Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ቤተ ክርስትያን \ ኢትዮጵያ

የኢትዮጲያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ፣ ከኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጉባኤ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጲያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ፣ ከኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጉባኤ የተሰጠ መግለጫ - RV

28/12/2017 10:09

+በስመ አብ፣ ወወልድ፣ ወመንፈስ ቅዱሰ፣ አሀዱ አምላክ፡፡ አሜን፡፡

አምላክ ሆይ ሕዝብህን አድን፣ የአንተ የሆኑትንም ባርክ፣

እረኛቸውም ሁን፣ ለዘለዓለም ተንከባከባቸው። መዝ.፳፰፣፱

 

 

ስለሀገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ፣

ከኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጉባኤ የተሰጠ መግለጫ፡

 

 

ለመላው ካቶሊካውያንና በጎፊቃድ ላላቸው ኢትዮጵያውያን ሁሉ የእግዚአብሔርር ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን፡፡

እኛ የኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጉባኤ አባላት በዚህ ሳምንት በሚጠናቀቀው በ43ኛው መደበኛ ጉባኤችን ስለአገራችን ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ከገዳማውያን፣ ገዳማውያት፣ ካህናት እና ምእመናን በያሉበት በቅዳሴ ጸሎት ስናደርስ ሰንብተን ዛሬ የሚከትለው መልእክታችን ለማስተላለፍ ወደናል።

የዚህን መግለጫ ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ከሁሉም በፊት በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት በጠፋው ክቡር የሰው ሕይወት የተሰማንን መሪሪ ሃዘን እየገለጽን የሞቱ ወገኖቻችንን ቸሩ እግዚአብሔር አምላክ በመንግሥተ ሰማይ በምህረቱ እንድቀበላቸው፣ ለቤተ ሰቦቻቸውም መጽናናትን እንዲሰጣቸው ጸሎታችንን እንቀጥላለን። እንደዚሁም በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ከየቀዬአቸው ለተፈናቀሉ ወገኖቻችንና ሀብት ንብረታቸው ለወደመባቸው ከልብ የመነጨ ሀዘናችን እንገልጻለን፡፡  

የአገራችን የኢትዮጵያ ሕዝቦች በብዝኃነት ውስጥ ያለውን አብሮ ተከባብሮ፣ ተባብሮ የመኖርን ምስጥር  ብቻ ሳይሆን ይህ ከእግዚአብሔር የተስጠ ድንቅ የሆነ ጸጋ በውጭ ኃይሎች እንዳይበርዝ በጋራ በመከላከል የነጻነት ተምሳሌት በመሆን እንድንጠራ አድርገዋል።  ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን፡ ይህ መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ እሴቶቻን አደጋ ላይ የሚጥል ፈተናዎች እያተጋረጡብን መጥተዋል። ቀጠናችን ዘርፈ ብዙ በሆኑ ምክንያቶች ቢሆንም ግን በብሔረተኝነት የሚገለጹ በመንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ማንነታችን የሚፈታትኑ  ግጭቶች እየተከሰቱ ናቸው። በነዚህ ግጭቶች ምክንያት በርካታ ወገኖችን ለህልፈተ ሕይወት፣ የተረፉትን ደግሞ ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ ሆኖዋል።

እንደሚታወቀው፡ በምስራቅ አፍርቃ የሚገኙ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፡ ለረጂም ዘመናት ልዩነታቸውን የአንድነት ምንጭ አድርገ፡ በሰላምና ባንድነት፣ በመደጋገፍና በፍቅር ሲኖሩ ቆይተዋል፡፡

 

ይህንንም ሁኔታ ስላሳሰበን በምሥራቅ አፍርቃ ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት አባል አገሮች ታንዛንያ፣ ማላዊ፣ዛምብያ፣ዩጋንዳ፣ኬንያ፣ ኢትዮጲያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኤርትራ፣ እና ታዛቢ አገሮች ጁቡቲ እና ሶማልያ ከ 2006 ዓ.ም. ጅምሮ ከእግዚአብሔር ስለተሰጠው የብዝኀነት፣ የሁሉም የሰውልጅ እኩል ክቡርነትና ሰላም ስናመሰግን፣ በሐጢአት ምክንያት ይህ ታላቅ ጸጋ እንዳይወሰድብንም ስንጸልይ ከርመናል።  ይህን መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የምስራቅ አፍርቃ ጳጳሳት ጉባኤን በሐምሌ ወር 2010 ለማካሄድ ዝግጅት በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡ ጉባኤውን የሚያውጠነጥነው በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሠረተ ሕያው ብዝኃነት፣ሰብአዊ ክብርና ሰላማዊ አንድነት ለአመሰያ ሀገራት የሚል መሪ ላይ ነው፡፡ ይህን መሪ ቃል የመረጡበት ዋናው ምክንያት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየታዩ ያሉ የብሔሬተኝነት ጉዳዮች ወደ ዘረኝነት ሊያመሩ የሚችሉ አዝማሚያዎች በመገንዘብ ነው፡፡

ይህንን አስከፊ ክስተት ለመቀልበስና፡ ኣከባቢውን ዳግም ወደ ነበረበት የሰላምና ተከባብሮ ኣብሮ የመኖር ቀጠና ለመመለስ፡ የካቶሊክ ቤተክርስትያን፡ ለቀጠናው ህዝብ በተለይም ለአገራችን ሕዝቦች እርቀ ሰላሙ፣ እንዲሁም ደግሞ ህብረቱ ተፋቅሮና ተከባብሮ የመኖር ጸጋ ተመልሶ እንዲመጣ በማድረግ ሂደት፡  የበኩሉዋን ነቢያዊና ሞራላዊ ሃላፊነት ትወጣ ዘንድ እንደሚገባት ትገነዘባለች፡፡ ይህንን ኣንገብጋቢ ተልእኮ ባ ግባቡ መወጣት ትችል ዘንድ ደግሞ፡ በሂደቱ የካቶሊክ ቤተክርስትያን፡ ሚናና ድርሻ ምንነትና ኣስፈላጊነት ላይ በጥልቀት መመርመርና ማሰላሰል ኣስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በዚህም ምክንያት፡ የምሥራቅ አፍርቃ ካቶሊክ ቤተክርስትያን የጳጳሳት ጉባኤዎች ህብረት ይህንን ጉባኤ ጠርቷል፣ በኢትዮጲያም እንዲካሄድ ምልአተ ጉባኤው ከአራት ዓመት ብፊት ወስነዋል፡፡ ጉባኤው በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ በጥልቀት እንደሚወያ ይጠበቃል፣ በአመዛኙ የትኩረት አቅጣጫ ሊሆኑ የሚችለው ጉዳዮች፤

በ19ኛው የኅብረቱ ጉባኤችን በእግዚአብሔር ላይ የተመሠረተ ሕያው ብዝኃነት፣ ሰብአዊ ክብርና ሰላማዊ አንድነት ለአመሰያ ሀገራበሚለው መሪ ቃል መሰረት፡ የቀጠናውን ሁኔታ በጥልቀት መመርመር፣

 • < > ብዝሃነት በቀጠናው ለሚኖሩ ሕዝቦች አብሮ የመኖርን ጉልበት፣ተስፋ እንደሆነ፣< > እድገት ብዝሃነትን ስለመቀበል፣< > ክብርን ለእውነተኛ ኣንድነት ስለማስተዋወቅ፣በመሆኑም፣ የአገራችንም ተጨባጭ ሁኔታ የዚሁ የምሥራቅ አፍሪቃ ቀጠና አካል በመሆኑ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሀገራችን የብዙኀነት ጸጋዎች ሁኔታዎች ጎልተው መሰማትና መታየት ጀምረዋል፡፡ የብዝኃነት እሳቤዎች ምንጩ ከእግዚአብሔር ስለሆነ መልካም ነው ሆኖም በአንዳንድ አጋጣሚዎች እነዚህን የብዙኀነት እሳቤዎችን ተከትለው የሚነሱ ጥያቄዎችን በጊዜና በአግባቡ አለማስተናገድ የሚፈጥረው የፍርሃት ጫና እና የእርስ በርስ ጥርጣሬ ቢስተዋልም የሰው ልጅ ሕይወት ግን ከማንኛውም ጥያቄና ፍላጐት በላይ በእግዚአብሔር የተሰጠን ክቡር ስጦታ ስለሆነ በሰው ሕይወት ላይ የሚመጣው አደጋ ፍጹም ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም፡፡

   

  በሕይወትና በንብረት አደጋ የሚያመጣ አካሄድ ለዘመናት አብሮ ለኖረው ሕዝብና ብሎም ለአገራዊ አንድነት፣በሰላም ድህነትን በጋራ ለማሸነፍ ተስፋዎችን የሚያመነምን በመሆኑ ልናስወግደው ይገባል፡፡ ማህበረሰባችን ሌላውን የማዳመጥ የመቀበል፣ የማከበር፣ ይቅር የማለትን ወርቃማ ባሕል እየዳበረ የሕይወት ትስስራችንንም በማሳደግ ሁሉም የሕብረተሰብ አካላት የመጠበቀ ግዴታችሁን እንድትወጡ በእግዚአብሔር ስም አደራ እንላለን፡፡

  እግዚአብሔር ፍጥረትን ሲፈጥር በብዙሃነት እሳቤ ፈጥሮአል፡፡ በመሆኑም ይህ ብዙሃነት እርስ በርስ በሚደጋገፍ ትስስር ላይ የተመሠረተ በመሆኑ የተፈጥሮ ልዩነቶች የአንድነትም መሠረት መሆናቸውን እንረዳለን፡፡ እኛም እንደዚሁ ልዩነታችንን እንደ ተፈጥሮ ፀጋ በመቀበል እርስ በርስ በመከባበር በመቻቻል፣ በመደጋገፍ፣ በመረዳዳት በይቅርባይነት መንፈስ የተጣሉትን በማስታረቅ፣ ውልጆቻቸው ያጡ የሆኑ ልጆችን በመርዳት፣ ከቤት ንብረታቸውም የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቦታቸው እንደመለሱ በማገዝ የአብርነታችንን ውበትና ጥንካሬ እንደገና እንዲንሰራራ የማድረግ የሁሉም ሀገርና ወዳድ ዜጋ ሃላፊነት መሆን አለበት፡፡

  የብዝኀነት ጉዳይ ሲነሳ በተለይ የሀገራችን ሕዝብ በደም፣ በሥጋ፣ በጋብቻ፣ በባህልና በማህበራዊ ኑሮ የተሳሰረ በመሆኑ የአንዱ ሀዘንና ችግር የጋራ ሀዘችንና ችግራችንነ ው፡፡ አንዱ ሲደሰት ሌላዉም ይደሰታል፣ አንዱ ሲያለቅስ ሌላውም ያለቅሳል፡፡ በተለይም በቅርብ ጊዜ በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልሎች መሃከል እንዲሁም በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች በተከሰተው ግጭት የጠፋው የሰው ሕይወት እ ያሳዝነናል፡፡

  በተመሳሳይ መልኩ የፍቅርና የወንድማማችነት መገለጫ መሆን የሚገባው የስፖርት ውድድሮች የጥላቻና የተቃርኖ መገለጫዎች  ሆነዋል፡፡ ከፍተኛ የትምህርት ተቅዋማት የዕውቀት መገብያ ማዕከል መሆን ሲገባቸው የግጭትና የሕይወት መጥፊያና የንብረት ማውደሚያ ማዕከል ሆነው መታየታቸው ያስቆጨናል፡፡  ይሁንና ለዘመናት የቆየው ማህበራዊና ቤተሰባዊት ስስራችን በአሁኑ ሰዓት ለተከሰተው ግጭትና አለመተማመን የእርቅ ተምሣሌነት በመሆን በጨለማ ውስጥ የእርቅ ብርሃን እንዲሰነጥቅ፣ የተጋጩትም እንዲታረቁ በማድረግ፣ የተፈናቀሉትም ወደየቀዬያቸው እንዲመለሱ፤ ንብረት ለወደመባቸው እንደገና እንዲያንሰራሩ በማገዝ የቆሰሉ ልቦችን ለመፈወስ መንግስት፣የሃይማኖት ተቃዋማት፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች በጎፍቓድ ያላችሁ ኢትዮጵያዊያን የብኩላችሁን ድጋፍ እንድታደርጉ እንማጠናለልን፡፡

  በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ አለመግባባቶችን ወደእርቅና ሰላም ለማሸጋገር የሚቻለው በመደማመጥና በመከባበር ላይ የተመሠረተ ሲሆን ብቻነው፡፡ በመሆኑም ሁሉም ወገኖች በሆደ ሰፊነት መርህ የመነጋገር፣ የመደማመጥ፣ የመከባበር፣ ብሎም የመቀባበል ባህል በማሳደግ እርስበርሳችን ሰላም ለመፍጠር መትጋት አለብን፡፡እኛ የእምነት አባቶች ደግሞ ነቢያዊ ሃላፊነታችንን ለመወጣት የሰላምና የእርቅ መሣሪያ ለመሆን በየአካባቢያችንም ሆነ በአገር አቀፍ ደረጀ ድምፃችንን ከፍ አድርገን በማስማት የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን፤ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረው የሰው መብት እንዲከበር፤ ያለፍርሃት የጥፋት ኃይሎችን መገሠፅ ይጠበቅብናል፡፡የእምነት አባቶች የተጣሉትን በማስታረቅ የሰላም መሣሪያ የመሆን የሞራል ኃላፊነት፤ ከአምላክ የተሰጠን አደራም ስለሆነ የተለያዩ የሕብረተሰብ አካላትን፣ ማህበረሰቦችንም፣ የመንግስት ኣካላትንም፣ ያለምንም ወገናዊነት እና ፍርሃነት ተግሣፅ የሚገባውን በመገሠፅ፣ይቅርታ መጠየቅ ያለበትን እንድጠይቅ፣ ይቅርታ መሰጠት ያለበት እዲሰጥ ከሁሉም በላይ ደግሞ ቃሉም በዮሐንስ ወንጌል  እውነት ነፃ ያወጣችኋል። /ዮሐ8፡32/ እንደ ሚለው፣ እውነትን መሰረት ያደረገ ዕርቀ ሰላም እንድሰፍን የነቢይነት ኃላፊነታችንን መወጣት ይኖርብናል፡፡

  በአገራችን ያለፈው 2009 ዓ/ም ፈታኝ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡ አሁንም ቢሆን በ2010ዓ/ም የማህበረሰቡን አብሮነትና አንድነት በአደጋ ላይ እየጣሉ ነው፡፡በመሆኑም፡-

  1. < > የመንግስት አካላት በሙሉ፡- ሀገራዊ ቁስሎችን የማዳን፣ እርቅን የማውረድ ኃላፊነት የመጀመሪያው ባለቤት እንደመሆናችሁ በየደረጃው ያለው የመንግሥት መዋቅር ለሰላም ሥራ የበኩሉን ሚና እንዲጫዎትና ለዚህም አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርግ አደራ እንላለን፡፡በተለይ በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ በአገራችን አካባቢዎች እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች ለአገር ሕልውናና የሕዝቡ አንድነት በከፍተኛ አደጋ ላይ የሚጥል ስለሆነ ማንኛውንም ዓይነት ልዩነት ወደጎ ንበመተው ሕዝብንና አገርን ለማዳን ግንባር ቀደም ሚና መጫወት ይኖርባችኋል፡፡ የውስጥ ልዩነት እንኳን ቢኖራችሁ የግጭት መልክ ይዞ ወደ ሕዝብ እንዳይወርድ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳስባልን፡፡ ማንኛውንም ልዩነት በውይይትና በድርድር በመፍታት፣ የውይይት መድረክ እንድይዘጋ አስፈላጊውን መስዋዕት በመክፈል፣ አገርቷን ከውድቀት፣ ሕዝቡንም ከሞትና ስደት የመታደግ ከባድ ሞራላዊና መንግስታዊ ኃላፊነት አለባችሁ፡፡ ይህን ክፍተት በመጠቀም ቋንቋንና የዘር ሀረግን በመከተል ሕዝብን ከሕዝብ ጋር የሚያጋጩ የጥፋት ኃይሎች በሕዝብ ላይ የባሰ ትርምስና ጉስቁልና እንዳያስከትሉ ጥበብ የተሞላበት ለሕዝቡን ታሪካዊ አንድነት የመጠበቅ ኃላፊነት አለባችሁ፡፡< > ማእከላት፤ እና የአገራችን ምሁራን ወጣት ልጆቻን በሥነ ምግባር ታንጸው እንዲያድጉ የበክኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ እናሳስባለን።< > ክርስቲያናችን ካህናት ገዳምውያን/ያት፣ ካታኪስቶች፣ ምእመናን ሁላችሁ፣ እንደዚሁም በትምህርት ቤቶቻችን የምታስተምሩ አስተማሪዎችና በተቅዋሞቻችን የምትሠሩ በሙሉ የፍቅር፣የሰላም፣ የመቻቻልዬ﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽፣ተምሳሌት እንድትሆኑ አደራ እንላለን።< > ተቋማትና የኃይማኖት መሪዎች ፈጣሪያችን በሚያዘን መልኩ የሠላም የእርቅና የአንድነት መሣያዎች እንዲሆኑ እናሳስባን፡፡ ተከታዩቻቸውን ሁሉ በግልም በጋራም ለእርቅ ለሰላም ለአንድነት እንዲሰሩ እንዲያተጓቸው በእግዚአበሔር ስም እንጠይቃለን፡፡ የሃይማኖት መሪዎች ተመሪዎቻቸና መልእክቶቻቸው በሙሉ የሠላም የእርቅ የፍቅር እንዲሆኑና በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባርም እንዲውል መጣር ይኖርባቸዋል፡፡  < > የሀገር ሽማግለሌዎች፤ክቡራን ወላጆች ለትውልድ የሚተላለፉ በጎ እሴቶች ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው በአባቶችና በሀገር ወዳድ ሸማግሌዎች መሆኑን ተገንዝባችሁ ሁለ ሀገር ተረካቢ ለሆነው ወጣቱ ትውልድ ምክራችሁንና መልካም አርአያነታችሁን እንታበረክቱ አደራ እንላለን፡፡< > የሀገራችን ወጣቶች፣በሀገራችን ሰርታችሁ፣ ለኑሮ በቂየ ሆነውን ገቢ አግኝታችሁ፤ ቤተሰብ መስርታችሁ ክብር ያለው ሕይወት ለመኖር ያላችሁን ምኞትና ቁርጠኝነት ቤተክርስቲያን ትገነዘባለች፡፡ ይህንን ሊያሰናክሉ የሚችሉ ውጫዊ ፈተናዎችን አሸንፋችሁ ለነገው ሀገር የመረከብ ሃለፊነታችሁ እንድትበቁ ከመንግስት፣ ከሀገር ሽማግሌዎችና ከሌሎች መልካም ፊቃድ ካላቸው አካላት ጋር በመከባበርና በመደማመጥ ላይ በመመስረት እንድትወያዩ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡< > እናቶቻችንና እህቶቻችን በሙሉ፤ ለሰላም መስፈንና ለግጭቶች መፈታትና እልባት ማግኘት ያላችሁ ሚና ከሁሉም የላቀ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ሰለዚህ ቤተሰብን ያለአንዳች መድልዎ አንድ አድርጋችሁ እንደምትይዙ ሁሉ፣ ለሀገርም ጉዳይ የበኩላችሁን ሚና በአንድነት እንድትጫዎቱ አደራ እንላለን፡፡ 

    

   እግዚአብሔር ሀገራችንና ሕዝቦችዋን ይባርክ፡፡ አሜን

   ታኅሣሥ  12 2010 ..

   ጳጳሳት ማእከል፣ አዲስ አበባ

    

28/12/2017 10:09