Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ ሳይንስና ትምህርት

በመቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ ጽ/ቤት እና ሳሊዚያን ማኅበር መካከል የተደረገው ስምምነት

በመቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ ጽ/ቤት እና ሳሊዚያን ማኅበር መካከል የተደረገው ስምምነት - RV

27/12/2017 13:04

ዋናው ትኵረቱ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ የበላይ መዋቅራዊ ኅዳሴ እንዲከናወን የሰጡት ውሳኔ እና በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን እየተከናወነ ያለው ኅዳሴ ላይ በማነጣጠር፡ ከዚህ ቀደም የቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙኃን ተንከባካቢ ጽ/ቤት ከኢየሱሳውያን ማኅበር ጋር በልኡካነ ወንጌላዊነት ዓይነተኛ መለያው ኅልው የሚያደርገው በመረጃ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ ተባብሮ መሥራት እንዲኖር ለማድረግ የተደረሰው የጋራው ስምምነት ተከትሎ ይኸው ተመሳሳይ ስምምነትም ከቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘሳለስ ማኅበር ጋር መከናወኑ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ያመለክታል።

ባለፉት ቀናት የቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ የሚከታተለው ጽ/ቤት (የማስታወቂያ እን የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ ጽ/ቤት) ከሳሊዚያን ማኅበር ጋር ያከናወነው ስምምነት በዚህ የቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት አማካኝነት የዶን ቦስኮ መንፈሳዊ ዓላማው በቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ አስተዋጽኦ እንዲኖረው ማድረግ የሚል ሲሆን፡ የተደረሰው የጋራው ስምምነትም ሦስት ዓመታዊ መሆኑ የቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ ጽ/ቤት ያሰራጨው መግለጫ የጠቀሰው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ዜና ምንጭ አክሎ የስምምነቱን ሰነድ የፈረሙት የቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ ጽ/ቤት ኅየንተ የኔታ ዳሪዮ ኤድዋርዶ ቪጋኖ እና የቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘሳለስ ማኅበር አቢይ አለቃ አባ አንገል ፈርናንደዝ አርቲመ መሆናቸው ይጠቁማል።

27/12/2017 13:04