Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ስብከቶች

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ ክርስቲያኖች ዘንድ በተከበረው የገና በዓል ወቅት ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት መልእክት

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ ክርስቲያኖች ዘንድ የገና በዓል በተከበረበት ወቅት - AFP

27/12/2017 15:02

በታኅሳስ 16/2010 ዓ.ም. የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ ክርስቲያኖች ዘንድ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በደማቅ ሁኔታ ተክብሮ ማለፉን መዘገባችን ያታወሳል። በእለቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በርካታ ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተግኙበት በእርሳቸው መሪነት መሳውዕተ ቅዳሴን አሳርገዋል። በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ባሰሙት ስብከት ማሪያም “የበኵር ልጇ የሆነውን ወንድ ልጅ ወለደች፤ በጨርቅም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማረፊያ ቦታ ስላላገኙ በግርግም አስተኛችው” የሚለውን በሉቃስ ወንጌል በ2:7 ላይ የተጠቀሰውን በማስታወስ ስብከታቸውን ጀመረው ንጉስ ሄሮደስ የሕዝብ ቆጠራ እንዲደረግ አዋጅ ባወጀበት ወቅት  ማሪያም እና ዮሴፍ ለመቆጠር ወድ ሀገራቸውን፣ ንብረታቸውን ቤታቸውን ሳይቀር ጥለው ወደ ቤተልሔም እንዴሄዱ አስታውሰው በዚያ የገጠማቸው ሁኔታ ግን በጣም ያልጠበቁት እና ግራ የሚያጋባ እንደ ነበረ አስታውሰዋል። ምክንያቱም ለእነርሱ የሚሆን የማረፊያ ቦታ በቤተልሔም ስላልነበረ መሆኑን አስታውሰው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የተጸነሰው የእግዚኣብሔር ልጅ በከብቶች ግርግም ውስጥ ለመወለድ መገደዱን ቅዱስነታቸው ገልጸዋል። ዛሬም ቢሆን ስልጣንን በመሻት የሕዝቡን ሀብት ብቻቸውን ለመሰብሰበ ዓላማ ባላቸው የዛሬው ዘመን ሄሮድሶች አማካይነት ብዙ ሰዎች ለስደት እንደ ሚዳረጉ ገልጸው ልክ ማሪያም እና ዮሴፍ በቤተልሔም የእንግዳ ማረፊያ ቦታ አጥተው ተቸግረው እንደ ነበረ፣ የበኩር ልጃቸውንም በበረት ውስጥ ለመውለድ ተገደው እንደ ነበረ ሁሉ በተለያዩ አስገዳጅ የሆኑ ሁኔታዎች አማክይነት ሀገር፣ ዘመድ አዝማዶቻቸው እና ቤታቸውን ጥለው ወደ ተለያዩ ሀገራት የሚሰደዱ ሰዎችን መጠጊያ አጥተው እንዳይግላቱ በተቻለን የበኩላችንን መልካም አስተዋጾ ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል።

የዚህን ዝግጅት  ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በመቀጠልም በዚያ ምሽት በቤተልሔም ከተማ በከብቶች ግርግም ውስጥ የተወልደው ክርስቶስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰበከው ለእረኞች እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ገለዋል። እነዚህ እረኞች በከተማው ጎዳናዎች ላይ የሚኖሩ ሰዎች ነበሩ፣  ይህ የምሥራች ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰበከው ደግሞ ለእረኞች ነው።

በሥራቸው ባሕሪ ምክንያት ከኅብረተሰቡ ውጪ ለመኖር ተገደው ነበር።  የኑሮ ሁኔታቸው እና የሚኖሩበት ስፍራ ሳይቀር ከሌላው የማኅብረሰብ ክፍል አንጻር ዝቅ ያለ እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው አስታውሰው በዚህም ምክንያት እንደ ርኩስ ተደርገው ይቆጠሩ ነበር። ቆዳቸው፣ ልብሳቸው፣ ሽታቸውም የአነጋገራቸውም ሁኔታን መነሻ በማድረግ ኅብረተሰቡ ያገለላቸው ሰዎች ነበሩ። በአማኞች መካከል የሚገኙ አረማዊያን፣ በቅዱስና መካከል የሚኖሩ ኃጢአን፣ በዜጎች መካከል የሚኖሩ መጤዎች ተደርገው ይቆጠሩም ነበር። በአንጽሩ ግን አረማዊነት፣ ኃጢያተኛነት፣ እና የመጤነት ስሜት ለሚሰማቸው ለእነዚሁ እረኞች መልአኩ ግን እንዲህ አላቸው፤ “አትፍሩ፤ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች አምጥቼላችኋለሁና።  ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀን ተወልዶላችኋልና፤ እርሱም ጌታ ክርስቶስ ነው” በማለት ለመጀመሪያ ጊዜ አበሰራቸው። ስለዚህም ክርስቶስ በቅዳሚነት የተወለደው ለተናቁ፣ ለታሰሩ በእየጎዳናው ማረፊያ አጥተው ለሚሰቃዩ ሰዎች እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው አበክረው ገልጸዋል። እኛም ክርስቲያኖች ነን የምንል ሰዎች ሁሉ ይህ በመኅበርሰብ ውስጥ የሚፈጠር ልዩነት እንዲፈታ የበኩላችንን ጥረት በማድረግ ማኅበራዊ ፍትህ ይሰፍን ዘንድ የበኩላችንን አስተዋጾ ማድረግ ይጠበቅብናል በማለት ጨምረው አሳስበዋል።

በማስከተልም በላቲን ቋንቋ Uribi et Orbis በአማሪኛው ሲተረጎም ለከተማው (ሮም) እና ለመላው ዓለም የሚል ትርጉሜ አለው፣ በተለይም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ቀን እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በተነሳበት በፋሲካ ቀናት እንዲሁም በአንድ አንድ ታላላላቅ  መንፈሳዊ በዓላት በሚከበሩበት ወቅት ለሮም እና ለመላው ዓለም የእንኳን አደረሳችሁ እና የቡራኬ መልእክታቸውን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ  እንደ ሚሰጡ ይታወቃል። በታኅሳስ 16/2010 ዓ.ም. ረፋዱ ላይ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች ባስተላለፉት የurbi et Orbis ለሮም እና ለዓለም በተሰኘው መልእክታቸው እንደ ገለጹት የብርሃን እና የሰላም አምላክ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደው በኢየሩሳሌም በምትገኘው ቤተልሔም በሚባል ስፍራ እንደ ሆነ አስታውሰው ዛሬ ግን ያ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት የብርሃን እና የሰለም ስፍራ በሁከት እየታመሰ መገኘቱ እንደ ሚያሳዝናቸው ገለጸው፣ ይህ ሁከት እና ብጥብጥ ተወግዶ ሰላም ይሰፍን ዘንድ የሚመለከታቸው አካላት የበኩላቸውን አስተዋጾ ማድረግ እንደ ሚገባቸው አብክረው ገለጸዋል። በተለይም ደግም ምንም የማያውቁ ንጹኃን የሆኑ ሕጻናትን ከአደጋ መጥበቅ እንደ ሚገባ አስታውሰው በዚያው ማለትም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት ስፍራ እና በዓለም ዙሪያ ሳይቀር ለሕጻናት እንክብካቤ ይደረግ ዘንድ ቅዱስነታቸው አበክረው አሳስበዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ባለፈው ሰኞ በደማቅ መንፈሳዊ ስነስርዓት በተከበረው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ላይ በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ያደረጉትን ስብከት ጠቅለል ባለ ሁኔታ እና ከእዚያም በመቀጠል ሰኞ ኣለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ኣን ኣየሀገር ጎብኚዎች ባስተላለፉት የUrbi et Orbis (ለሮም እና ለዓልም ሁሉ) በተሰኘው መልእክታቸውን ነበር ጠቅለል ባለ መልኩ ያቀርብንላችሁ። አብራችሁን በመሆን ስለታደመችሁ ከልብ እናመስገናችኃለን።

27/12/2017 15:02