2018-01-18 16:28:00

ቅዱስነታቸው በቺል ለሚገኙ ብጹዕን ጳጳሳት "“እናንተ የተመረጥችሁት ለሕዝቡ መሆኑን ማስታወስ ይኖርባችኃል” ማለታቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቺል ከሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካህናት፣ ገድማዊያን/ገድማዊያት ጋር ከነበራቸው ቆይታ በመቀጠል በእዚያው በቺሊ ከሚገኙ 50 ከሚሆኑ ብጽዕን ጳጳሳት ጋር በሳንቲያጎ በሚገኘው ካቴድራል መገናኘታቸው እና በተለያዩ የቤተክርስቲያኒቷ ወቅታዊ እና ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ ምይይት ማድረጋቸው ተገልጹዋል። 

ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደርጉትን ንግግር የጀመሩት ከእዚህ ቀደም በሮም ተካሄዶ በነበረው የብጹዕን ጳጳሳት ጉቡሄ ላይ እርሳቸው በተደጋጋሚ የጠቀሱትን “እናንተ የተመረጥችሁት ለሕዝቡ መሆኑን ማስታወስ ይኖርባችኃል” በሚል ሀረግ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን “በአሁኑ ወቅት ያለውን የማኅበረሰብ ክፍል እያጠቃ የሚገኘው ትልቁ ችግር የወላጅ አልባነ እና የብቸኝነት ስሜት እንደ ሆነ” ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

አሁን ባለው ዘመናዊ ዓለማችን እኛም ብጹዕን ጳጳሳት እና እንዲሁም ካህናት በእዚህ በዘመናችን በሚታየው የማንም እንዳልሆንን እንዲሰማን የሚያደርገው ስሜት እኛንም ቢሆን ሊያጠቃ የሚችል ስሜት እንደ ሆነ በማስታወስ ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የእግዚኣብሔር ቅዱስ ሕዝብ አንዱ አካል መሆናችንን አንድ አንዴ እንዘነጋለን ካሉ በኃላ ቤተክርስቲያን አሁንም ወደ ፊትም  የተመረጡ የጥቂቶች የካህናት፣ የገዳማዊያን/የገዳማዊያት እንዲሁም የጳጳሳት ብቻ በፍጹም ልትሆን አትችልም በማለት አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል።

“እኛ የእግዚኣብሔር ሕዝብ አንዱ አካል መሆናችንን የማናስታውስ ከሆነ እና ራሳችንን እንደ አለቆች አድርገን ብቻ የምንቆጥር ከሆንን” አሉ ቅዱስነታቸው “ከእዚህ ቀደም የነበሩ ወንጌልን ለማሰራጨት የተጠሩ ሚሲዮናዊያን አድረጕውት እንደ ነበረው፣ የተሰጠንን መንፈሳዊ ጥሪ ዘንግተን እንደ ፈሪሳዊያን እንዳንሆን መጠንቀቅ ይገባናል” ብለዋል።

“የቤተክርስቲያን ተልዕኮ ለሁሉም የእግዚኣብሔር ሕዝቦች የተሰጠ ተልዕኮ ነው እንጂ፣ ለካህናት ወይም ለጳጳት ብቻ የተተወ ተልዕኮ አለመሆኑ በጥልቀት መረዳት እንደ ሚያስፈልግ” የገለጹት ቅዱስነታቸው “የቤተክርስቲያን ተልዕኮ የሁሉም የእግዚኣቤሔር ልጆች ተልዕኮ መሆኑን የማንገነዘብ ከሆንን ግን የቤተክርስቲያንን አድማስ እንገድባለን፣ ከእዚህም ባስ ሲል ደግሞ በመካከላችን በመገኘት የሚያነሳሳንን እና የሚያነቃቃንን የመንፈስ ቅዱስ ተግባርም መገደብ እንገድባለን” ማለታቸው ተገልጹዋል።

“ምዕመናን የእኛ ገበሬዎች ወይም ቅጥረኛ ሠራተኞቻችን አለመሆናቸውን በጥብቅ መገንዘብ” እንደ ሚገባቸው ለጳጳሳቱ የገለጹት ቅዱስነታቸው “ወግ አጥባቂ ካህናት በምንሆንበት ወቅት ለማኅበረሰቡ መልካም የሆነ አስተዋጾ ከማድረግ ይልቅ መላዋ ቤተክርስቲያን እንድትመሰክር የተጠራችሁን የነቢይነት ተሎዕኮ ቀስ በቀስ እንዲደመዝዝ እንደ ሚያደርግ ከገለጹ በኃላ የዘረዐ ክህነት ተማሪዎች ከእዚህ ዓይነቱ ፈተና ተጠብቀው ትክክለኛውን መንገድ የተከተል የሕነጻ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያድጉ ዘንድ ጳጳሳት ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርጉ ቅዱስነታቸው ካሳሰቡ በኃላ መንፈሳዊ ተልዕኮዋችውን የምያሰናክሉን ነገሮችን በድፍረት መጋፈጥ እንደ ሚገባቸው ለብጹዕን ጳጳሳቱ ማሳሰባቸውምን ለመረዳት ተችሉዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.