውት እንዲጓዙ ይዞዋቸው ወደ ገሊላ እንደ ሄደ ገልጸው በእዚህም መሰረት ኢየሱስ ከደቀ-መዛሙርቱ ጋር በየከተማው እየተዘዋወረ የሕዝቡን የኑሮ ሁኔታ በማየት እና በመስማት፣ ችላ ተብለው በየመንገዱ ያሉትን ሰዎች፣ የከፍተኛ ኃጢኣት ውጤት የሆነው የሙስና ተግባር ምክንያት ለእንግልት የተዳረጉ ሰዎች፣ ሞቶ የነበረውን ተስፋቸውን መልሶ እንዲያንስራራ ለማድረግ ኢየሱስ በየከተማው መንገድ ላይ መመላለሱን ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ኢየሱስ በገሊላ ከተማ ጎዳናዎች ላይ በሚመላለስበት ወቅት የእግዚኣሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናት በማለት ኢየሱስ ስብከቱን ቀጥሎ እንደ ነበረ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ ርኅራኄን ለወንድሞቻችን በምናሳይበት ወቅት እግዚኣብሔር ቅርባችን እንደ ሚሆን ገልጸው መቼም ቢሆን አሉ ቅዱስነታቸው “መቼም ቢሆን እግዚኣብሔር በእየመንገዶች ላይ እየተረማመደ  ልጆቹን ከመፈልግ አያትክትም” ካሉ በኃላ ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

ቅዱስነታቸው አሁንም በፔሩ የሚያደርጉትን ጉብኝት በመቀጠል ባለፈው እሁድ ማለትም ጥር 13/2010 ዓ.ም. በሀገሪቷ ከሚገኙ ብጹዕን ጳጳሳት ጋር ተገናኝተው በተለያዩ ነባሪ ሁኔታዎችን በማንሳት መወያየታቸው ተገልጹዋል። በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባደርጉትን ንግግር ብጹዕን ጳጳሳት ሕዝቡ በሚረዳው ቋንቋን ተጠቅመው ቅዱስ ወንጌልን መስበክ እንደ ሚገባቸው ገልጸው በሀገሪቷ ሕብረት እና አንድነት ይፈጠር ዘንድ የበኩላቸውን አዎንታዊ አስተዋጾ ማድረግ እንደ ሚገባቸውም ቅዱስነታቸው አሳስበዋል።

ቅዱስነታቸው በእዚሁ በፔሩ የሚያደርጉት 22ኛው ሐዋሪያው ጉብኝት ማብቂያ ላይ ለብጹዕን ጳጳሳቱ ባደርጉት ንግግር ይህ 22ኛው ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸው በተለያዩ ዝግጅቶች የተጣበበ እንደ ነበረ ከገለጹ በኃላ ነገር ግን በፔሩ የነበራቸው ቆያታ አርኪ እንደ ነበረም ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

በፔሩ ያደርጉት 22ኛው ሐዋሪያዊ ጉብኝት “ሕብረት እና ተስፋ” የሚል መሪ ቃል ያነገበ እንደ ነበረ በማስታወስ ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በቤተ ክርስትያኒቷ ውስጥ ሕብረት እና አንድነት ይፈጠር ዘንድ ብጹዕን ጳጳሳቱ ጠንክረው መስራት እንደ ሚጥበቅባቸው ቅዱስነታቸው ገለጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የላቲን አሜርካ ሀገራት ወደ ሆኑት ቺሊ እና ፔሩ ከጥር 7-14/2010 ዓ.ም. በቅደም ተከተል ያደርጉትን 22ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን በተሳካ መልኩ ካጠናቀቁ በኃላ በትላንትናው ምሽት በፔሩ ዋና ከተማ ሊማ ከሚገኘው ዓለማቅፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ደማቅ አሸኛኘት ተደርጎላቸው የነበረ ሲሆን ቅዱስነታቸውም በፔሩ ለተደረገላቸው ከፍተኛ መስተንግዶ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅረበው እና ቡራኬያቸውን ከሰጡ በኃላ 11,223 ኪሎ ሜትሮችን በአየር ላይ አቆራርጠው በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 1፡15 ደቂቃ ላይ  ሮም ከተማ በሚገኘው ሊዮናርዶ ዳቪንቺ ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ከደረሱ በኃላ ወደ ቫቲካን ማቅናታቸው ታውቁዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.