2017-12-28 14:00:00

በፊሊፒን አገር በርካቶች የዘንድሮን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው እንዳከበሩ ተሰማ።


በፊሊፒን አገር፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች፣ የዘንድሮን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ልደት በዓል ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው እንዳከበሩ ተሰማ።

የዚህን ዜና ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በፊሊፒን ሃይለኛ አውሎ ነፋስ ባስከተለው አደጋ ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች፣ የዘንድሮን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ልደት በዓል፣ በተጠለሉበት ድንኳን ውስጥ ሆነው ማክበራቸው ተሰማ። ተምቢን በተባለ አካባቢ በአደጋው የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 240 መድረሱ ታውቋል። ከ35 ሺህ ቤተሰብ በላይ መኖሪያ ቤታቸው በመሬት መሸርሸር እና በጎርፍ እንደወደመባቸው ታውቋል። በተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት እንዳስታወቀው፣ የአደጋው ሰለባዎች በተጠለሉበት ጣቢያ የተላላፊ በሽታዎች መዛመት ስጋት ከፍተኛ እንደሆነ አስጠንቅቋል።

በፊሊፒን፣ ተምቢን በተባለ ሥፍራ፣ በሺዎች ለሚቆጠሩ ተፈናቃዮች የዘንድሮ የብርሃነ ልደቱ በዓል ወቅት ምቹ እንዳልሆነላቸው ታውቋል። ወደ 21 ሺህ የሚጠጉ ቤተሰቦች፣ ሚንዳናዎ በተባለች ደቡባዊ ደሴት በተዘጋጁላቸው 26 ጣቢያዎች ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን  ከ20 ሚሊዮን በላይ የደሴቲቱ ነዋሪዎች ሃይለኛ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍና በፈጣን አውሎ ነፋስ የተጎዱ እንደሆነም ታውቋል። በተመሳሳይ አደጋ የተፈናቀሉ የተለያዩ አውራጃዎች ነዋሪ የሆኑ ከ16, 500 በላይ ቤተሰቦች ከዘመዶቻቸው ተጠልለው እንደሚገኙ ታውቋል።

በአደጋው 240 ሕይወታቸውን እንዳጡ ሲነገር ከእነዚህም 135 ሺህ ከሚንዳናዎ ሰሜናዊ ክፍል፣ የተቀሩት የአደጋው ሰለባዎች ከደቡባዊው ክፍል እምደሆንና ይህ ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል በሥፍራው እርዳታን በማዳረስ ሥራ ከተሰማረው ድርጅት ለማወቅ ተችሏል። እንደ እርዳታ አቅራቢዎች መረጃ መሰረት 107 ሰዎች የደርሱበት እንደማይታወቅና ፍለጋውም እንደቀጠል ተነግሯል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕጻናት መርጃ ድርጅት በበኩሉ እንዳሳሰበው ይህን የተፈጥሮ አደጋን ተከትሎ ሕጻናትንና ወላጆቻቸውን የሚያጠቁ የወረርሽኝ በሽታዎች ሊዛመቱ እንደሚችል የሚታወቅ ሲሆን ድርጅታቸው አስፈላጊውን እርዳታ ለማቅረብ ዝግጁ እንደሆነ በፊሊፒን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕጻናት መርጃ ድርጅት ተጠሪ የሆኑት ሎታ ሲልዋንደር አስታውቀዋል። ተጠሪው እንዳስታወቁት ማራዊ በተባለ ከተማ የአደጋው ተጠቂዎች የተጠለሉበት በአውሎ ነፋስ መወሰዱንና በርካታ ቤተሰቦች ያለ መጠለያ መቅረታቸው ችግሩን አባብሶታል ብለዋል።

ዘንድሮ ከተከበርው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ልደት በዓል ጥቂት ቀናት አስቀድሞ በሰሜናዊው የፊሊፒን፣ አጉ በተባለ ግዛት የጣለው ሃይለኛ ዝናብና አውሎ ነፋስ፣ ለ20 ስዎች ሕይወት መጥፋት ምክንያት ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል 6 ሕጻናት እንደሆኑ ታውቋል። የአደጋው ሰለባዎች በአሙሉ የአንድ ቤተሰብ አባላት ሲሆኑ፣ በዝናብና አውሎ ነፋስ መካከል ከሚኖሩበት አካባቢ ተነስተው፣ የብርሃነ ልደት በዓል መስዋዕተ ቅዳሴን ለማሳረግ ወደ ሌላ ሥፍራ በመጓዝ ላይ እንዳሉ በደረሰባቸው የመኪና አደጋ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።   

              








All the contents on this site are copyrighted ©.