2018-01-16 15:53:00

ር. ሊ. ጳ. ፍራንቸስኮ በጥር 08/2010 ዓ.ም. በቺሊ ዋና ከተማ በሳንቲያጎ ባሳረጉት መስዋዕተ ቃዳሴ ላይ ያሰሙ ስብከት


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ 22ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን ለማድረግ የላቲን አሜሪካ ሀገራት ወደ ሆኑት ወደ ቺሊ እና ፔሩ የሚያደርጉትን ጉብኝት በትላንትናው እለት መጀመራቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ለቅዱስነታቸው ከወጣው የጉዞ መርሃ ግብር ለመረዳት እንደ ተቻለው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት የቺሊ ዋና ከተማ ወደ ሆነችው ስንቲያጎ (በማሪኛው ቅዱስ ያዕቆብ ማለት ነው) በሰላም ደርሰዋል።

የእዚህን ስብከት ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በጥር 8/2010 ዓ.ም ማለት ነው በቺሊ ብሔራዊ ቤተመግሥት በመገኘት የሀገሪቷ ፕሬዚዳንት እና የተለያዩ ባለስላጣንት በተገኙበት በቺሊ የመጀመሪያ ኦፊሴላዊ ንግግራቸውን አድርገዋል። ቅዱስነታቸው በቺሊ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ተገኝተው የሀገሪቷ ርዕሰ ብሔር እና የሀገሪቷ ባለስልጣናት በተገኙበት ካደርጉት ንግግር በመቀጠል በስንቲያጎ በሚገኘው ሆሂግንስ ፓርክ በጊዜያዊነት በተሠራው ስፍራ ላይ መስዋዕተ ቅዳሴን አሳርገዋል። ቅዱስነታቸው በእዚሁ በእርሳቸው መሪነት በተካሄደው የመስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙትን ስብከት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

 ብዙ ሕዝብ እንደ ተሰበሰበ ባየ ጊዜ. . .” (ማቴ. 51) በእነዚህ በዛሬው የወንጌል የመጀመሪያ ቃላቶች ውስጥ ኢየሱስ እንዴት እኛን ልገናኘን እንደሚፈልግ፣ እግዚአብሔር ዘወትር ህዝቡን የሚያስደንቅበትን መንገድ እናገኛለን። ኢየሱስ መጀመሪያ ያደረገው ነገር የሕዝቡን ፊቶች ማየት እና መመልከት ነበር። እነዚህ ፊቶች የእግዚአብሔርን ጥልቅ ፍቅር ይገልጻሉ ወይም ያሳያሉ። የኢየሱስ ልብ የሚንቀሳቀሰው በጽነሰ-ሐሳቦች ላይ ተመርኩዞ ሳይሆን ነገር ግን የሰዎችን ልብ በመመልከት ነው።

ኢየሱስ ሕዝቡን ሲመለከት፣ በቅድሚያ በቅድሚያ ያደረገው የተከታዮቹን ፊት መመልከት ነበር። በጣም የሚያስደንቀው ግን እነርሱም በበኩላቸው በኢየሱስ ላይ የነበራቸው ፍላጎትና ምኞት ኢየሱስ በአስተዋለው መልኩ መግለጻቸው እና መቀበላቸው ነው። ይህ በኢየሱስ እና በሕዝቡ መካከል የተደረገው ግንኙነት የተራራው ስበክት በመባል የሚታወቀው ስብከት ዝርዝር ሐሳብ እንዲመነጭ በማድረግ፣ እኛ ወደ ተጠራንበት እና የምንሄድበት አድማስ ተግዳሮቶችን እንዲያመለክት አድርጎታል። በተራራው ስብከት ውስጥ የተጠቀሱት ቃላት ነባራዊ እውነታን  እያዩ ዝም ከማለት የመነጩ ፍሬዎች ሳይሆኑ፣  እንዲሁም ደግሞ እየተከሰቱ የሚገኙትን በጣም አስደንጋጭ የሆኑ ነገሮችን እያዩ አኃዛዊ መረጃዎችን በመስብሰብ ላይ ብቻ የተወሰነ አይደለም። ይህ የተራራው ላይ ስብከት በመባል የሚታወቀው ስብከት በሕዝቡ ላይ የሚደርሰውን አስደንጋጭ ሁኔታ፣ በደል ተናግረው ያለፉ ነቢያት ውጤትም አይደለም። ወይም ደግሞ ህልም በሚመስል መልኩ በአንድ ቅጽበት ደስታን እናገኛለን ብለው ከሚጠብቁ ተአምራዊ አመልካከቶች የመነጨ አይደለም ይህ የተራራው ላይ ስብከት። ነገር ግን ይህ ኢየሱስ በተራራው ላይ ያደርገው ስብከት የተወለደው ደስተኛ የሆነ ሕይወት ከሚመኘው የሰዎች ልብ ጋር ለመገናኘት ከሚፈልገው ርኅሩኅ ከሆነው ከኢየሱስ ልብ ነው። ስቃይ ምን መሆኑን የሚያውቁ ሰዎች፣ ግራ የመጋባት መንፈስ እና በእግራቸው ሥር ያለው መሬት ስንቀጠቀጥ እያዩ  ደስ ከሚሰኙ ወይም ደግሞ ሰዎች ቋሚ የሆነ የሥራ ገበታቸውን በሚያጡበት ጊዜ ሕልማቸው ሁሉ ተጠራርጎ ሲጠፋ ዝም እንደ ሚሉ ሰዎች ዓይነት አልንበሩም። ነገር ግን እነዚህ ኢየሱስ በተራራ ላይ ያደርገውን ስብከት የተከታተሉ ሰዎች በብርታት ወደ ፊት መሄድ ምን ማለት እንደ ሆነ የሚያውቁ እና ሕይወታቸውን ለመገንባት የሚጣጣሩ፣ ሕይወትን እንደ ገና በአዲስ መልክ ለመገንባት እና ለመጀመር የሚፈልጉ ሰዎችም ነበሩ።

እንደ ገና ሕይወትን ለመገንባት እና በአዲስ መልክ መጀመርን የሚያውቁ የቺሊያውያን ልብ ምን ያህል ይሆን? ከብዙ ወድቀቶች በኃላ እንደ ገና ተነስቶ መቆም እንደ ሚገባቸው የሚያውቁ ቺሊያዊያን ልብ ስንት ይሆን! ለእነደ እዚህ ዓይነቱ ልብ ነው ኢየሱስ የሚናገረው፣ ለእዚህ ዓይነቱ ልብ ነው ይህ የተራራው ላይ ስብከት የተሰበከው።

በተራራው ላይ ኢየሱስ ያደርገው ስብከት በከፍተኛ ሁኔታ ምክንያታዊ ካልሆነ ባሕሪ የመነጨ ወይም እንዲያው  ዝም ብሎ ነገሮችን እናውቃለን ብለው ከሚያስቡ፣ ነገር ግን ችግሮችን ለመቅረፍ ራሳቸውን ያላዘጋጁ ወይም ፍላጎት ከሌላቸው፣ ለምንም ነገር ወይም ለማንም ሰው አገልግሎት ራሳቸውን ያላዘጋጁ ሰዎች፣ ወይም ደግሞ በማኅበረሰቡ ውስጥ የለውጥ ሂደት እንዳይኖር የሚቃወሙ፣ ማኅበረሰቡ በለውጥ እንዲገነባ ከማይፈልጉ ሰዎች የወጣርካሽ የሆነ ቃልውጤት አይደለም ኢየሱስ በተራራው ላይ ያደረገው ስብከት። ነገር ግን የተራራው ላይ ስብከት የተወለደው መቼም ቢሆን ተስፋ ከማይቆርጥ መኅሪ ከሆነ ልብ ነው። ይህም ልብከፈዘዘ ወይም ከማይንቀሳቀስ፣ በጭንቀቶች ከሚንቀጠቀጥ፣ በአሉታዊ ነገሮች ከተሞላ ተመክሮዎች ተላቂን አዲስ ይሆኑ ቀን እንዲኖረን ያደርጋል።

እንዲህም እያለ ያስተምራቸው ጀመርበመንፈስ ድኾች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፣ ሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፣ የዋሆች ብፁዓን ናቸው፣ ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፣ ስለ ጽድቅ ብለው የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፣ ሰላምን የሚያወርዱ ብፁዓን ናቸው፤ የሚታገሱ ሰዎች ብጹዕን ናቸው. . .” በማለት ፈዘው ወዲያ ወዲህ ማለት ተስኑዋቸው፣ የተለያዩ ጉዳዮች ሕይወታቸውን ተብትቦ በመያዙ የተነሳ፣ ሁሉምን ነገር መቀየር በሚችለው በተለይም ደግሞ ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ሕይወት የመለወጥ  ኃይል ባለው እግዚኣብሔር ላይ የነበራቸውን እምነት አጥተው ለኖሩ ሰዎች  ያስተላለፈው መልእክት ነው። ኢየሱስ በእዚህ በተራራው ላይ ባደረገው ስብከት  ይህንን አሉታዊ የሆነ የሕዝቡን ባሕሪ በማነቃነቅ፣ ከእዚህ የተሻለ ሕይወት ሊኖር አይችልም የሚለውን እመንት በመናድ ሁል ጊዜም አዲስ የሆነ ሕይወት እንዳለ እና ከችግር መወጣት እንደ ሚቻል ሕዝቡ እንዲያስቡ በማደረግ፣ ሰዎች ሁሉ በውስጣቸው ባለው የግል ምቾት ተመክሮ የተነሳ ረስተው የነበረውን ቁም ነገር፣ እንዲሁም ፍጆታ መር የሆነ እለታዊ ሕይወታችን በፈጠረው ስሜት የተነሳ ሞቶ የነበረውን ስሜታችንን ለመቀስቀስ ፈልጎ ያደርገው ስብከት ነው። ከሌሎች እኛን ለማራቅ ፣እኛን ለመከፋፈል እና ለመለያየት የሚያስችለን የሥራ እንድንሰራ በማድረግ በዙሪያችን ያለውን ሕይወት እንዳንመለከት ዓይኖቻችንን በማሳወር የሌሎች ሰዎች ስቃይ እና መከራን እንዳንመለከት ከሚያደርጉን ነገሮች ሊያላቅቀን ፈልጎ ያደርገው ስብከት ነው።

ኢየሱስ በተራራው ላይ ያደርገው ስብከት የወደ ፊቱን ነገር ለሚመለከቱ ሰዎች፣ በቀጣይነት ባለው መልኩ ሕልም ለምያልሙ ሰዎች፣ በእግዚኣብሔር መንፈስ መነካት እና ይህ መነፈስ የሚልካቸው ቦታ ለሜድ ለሚያስቡ ሰዎች ሁሉ  አዲስ ቀን የሚፈጥር ነው ይህ የተራራው ላይ ስብከት። ኢየሱስ በተራራ ላይ ሆኖ እኛንብጹዕን ናችሁ፣ በእግዚኣብሔር መንፈስ የምንቀሳቀሱ ሁሉ ብጹዕን ናቸው፣ አዲስ ቀን ለመፍጠር የሚታገሉ ሰዎች ሁሉ የእግዚኣብሔር መንግሥት የእነርሱ ናት. . . ብሎ ማስተማሩን ማሰብ እንዴት ደስታን ይሰጣል።ሰላምን የሚያወርዱ ብፁዓን ናቸው፤ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉና” (ማቴ 59)

ከአሉታዊ መንፈስ የመነጨ ጥልቅ የነበረውን ግንኙነታችንን የሚያዳክምና እኛን የሚከፋፍለን ይህንንም ክፍፍላችንን የሚያበረታታ ተግባር ላላቸው ሰዎች ሁሉእርቅ ይፈጠር ዘንድ የሚሰሩ ሰዎች የተባረኩ ናቸውበማለት ኢየሱስ ይናገራል።

ሌሎች ሰዎች በሰላም መኖር ይችሉ ዘንድ የሚለፉ ሰዎች ብጹዕን ናቸው። ጥልን ለመዝራት የማይሞክሩ ሰዎች የተባረኩ ናቸው። በመካከላችን የእርቅ መንፈስ የበለጠ እንዲኖር ለማድረግ እንድንሞክር ያሳስበናል። ደስተኞች ለመሆን ትፈልጋላችሁ ወይ? ሌሎች ሰዎች  ደስተኞች ይሆኑ ዘንድ አጥብቀው የሚለፉ ሰዎች የተባረኩ ናቸው። ሰላም እንዲኖራችሁ ተፈልጋላችሁ? እንግዲያውስ ሰላምን ከፈለጋችሁ ለሰላም መሥራት ይኖርባችኃል።

እዚህ ጋርሰላም የምትፈልግ ከሆነ ለፍትህ ሥራበማለት አንድ የሳንቲያጎ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ተናግረውት የነበረውን ነገር ለመጥቀስ እወዳለሁ። አንድ ሰውፍትህ ምንድነው ብሎ ሊጠይቅ ይችል ይሆናልወይም ደግሞ ፍትህ ማለት አለመስርቅ የሚለውን ትርጉም ብቻ ሊያስተጋባ ይችል ይሆናል። እኛ ደግሞ ፍትህ ማለት ሌላ ትርጉም እንዳለው እንናገራለንፍትህ ማለት አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት በእኩልነት መሰትናገድ ይኖርባቸዋል ነው እኛ የምንለው።

ሰላምን በቅርበት መዝራት ይቻላል! ይህንንም በቀላሉ ከቤታችን በመውጣት እና የሰዎችን ፊት በማየት፣ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ለመጎብኘት በመሄድ፣ እንደ ሰው የማይቆጠሩ የማኅበረሰብ ክፍሎችን በመጎብኘት፣ እነዚህን እና እነዚህን በመሳሰሉ ተግባራትን በመፈጸም ሰላምን መዝራት ይቻላል። የወደፊቱን የማይለወጥ እና የማይቀለበስ የሰላም መንገድ ልንዘይድ የሚገባው በእዚሁ  ብቸኛ የሰላም መንገድ ነው። አንድ ሰላም አስከባሪ የሆነ ሰው ስልጣንን ለማየዝ ካለ ጉጉት የተነሳ ታላላቅ ወይም ስውር ስህተቶችን፣ ምኞቶችን ለማሸነፍ እና በሌሎች ሰዎች ትክሻ ላይ ተንተርሶ  "ለራስ ብቻ ስም ማግኘት" በማሰብ ፍልጎት የሚያሳዩ ሰዎችን እንዴት ማሸነፍ እንዳለበት ያውቃል። አንድ ሰላም አስከባሪ የሆነ ሰው እንዲሁ በቀላሉእኔ ማንንም ሰው አልጎዳሁኝምማለቱ ብቻ በቂ እንዳይደለ ያውቃል። ቅዱስ አልቤርቶ ሁርታዶ እንዲህ ይል ነበርከፉ የሆኑ ነገሮችን አለመስራት በራሱ በጣም ጥሩ ነገር ነው፣ ነገር ግን መልካም ነገሮችን አለማከናወን በራሱ ደግሞ በጣም መጥፎ ነገር ነውይል እንደ ነበረ ሁሉ እኛም መልካም የሆኑ ነገሮችን ለመሥራት መትጋት ይኖርብናል።

የሠላም ግንባታ ሂደት ሁላችንንም በጋራ በመጥራት እና ከጎረቤቶቻችን ጋር ያለንን ግንኙነት በማጠናከር፣ ጎረቤቶቻችንን እንደ ባዕድ፣ እንደማናውቃቸው ከማሰብ ይልቅ የአንድ ሀገር ወንድም እና እህት መሆናችንን በመረዳት ይህንንም ለማጠናከር የፈጠራ ችሎታችንን ያነሳሳልናል።

ይህንንም ሁሉ በተግባር ማዋል እንድንችል የእዚህ ከተማ ጠባቂ የሆነችው እኛ ከላይ ሆና ለምታየን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በአደራ እንስጣት።

እርሱ የተራራው ላይ ስብከትን በሕይወታችን በመኖር እንድናሳይ እና በእዚህ ከተማ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ “ ሰላምን የሚያወርዱ ብፁዓን ናቸው፤ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉና” (ማቴ 590) የሚለውን የሎሕሳስ ድምጽ መስማት ይችሉ ዘንድ የበኩላችንን እንድናደርግ እመቤታችን ድንግል ማሪያም በአማላጅነቷ ትርዳን።








All the contents on this site are copyrighted ©.