Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ስብከቶች

ቅዱስነታቸው "ደካማ እና ምስኪን ለሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ንቀት ማሳየት ሰይጣናዊ ተግባር ነው " ማለታቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት መስዋዕተ ቅዳሴን ማሳረጉበት ወቅት

10/01/2018 09:41

ርዕሰ ሊቃን ጳጳሳት ፍራንቸስኮ  በታኅሳስ 30/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገልጹት በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ደካማ እና ምስኪን ለሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ንቀት ማሳየት ሰይጣናዊ ተግባር ነው ማለታቸው ተገለጸ።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በተለያዩ ምክንያቶች ደካማ እና ምስኪን በሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ላይ እንድናሾፍ የሚገፋፋን በውስጣችን ያለው ነገር ምንድን ነው? በማለት ጥያቄን በማንሳት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እጅግ በጣም ጠንካራ የሆኑ ሰዎች ባጣም ደካማ የሆኑትን ሰዎች እንደ ሚበድሉ የሚያሳይ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተከሰቱት በርካታ ክስተቶች እንዳሉ ጠቅሰዋል። በእዚህ ዓይነቱ ባሕሪ ውስጥ ሁል ጊዜም ቢሆን ስይጣን እንደ ሚገኝ የገለጹት ቅዱስነታቸው ስይጣን መቼም ቢሆን የርኅራኄ ስሜት ሊኖረው አይችልም ብለዋል።

በዕለቱ የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የላንቲን ስርዐተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት በቀዳሚነት ከመጀመሪያ መጽሐፈ ሳሙሄል ከ1፡1-8 ላይ ተወስዶ በተነበበው ምንባብ ላይ በተጠቀሰው “በተራራማው በኤፍሬም አገር በአርማቴም መሴፋ የሚኖር ሕልቃና የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም ኤፍሬማዊ ሲሆን፣ እርሱም አንዲቱ ሐና፣ ሌላዪቱ ፍናና የተባሉ ሁለት ሚስቶች ነበሩት፤ ፍናና ልጆች ሲኖሯት፣ ሐና ግን ምንም ልጅ አልነበራትም” በሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ላይ ተመርኩዘው ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ፍናና ጣውንቷ የሆነችውን ሐና ልጅ ስላልነበራት ከማጽናናት እና ከማበረታታት ይልቅ ታስቈጣት፣ ታበሳጫትም ነበር” ካሉ ቡኃላ ይህም ሐና መሐን መሆኑዋን በማስታወስ እንድታዝን እና እንድታለቅስ አድርጓት እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ በተመሳሳይ መልኩ ይህንን ታሪክ የመሳሰሉ በርካታ የሆኑ ሚስኪን የሚባሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች ላይ የሚደረሰውን በደል እና መገለል የሚያሳይ ታሪክ ተጠቅሶ እንደ ሚገኝ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው የአብርሃም ሚስቶች የሆኑት የአጋር እና እንዲሁም መሐን የነበረችሁ የሳራን ታሪክ በዋቢነት ጠቅሰዋል።

በሚስኪኖች  ላይ ማላገጥ እና እነርሱን ማሳፈር ብዙን ጊዜ በእኛ በሰዎች ላይ የሚታይ ባህሪ መሆኑን በመገልጸ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በተጨማሪ የዳዊትን እና የጎሊያድን፣ እንዲሁም በችግር እና በመከራ ውስጥ ይገኙ የነበሩትን ምስኪን የሆኑ ባሎቻቸውን  ስያሳፍሩ እና ስያሰቃዩ የነበሩትን የኢዮብን እና የጦቢያ ሚስቶችን በዋቢነት ማንሳት እንደ ሚቻል ቅዱስነታቸው አክለው ከገለጹ ቡኃላ የሚከተለውን ብለዋል

እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ! በእነዚ ሰዎች ልብ ውስጥ ያለው ነገር ምንድነው? ምስኪን የሆኑ ሰዎችን እንድናዋርዳቸው፣ እንድንገፋቸው እና እንድናላግጥባቸው የምያደርገን በውስጣችን ያለው ነገር ምንድነውበጥንካሬው ከእኛ ከሚበልጥ ሰው ጋር ይህንን ግብግብ የምናደርግ ከሆነ አዎን. . . ምን አልባት  በጥንካሬ ከእኛ የተሻሉ ሆነው በመገኘታቸው የተነሳ በተፈጠረው የቅናት መንፈስ ሊሆን ይችላል ብለን ለመገንዘብ እንችል ይሆናል። ነገር ግን ይህ የማሳፈር እና የማዋረድ ተግባራችንን ምስኪን የሚባሉ ሰዎች ላይ መፈጸማችን ለምን ይሆን? ይህንን እንድናደርግ የሚገፋፋን በውስጣችን ያለው ነገር ምንድነው? የሌላውን ሰው ምስኪንነት ተመርኩዘን ራሳችንን ለመጥቀም እንችል ዘንድ ሌላውን እንደ ሚስኪን በመቁጠር አርሱን በማሳፈር እና በመጨቆን ያራሳችንን ደኅንነት ለማረጋገጥ ከመነጨ ልማዳዊ ፍላጎት ነው? ይህንን እንዴት እንረዳዋለን. . .?”

የእዚህ ዓይነቱ በጭካኔ የተሞላ ድርጊ ሕጻናትም ሳይቀሩ አንድአንዴ የሚፈጽሙት የጭካኔ ተግባር እንደ ሆነ በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እርሳቸው ልጅ በነበሩበት ወቅት የገጠማቸውን ገጠመኝ እነ ሚከተለው አስታውሰዋል. .

“በሰፈራቸው ትኖር የነበረች አንድ በአእምሮ ሕመም በጣም የምትሰቃይ ሴት እንደ ነበረች፣ በሽታዋ በጣም የከፋ ስለነበረ ከቤቷ በመውጣት በየመንገዱ ላይ ትዞር ነበር። ለእዚህች የእዕምሮ እምምተኛ ለሆነችው ሴት አንድ አንድ ሴቶች ምግብ እና አልባሳት ይሰጡዋት ነበር። በወቅቱ የነበሩት ሕጻናት ግን እንሂድና ያችን በእዕምሮ ሕመም የምትሰቃየውን ሴት እንፈልጋት፣ ትንሽ እንዝናናባት በማለት ተጠራርተው ይሄዱ እንደ ነበረ። ሕጻናትም ቢሆኑ ምኪስን በሚባሉ የማኅብረሰብ ክፍሎች ላይ አንድአንዴ  ያላግጣሉ”።

ዛሬም ቢሆን በእየ ትምሕርት ቤቱ ቀጣይነት ባለው መልኩ ምሲኪን እና ደካማ በሆኑ ሰዎች ላይ የማደናበሪያ እና የማስፈራሪያ ተግባራት እንደ ሚፈጸሙ ገልጸው እነዚህን በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ምስኪን እና ደካማ የሆኑ ሰዎችን ለመጉዳት ለመጨቆን፣ ለመጨፍለቅ፣ ለመቆጣጠር ወይም ለማሰቃየት የመፈለግ ዝንባሌ እና እንዲሁም አንተ መጤ የሆንክ ሰው ነህ፣ ወይም ደግሞ አንተ በመልክ ጥቁር የሆንክ ሰው ነህ በማለት የግፍ ጭቆና በስፋት እንደ ሚፈጸም ጠቁመው ይህንን ተግባር በመጽሐፍ ቅዱስ ወስጥ የተጠቀሱት ፍናና፣ አጋር፣ የጦቢት ሚስት ወይም ደግሞ የእዮብ ሚስት የፈጸሙት ግፍ ባቻ ሳይሆን አንድ አንድ ሕጻናትም በተለያዩ ምክንያቶች ደካማ እና ምስኪን በሆኑ የማሕበረሰብ ክፍሎች ላይ የሚፈጽሙት ግፍ እንደ ሆነ ገልጸዋል።

“ታዲያ ይህ ሌሎችን የማዋረድ እና የማሰቃየት ተግባር ከየት ሊመነጭ ቻለ?” በማለት ጥያቄን በማቅረብ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምናልባት የሥነ-አእምሮ ጠበብቶች በሚሰጡት ትንታኔ መሰረት ይህ ባሕሪ የመነጨው ደካማ ወይም ምስኪን የሆኑ ሰዎችን ለማጥቃት ካለ ፍላጎት የመነጨ ነው ብለው ሊመልሱ ይችሉ ይሆናል ካሉ ቡኃላ ለእኔ ግን አሉ ቅዱስነታቸው ለእኔ ግን “የእዚህ ዓይነቱ ባሕሪ የሚመነጨው” “ከሰይጣን እና ከኃጢያት” ነው ብለዋል።

እኛም መልካም ሥራ ለመስራት ስንነሳ፣ በጎ የሆነ ፍልጎት ሲኖረን፣ ለጋሾች ስንሆን፣ እነዚህን እና እነዚህን የመሳሰሉ በጎ የሆኑ ተግባራትን እንድንፈጽም እኛን ያነሳሳን መንፈስ ቅዱስ ነው" ብለን እንደ ምንናገር ሁሉ፣ እኛ በውስጣችን ያለውን ውስጣዊ ፍላጎት መርምረን ይህን በደካሞች እና በሚስኪኖች ላይ ጥቃት የመሰንዘር ፍላጎታችንን የሚያነሳሳው ደግሞ ሰይጣን መሆኑን መረዳት ይኖርብናል ያሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም በተለያዩ ምክንያቶች ደካም እና ምስኪን የሚባሉ የማኅብረሰብ ክፍሎችን ለመበደል የሚያነሳሳን ዲያቢሎስ እና የእርሱ ሥራ በመሆኑ የተነሳ ነው ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማብቅያ ላይ እንደ ገለጹት የርኅራኄን መንፈስ ጸጋ ያጎናጽፈን ዘንድ እግዚኣብሔርን መማጸን እንደ ሚያስፍልግ ገልጸው እግዚኣብሔር ለእኛ ርኅራኄን የሚያደርግ አምላክ በመሆኑ የተነሳ እኛም ርኅራኄን ለሌሎች ማሳየት እንችል ዘንድ አብሮን እንዲጓዝ ልንለምነው ይገባል ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 

10/01/2018 09:41