2018-01-01 16:50:00

በየመን፣ በአማጺያኖች ላይ በተከፈተው ጥቃት 71 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ።


በየመን፣ በአማጺያኖች ላይ በተከፈተው ጥቃት 71 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ።

በየመን፣ በአማጺያኖች ላይ በተከፈተው ጥቃት 71 ሰዎች ሲገደሉ ከእነዚህም መካከል 11 ሕጻናት መሆናቸው ታውቋል። የመን ከ2007 ዓ. ም. ጀምሮ በከፋ ጦርነት ውስጥ መሆኗ ይታወቃል።

በአዲስ መልክ በተቀሰቀሰው ጦርነት፣ ባለፉት 48 ሰዓታት ውስጥ ብቻ በአረብ ጦር የታገዙት የመንግሥት ወታደሮች ባደረሱት ጥቃት ከ71 ሰዎች በላይ፣ ከእነዚህም 11 ሕጻናት እና ሌሎች በርካታ ሰላማዊ ሰዎች እንደሚገኙበት ታውቋል።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

 

በደቡባዊው የሀገሪቱ ክፍል፣ ሃይስ በተባለ አካባቢ በአማጺያኑ ላይ በተከፈተው ጥቃት 18 የአማጺያኑ ወታደሮች መገደላቸው ሲነገር፣ በሁቲ ወታደሮች ቁጥጥር ስር በምትገኝ በሆደይዳ ወደብ አቅራቢያ በተካሄደው የቦምብና የአውሮፕላን ጥቃት 35 የአማጺያኑ ወታደሮች መገደላቸው ታውቋል። በዋናዋ ከተማ በስንዓ አካባቢ በተካሄደው የአየር ላይ ጥቃትም የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ ሰባት ሰዎች መገደላቸው ታውቋል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2015 ዓ. ም. ጀምሮ በየመን ውስጥ በአረብ አገራት የሚታገዝ የመንግሥት ሚሊሻዎች በሆኑ የሱኒ እምነት ተከታዮችና በኢራን በሚታገዘው እና ዋና ከተማዋን ጨምሮ አንዳንድ የአገሪቱን ግዛት በሚቆጣጠረው የአማጺያኑ ሁቲ ሚሊሻዎች መካከል ከባድ የርስ በርስ ጦርነት ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል።       

ህዳር 25 ቀን 2010 ዓ. ም. የአገሪቱ የቀድሞው ጠንካራ ፕሬዚዳት የነበሩት አሊ አብዱላህ ሳላህ በሁቲ ተዋጊዎች መገደላቸው ይታወሳል። በኢራን የተደገፉ ሃይላት፣ በበርካታ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እውቅና የተሰጣቸውን፣ ፕሬዚዳንት አብድራቦ ማንሱር ሃዲ ላይ ጦርነት እያካሄዱ ይገኛሉ።

የዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳሬክተር፣ ዴቪድ ብስሌይ፣ በሃገሪቱ ሰብዓዊ ቀውስ የከፋ መሆኑን ገልጸው  ለጋሽ አገሮች እርዳታን እንዲቀርቡ ተማጽነዋል።

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.