2017-12-27 16:05:00

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የሰላምችን ምንጭ ነው


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን ለሚሰብሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በተለያዩ አርዕስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ምያደርጉ ይታወቃል። የዚሁ መርሃ ግብር አንዱ ክፍል በሆነው የዛሬው ቀን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮዋቸው ከዚህ ቀደም መስዋዕተ ቅዳሴን እና በመስዋዕተ ቅዳሴ ውስጥ የሚከናወኑ ትልቅ ትርጓሜ ያላቸውን የእምነታችን መገለጫ የሆኑ ምልክቶችን አንድ በአንድ በመጥቀስ በተከታታይ ማብራሪያ እየሰጡ እንደ ነበረ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በዛሬው እለት ግን የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ ክርስቲያኖች ዘንድ ባለፈው ሰኞ የተከበረውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በማስምልከት ይህንኑ የገና በዓል እና መንፈሳዊ እሴቶቹን የሚገልጽ አስተምህሮ ማድረጋቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህን አስተምህሮ ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት በጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ ያደረጉትን የጠቅላላ አስተምህሮ እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አረፈዳችሁ!

በአሁኑ ወቅት በእመንት እያከብርነው የምንገኘው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ምን ማለት እንደ ሆነ ዛሬው አስተምህሮ መናገር እፈልጋለሁ።

የገና ዛፍ በየቤታችን መሥራት፣ በተለይም ደግሞ በስርዓተ አምልኮዋችን ወቅት የተነበቡልን የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት፣ በዚሁ በገና ሰሞን የተዘመሩት ባሕላዊ የሆኑ ዝማሬዎች፣ ዛሬ የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ ልደት ዛሬ እንደ ተከሰተ እንዲሰማን በማድረግዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀን ተወልዶላችኋልና፤ እርሱም ጌታ ክርስቶስ ነው” (ሉቃስ 211) በማለት አክብረነዋል።

በጊዜያችን በተለይም በአውሮፓ የገና በዓል ትክክለኛ እሴቱ "በማዛባት" ላይ ይገኛል፣ ወይም ለመዛባት እየሞከረ ነው። ክርስትያኖችን ያልሆኑ ሰዎች፣ ነገር ግን ክርስቲያን ለመምሰል የምፈልጉና ብዙውን ጊዜ እምነታቸውን  የሚደብቁ ሰዎች ባሉበት ሥፍራ፣ ከዚሁ ታላቅ ከሆነ አመት በዓል የኢየሱስን መወለድ የምያመልክቱ ነገሮችን ሁሉ ለመሰረዝ ይፈልጋሉ።

ነገር ግን እውነታው የሚያሳየው ይህ ክስተት ብቻውን  እውነተኛ የገና በዓል ምን መሆኑን ያሳያል! ያለ ኢየሱስ ክርስቶስ ትክክለኛውን እና እውነተኛውን የገና በዓል ማክበር አይቻልም። ነገር ግን እርሱ በዓሉ መካከል በአጠቃላይ የበዕእሉ ንድፍ ሐሳቦች ውስጥ ማለትም በገና መብራቶች፣ በሙዝቃዎች፣ በተለያዩ የከባቢ በህሎች፣ ባሕላዊ የሆኑ ምግቦችን ጨምሮ በሁሉም የበዓሉ ሂደቶች ውስጥ ትክክለኛ የበዓል ሁኔታ ወይም ድባብ እንዲፈጠር አስተዋጾ ያደርጋሉ። ነገር ግን ከእነዚህ ነገሮች ውስጥ ኢየሱስን ነቅሰን ብናወጣ ግን የገና መብራት ይጠፋል፣ ይታዩ የነበሩ ነገሮች ሁሉ እንዳልነበሩ ይሆናሉ።

በቤተክርስቲያን አዋጅ መሰረት እንደ ወንጌል አብሳሪዎች (ሉቃ 2 9) እውነተኛውን ብርሃን ለመፈለግ እና ለማግኘትም ኢየሱስ በፈጠረልን አስገራሚ መንገድ በመጓዝ፣ በሚያስደንቅ አኩኻን ከአንድ ድሃ እና እንብዛም ከማትታወቅ ወጣት በእንስሳት ጋጣ ውስጥ የሚወለደው ልጅ፣ ከባለቤቷ ውጭ ማንም ሰው ያልረዳት ሴት፣ ይህ ሁኔታ በተከሰተበት ወቅት ዓለም ይህንን ጉዳይ አላወቀውም ነበር፣ ነገር ግን በሰማይ ያሉ መላእክት በደስታ ዘምረውለት ነበር። የእግዚአብሔር ልጅ ዛሬ ራሱን ለእኛ አሳልፎ የሚያቀርበው በዚሁ መልኩ ነው፣  በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ለነበሩ እና አንቀላፍተው ለነበሩ  የሰው ልጆች ከእግዚአብሔር የተሰጠ ፀጋ ነው (ኢሳያስ 9.1) ዛሬም በእኛ ዘመን እንኳን የሰው ልጅ ብዙውን ጊዜ ጨለማን ይመርጣል፣ የሚለውን እውነታ እውነተኛነቱን እያስመሰክርን እንገኛልን። ምክንያቱም ብርሃን እነዚያ በጨለማ የተዋጡ ድርጊቶቻችንን ሙሉ በሙሉ እንደ ሚያበራቸው እና በሕይወታችን የሚከሰቱ እነዚያ ሁሉ ድርጊቶች እና ሐሳቦች ህሊናችን መልሰን እንድንጎናጸፍ ወይም ህሊናችንን እንዲያነቃቃ ማድረግ እንደ ሚችል እያወቀን ዝም በማለታችን የተነሳ ነው። በዚህም ምክንያት በጨለማ ውስጥ መቆየት እና መጥፎ የሆኑ ልምዶቻችንን መቀበል እንመርጣለን።

ከዚህም ቡኋላ ከእግዚአብሔር በስጦታነት የሰጠን ኢየሱስ ክርስቶስን መቀበል ማለት ምን ማለት እንደሆነ ራሳችንን መጠየቅ እንችላለን። እሱ ራሱ እኛን በሕይወቱ እንዳስተማረን በዚሁ መንገድ ላይ ለሚመላለሱ ሰዎች በነጻ የተቀበልነውን ስጦታ በነጻ መስጠት ማለት ነው። ለዚህም ነው በክርስቶስ የልደት ቀን በሚከበርበት የገና ቀን ስጦታ የምንቀያየርበት በዚሁ ምክንያት ነው። የእኛ እውነተኛ ስጦታ ኢየሱስ ነው፣ እርሱ ለእኛ የተሰጠ ስጦታ በመሆኑ የተነሳ እኛም ራሳችንን ለሌሎች በስጦታነት ማቅረብ ይኖርብናል። ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ በመልእክቱ በጣም ውብ የሆኑ ቃላትን ተጠቅሞድነት የሚገኝበት የእግዚአብሔር ጸጋ ለሰዎች ሁሉ ተገልጦአልና፤ ይህም ጸጋ በኀጢአት መኖርንና ዓለማዊ ምኞትን ክደን፣ በአሁኑ ዘመን ራሳችንን በመግዛት በጽድቅ፣ በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት እንድንኖር ያስተምረናል” (ቲቶ 211-12) በማለት ይገልጸዋል። የእግዚአብሔር ፀጋ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት "ታይቷል" ይህም የእግዚአብሔር ልጅ ፊት የተገለጸው ድንግል ማርያም በዚህ ዓለም ውስጥ እንድ ሕፃን ልጅ ስለወለደችልን ነው፣ ነገር ግን ይህ ሕጻን "ከምድር" ያልመጣ ነገር ግን "ከሰማይ" እና ከእግዚአብሔር "የመጣ" ነው። በዚህ መንገድ ቃል ሥጋ በመልበሱ የተነሳ፣ እግዚኣብሔር በፍቅር ላይ የተመሠረተ የአዲስ የሕይወት መንገድን ከፍቶልናል።

በመጨረሻም አንድ በጣም ጠቃሚ የሆነ ገጽታን እንመልከት፡ በገና በዓል በኃያልን ክንድ ሥር የነበረው ዓለማችን እንዴት በእግዚኣብሔር እንደ ተጎበኜ የሚተርክ የሰው ልጅ ታሪክን እንመለከታለን። እናም እግዚአብሔር በማኅበረሰቡ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞችን ለሚጎበኙ ሰዎች የእርሱን ስጦታዎች የመጀመሪያዎቹ ተቀባዮች ናቸው፣ ይህም ስጦታ በኢየሱስ አማካይነት የተገኘው የድኽንነት ስጦታ ነው። በዚህም ትንንሽ ከሆኑ እና ከተናቁ ሰዎች ጋር ኢየሱስ በጊዜ ሂደት የሚቀጥል እና ለወደፊት የተሻለ ተስፋን የሚያጎለብት ጓደኝነትን ይመሰርታል። በቤተልሔም እረኞች የተወከሉት እነዚህ ሰዎች "ታላቅ ብርሀን ተገለጠላቸው" (ሉቃ 2 9-12) በቀጥታ ወደ ኢየሱስ አመራቸው። አምላክ ከእነርሱ ጋር በመሆን በሁሉም ጊዜያት፣ ማንም ሰው ሊቀበላቸው የማይፈልጋቸውን ሰዎች፣ የተበደሉ ሰዎችን እና የተቸገሩ ሰዎችን ሁሉ ነጻ በማውጣት አዲስ የሆነ ዓለም መገንባት ይፈልጋል።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እኅቶቼ፣ በዚህ ዘመን ውስጥ ይህንን የኢየሱስ ጸጋ ለመቀበል አዕምሮአችንን እና ልቦናችንን እንክፈትለት። ኢየሱስ ለእኛ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ጸጋ ነው። እኛም እርሱን ተቀበልነው፣ ለሌሎች በስጦታነት ማቅረብ እንችላለን፣ ብዚህም ሁኔታ ኢየሱስ በእያንዳንዳችን ሕይወት ዳግም ይወለዳል፣ በእኛም በኩል ለታናናሾች እና ለተገለሉት ሰዎች የመዳን ስጦታ በመሆን ይቀጥላል።

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.