Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ስብከቶች

ማሪያም የእግዚኣብሔር እናት አመታዊ ክብረ በዓል በደማቅ ሁኔታ በቫቲካን መከበሩ ተገለጸ

ማሪያም የእግዚኣብሔር እናት አመታዊ ክብረ በዓል በደማቅ ሁኔታ በቫቲካን መከበሩ ተገለጸ - AFP

02/01/2018 16:13

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ ክርስቲያኖች ዘንድ 2018 ዓ.ም. የአዲስ አመት በዓል በትላንትናው እለት በደማቅ ሁኔታ ተክብሩዋል። በዚሁ የአዲስ አመት መጀመሪያ ላይ የእግዚኣብሔር እናት የሆነችው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም አመታዊ ክብረ በዓል ተከብሮ አልፉላ። በእለቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በእርሳቸው መሪነት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙትን ስብከት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትታደሙ ከወዲሁ በማክበር እንጋብዛችኃለን።

የዚህን ዝግጅት ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ይህ አዲስ አመት የሚጀምረው የእግዚኣብሔር እናት በሆነችው በማሪያም ስም ነው። የእግዚአብሔር እናት የሚለው መጠሪያ ለማሪያም የተሰጣት በጣም አስፈላጊ የሆነ መጠሪያ ነው። ነገር ግን እርሷ የኢየሱስ እናት ሆና ሳለች ለምንድነው የእግዚኣብር እናት ብለን የምንጠራት? ብለን እንጠይቅ ይሆናል። ቀደም ባሉት ጊዜያት የነበሩ ክርስቲያኖች ማሪያም የኢየሱስ እናት ናት የሚለውን መጠሪያ ቀለል ባለ መልኩ ተቀብለውት የነበረ ቢሆን ቤተ ክርስቲያን ግን ማሪያም የእግዚአብሔር እናት ናት ብላ አውጃለች። ለዚህም ምክንያት እነዚህ ቃላት ስለእግዚአብሔርና ስለእራሳችን ታላቅ ምስጢር እውነታን የያዙ በመሆናቸው የተነሳ ልናመስግን ይገባል። ጌታችን በማርያም ውስጥ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ፣ ለዘለአለም ሰብአዊነታችንን ተላብሱዋል።

ኢየሱስ ሰውም አምላክም ነው፣ ኢየሱስ ከእናቱ የወሰደው ሥጋ ዛሬም ዘወትርም ለዘለአለምም የእኛ ሥጋ ነው። ማሪያምን የእግዚኣብሔርን እናት ብሎ መጥራት አንድ ሕፃን በእናቱ ማህፀን ውስጥ ሆኖ ከምትወልደው እናቱ ጋር ቅርብ እንደ ሆነ ሁሉ በዚህም ልክ አምላክ ለሰው ልጆች ቅርበት እንዳለው ያመለክታል ይህንኑ ሁኔታ ያስታውሰናልም።

እናት የሚለው ቃል ቁስ አካል ከሚለው ቃል ጋር ይዛመዳል። በእናቱ አማክይነት የሰማይ አምላክ የነበረው እርሱ ራሱን ዝቅ አደረገ፣ ከእኛ ጋር ለመሆን ባቻ ሳይሆን ነገር ግን እኛን ለመምሰል ፈልጎ ወደ አንድ ቁስ አካልነት ተቀየረ። ይህም ታላቅ የሆነ ተአምር እና ድራማዊ የሆነ ክስተት ነው። የሰው ልጅ ከአሁን ቡኃላ ብቻውን አይደለም፣ የሰው ልጅ ከአሁን ቡኃላ ወላጅ አልባ አይደለም፣ ነገር ግን ለዘለአለም የልጅነት መብት ያለው ሆኖ ይኖራል። ይህ አዲስ አመት የሚጀምረው በዚህ ድራማዊ በሚመስል ክስተት ነው። ይህንንም ማሪያምየእግዚኣብሔር እናትብለን በማወጅ እንጀምራለን። የእኛ የብቸኝነት መንፈስ ማብቂያ እንዳገኝ ማወቅ ደግሞ ከፍተኝ የሆነ ደስታን ይፈጥርልናል። የእኛ የልጅነት መብት ምንም ጊዜ ቢሆን ከእኛ ፈጽሞ ሊወሰድ እንደማይችል ማወቃችን እና ውድ ልጆች መሆናችንን ማወቃችን በራሱ ድንቅ ነው። ጨቅላ እና ሕፃን የሆነ አምላክ በእናቱ እጆች ውስጥ ማረፉ ይህንንም ነጸብራቅ ወደ ራሳችን በማምጣት የሰው ልጅ ለአምላኩ ውድ እና የተቀደሰ መሆኑን መረዳት እንድንችል ይረዳናል። በእዚህ መሰረት የሰውን ሕይወት ማገልገል ማለት አምላክን ማገልገል ማለት ነው። በእናት መህጸን ካለው ሕይወት አንስቶ ከእስከ ሽምግልና ድረስ ያለ ሕይወት ሁሉ፣ የታመሙ እና የሚሰቃዩ ሰዎች፣ ሚያስጨንቁ እና እንዲያውም ሌላውን ሰው ለመጉዳት በማሰብ የሚበቀሉ ሰዎች ሳይቀር ሕይወታቸው ውድ፣ በመሆኑ የተነሳ መወደድ እና መረዳት ይኖርባቸዋል።

ዛሬ በተነበበል ቅዱስ ወንጌል እንመራ። የእግዚኣብሔር እናት ሰለሆነች ስለ ማሪያም አንድ ነገር ተብሉዋልማርያም ግን ይህንን ሁሉ በልቧ ይዛ ታሰላስል ነበር” (ሉቃስ 219) ይላል። ሁሉንም ነገር በልቧ ይዛ ነበር። እንዲህ ቀለል ባለ መልኩ እነዚህን ነገሮች ሁሉ በልቧ ይዛቸው ነበር፣ ማሪያም ምንም ነገር አትናገርም። በዚህ በገና ሰሞን በተነበቡልን የወንጌል ምንባባት ውስጥ ማሪያም ተናግራለች የሚል አድ ቃል እንኳን አናገኝም። በዚህም ረገድ ይህቺ እናት ከልጇ ጋር ተመሳስላ ነበር፣ ምክንያቱም ኢየሱስ ሕጻን በመሆኑ የተነሳ አንድ ሕጻን ልጅ መናገር እንደ ማይችል ሁሉ እርሷም እንደ እርሱ ዝም አለች።እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በተለያየ ጊዜና በልዩ ልዩ መንገድ”(ዕብራዊያን 11) የተናግረው ቃል ነገር ግን አሁንየተወሰነው ዘመን በደረሰ ጊዜዝምታን መረጠ። ሁሉም ሰዎች በፊቱ በጸጥታ የሚቆሙለት አምላክ ራሱ እንደ ልጅ በመሆን ዝም አለ። ታላቅ የሆነው ምንም ቃል ስይተነፍስ ነበር፣ ይህም የታላቅነቱ የፍቅር ምስጢር በብቸኝነቱ ይገለጻል። ይህ ዝምታ እና ብቸኝነት የእርሱ የንግሥናው መገለጫ ቋንቋዎች ናቸው። እናቱም ብትሆን የልጇን አብነት በመከተል እርሷም እነዚህን ነገሮች ሁሉ በዝምታ በላቧ ይዛቸው ቆየች።

ይህ ዝምታራሳችንን መጠበቅ ከፈለግንዝም ማለት እንደ ሚያስፈልግ ያስተምረናል። ሕጻኑ ወደ ተኛበት ጋጣ በምንመለከትባቸው ወቅቶች ሁሉ በዝምታ ማዳመጥ እንደ ሚኖርብን ያስተምረናል። ይህንን ሕጻኑ የተኛበትን ሥፍራ መመልከት በራሱ እኛ ተወዳጅ እንደሆንን ይነግረናል፣ ትክክለኛውን የሕይወት ትርጉም እንድንረዳም ያደርገናል። በዝምታ ሆነን ሕጻኑ የተኛበትን ሥፍራ መመልከት ኢየሱስ በልባችን ውስጥ ዘልቆ እንዲናግረን መንገዱን ይከፍታል። የእርሱ ብቸኝነት የኩራት መንፈሳችንን እንድቀንስ ያደርገናል፣ የእርሱ ድኽነታችንን መላበሱ ደግሞ ለእኛ የታይታ መንፈስ  ተግዳሮት ይሆናል፣ የእርሱ በርኅራኄ የተሞላ ፍቅር ደንዳና የሆነውን ልባችንን ይነካል።

በእያንዳንዱ ቀን ከእግዚአብሔር ጋር በዝምታ ማሳለፍ ነፍሳችን "እንድትኖር ያደርጋታል ነጻነታች በከንቱ ቃላት፣ ጫጫታ እና የመሳሰሉ ነገሮች ነጻነታችንን እንዳናጣ ይረዳናል።

ቅዱስ ወንጌል ማሪያም እነዚህን ነገሮች ሁሉ በዝምታ በልቧ ውስጥ ይዛቸው ታሰላስል እንደ ነበረ ያወሳል። እነዚህ ነገሮች ምድናቸው? እነዚህ ነገሮች ደስታ እና ሐዘን ናቸው። በአንድ በኩል የኢየሱስ መወለድ፣ የዮሴፍ ፍቅር፣ በእረኞች መጎብኘታቸው፣ ደማቅ የሆነ ምሽት ይህን እና ይህንን የመሳሰሉትን በጎ ነገሮች እናገኛለን። ነገር ግን በሌላ በኩል ደግሞ ወደ ፊት ምን እንደ ሚከሰት እርግጠኛ ባለመሆን፣በእንግዶችም ማረፊያ ቦታ ስላላገኙ በግርግም አስተኛችውመጠለያ አልባ በመሆናቸው፣ በመገለላቸው የተነሳ የተፈጠረው የባዶነት ስሜት፣ ኢየሱስን በጋጣ ውስጥ መውለዷ ተስፋ አስቆራጭ የሆነ ስሜት ፍጥሮባታል። ተስፋዎችና ጭንቀቶች፣ ብርሃንና ጨለማ: እነዚህ ሁሉ ነገሮች በማርያም ልብ ውስጥ ይኖሩ ነበር። ታዲያ እርሷ ምንድን ነው ያደረገችው? እሷም እነዚህን ነገሮች በልቧ ውስጥ በማሰላሰል ከእግዚአብሔር ጋር በልቧ ትነጋገር ነበር። ምንም የደበቀችሁ ነገር አልነበረም፣ በእነዚህ ሁኔታዎችም ውስጥ ሆና እንኳን እነዚህን ነገሮች እንደ መጥፎ ነገሮች አልቆጠረቻቸውም ነበር። እንዲያውም ሁሉንም ነገሮች ለእግዚኣብሔር በአደራ ስጥታ ነበር። እነዚህንም ነገሮች የጠበቀችሁ በዚሁ መልኩ ነበር። ህይወታችንን በፍርሀት፣ በጭንቀት ወይም በአጉል እምነት፣ ውስጥ በትገባበት ወቅት ልባችንን መዝጋት ወይም ለመርሳት መሞካር ሳይሆን የሚኖርብን ነገር ግን ሁሉንም ነገር አውጥተን ከእግዚአብሔር ጋር ወይይት ማድተግ ያስፈልጋል። በልቡ ውስጥ የሚያኖረን እግዚኣብሔር አምላክ በዚህ ወቅት በልባችን ውስጥ ለመኖር የመጣል።

ስለዚህ እነዚህ ነገሮች የእግዚኣብሔር እናት ምስጢሮች ነበሩ፣ ሁሉንም ነገር በጥሩ ሁኔታ በመያዝ ወደ እግዚአብሔር ታቀርባቸው ነበር። እነዚህ ነገሮች ሁሉ በማሪያም ልብ ውስጥ እንደ ነበሩ ቅዱስ ወንጌል ይነግረናል። ልባችን የሰው ልጆችን ሕይወት እና ፍቅር በጥልቀት እንድንመለከት የሚያደርገን የአካል ክፍል ነው። በዚህ በአዲስ አመት መጀመሪያ ላይ እኛም በዚህ ምድር ላይ ተጓዢ የሆንን ክርስቲያኖች፣ አስፈላጊ ያልሆኑትን ነገሮች ከበስተጀርባችን በመተው እና በጣም አስፈላጊ የሆኑት ነገሮችን ይዘን  ወደ ፊት መራመድ ለመጀመር አስፈላጊነት የሆኑ ነገሮችን ማድረግ ይገባናል። ዛሬ ለአብነት የሚሆነን ነገር በፊት ለፊታችን ይገኛል፣ ይህም የእግዚኣብሔር እናት የሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ናት፣ እግዚኣብሔር እኛን እና ቤተክርስቲያን እንደ ማሪያም እንድንሆን ይፈልጋል፣ ይህም በጣም ትሁትና ምስኪን የሆነን፣ በቁሳዊ ሀብቶች ድኸ የሆነች ነገር ግን በፍቅር የተሞላች፣ ከኃጢአት ነጻ የሆነች እና ከኢየሱስ ጋር የተዋሀደች እናት በመሆን፣ እግዚአብሔርን በልባችን እና በጎረቤታችን ውስጥ በማኖር በሕይወታችን ውስጥ እግዚአብሔርን መጠበቅ መቻል ይኖርብናል።

ይህንንም ብለን ለመጀመር እናታችንን እንመልከት። የልቧ ትርታ የቤተ ክርስቲያንን ልብ ይነካል። የዛሬው በዓል ወደ ፊት መጓዝ ከፈለግን ወደ ኋላ መመለስ እንዳለብን ይነግረናል። በእጆቿ ውስጥ እግዚኣብሔርን በአቀፈችው እናቱ እቅፍ ውስጥ በመሆን ሕይወታችንን እንደገና መጀመር ይኖርብናል።

ለማርያም መሰጠት ማለት መንፈሳዊ ስነ-ምግባር ማሳየት ማለት ብቻ ሳይሆን፣ ከአንድ ክርስቲያን ሕይወት የሚጠበቅ መስፈርት ጭምር ነው። ይህችን እናት በመመልከት ጠቃሚ ያልሆኑ ኮተቶቻችንን ወደ ኃላ አሽቀንጥረን በመጣል በጣም አስፈላጊ የሚባሉ ነገሮች መፈለግ ማለት ነው። የእናታችን ስጦታ እያንዳንዷ እናት እና ሴት የሚሰጡን ዓይነት ስጦታ በመሆን፣ ለቤተ ክርስቲያን በጣም ውድ የሆነ ስጦታ ይሆናል፣ ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን ራሷ በእናት እና በሴት ስለምትመሰል ነው። ወንድ ልጅ ብዙውን ጊዜ በአፅንዖት ሐሳቦችን እና እቅዶችን በሰው ላይ ለመጫን ይፈልጋል፣ ነገር ግን ሴት እና እናት ሐሳቦችን እና እቅዶችን በአንድ ላይ በማቀናጀት "እንዴት መጠበቅ" እንደ ሚቻል ያውቁበታል በዚህም ተግባራቸው ሕይወት ይሰጣሉ። እምነታችን ወደ ምናብ ወይም ደግሞ ሕይማኖታዊ አስተምህሮ ብቻ ላይ ትኩረት ወደ ማድረግ ላይ ብቻ ያነጣጠረ ከሆነ ሁላችንም የእናት ልብ ያስፈልገና ማለት ነው፣ የእግዚኣብሔርን በርኅራኄ የተሞላ ልብ ማወቅ የሚፈልግ ሰው የእያንዳንዳችንን የልብ ምት ማወቅ ይኖርበታል። እግዚኣብሔር ከፈጠራቸው ፍጥረታት ሁሉ በላይ መልካም የሆነች እናታችን ይህንን አዲስ አመት በመጠበቅ የልጇን ሰላም በልባችን እና በዓለማችን ውስጥ ታኑርልን። ልጆች እንደ መሆናችን መጠን በትሕትና በኤፊሶን የሚገኙ ክርስቲያኖች ከጳጳሳቸው ጋር በመሆን ማሪያምንቅድስት የእግዚኣብሔር እናት ሆይ!” በማለት ሰላምታ እንዳቀረቡላት ሁሉ እኛም በተመሳሳይ መንገድየእግዚኣብሔር እናት ሆይ ሰላምታ እናቀርብልሻለን ማለት እንችል ዘንድ ሁላችንም ይህንን ጸሎት በአንድነት እንድንደግም ጥሪ አቀርባለሁ!

02/01/2018 16:13