2017-12-23 14:11:00

ቤተክርስቲያን እየሩሳሌም የእስራኤልና የፍልስጤም የጋራ ግዛት ናት የሚለው አቋም እንዳላት ተገለጸ።


በቅርቡ የአሜርካው ርዕሰ ብሔር የሆኑት ዶናልድ ትራንፕ እየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ ብቻ ናት፣ በማለት በተናጥል መወሰናቸውና ይህንንም ውሳኔያቸውን ለማጽናት በአሁኑ ወቅት በቴላቪቭ የሚገኘውን የአሜርካ ኤንባሲ ወደ እየሩሳሌም ለማዛወር ቅድመ ዝግጅት እንዲደረግ ማዘዛቸው ይታወቃል። ይህም ውሳኔ ከዚህ በፊት የነበረውን ዓለማቀፋዊ የሆነ የመግባቢያ ሰነድ ይህም ማለት “እየሩሳሌም የአይሁዶች እና የፍልስጤም” ግዛት ናት የሚለው ነው። ይህም ለዘመናት የመካከለኛው ምስራቅ የግጭት መንስሔ የሆነውን ጉዳይ በጣም የቆዬ እና አከራካሪ የሆነ ጉዳይ በመሆን የግጭቶች እና የጦርነቶች መንስሄ በመሆንም ጭምር የብዙ ሰዎችን ነብስ የቀጠፈ  ጦርነቶች የተካሄዱበት፣ ንብረት የወደመበት፣ በዓለማቀፍ ደረጃም ከፍተኛ የሆነ ፖሌቲካዊ ክርክር የተደረገበት እና እየተደረገት የሚገኝ፣ ብዙዎቹን ሀገራትን ያቃረን ያወዛገበ እና እያወዛገበ የሚገኝ ጉዳይ መሆኑም ያታወቃል። ይህም የሆነበት ምክንያት በእየሩሳሌም አብራሃማዊ መሰረት ያላቸው ሦስት ዋና ዋና የሆኑ የዓለማችን የሐይማኖት ተቋማት ስር መሰረታቸው የሚጀምርበት ቦታ በመሆኑ የተነሳ ነው። እነዚህም የክርስትና፣ የአይሁድ እና የእስልምና እምነቶች ናቸው፣ ይነስም ይብዛም ሦስቱም የሐይማኖት ተቋማት እየሩሳሌም የእምነታቸው መሰረት የሆነች ከተማ እንደ ሆነች በማመን በዚያም እጅግ ግዙፍ እና ታሪካዊ የሆኑ የእመንት ተቋማትን ገንብተው እንደ ሚገኙም ያታወቅል። ይህ አከራካሪ እና በጣም ጥንቃቄ የሚፈልግ ጉዳይ ብዙን ጊዜ የዓለማችን የግጭቶች መንስሔ በመሆኑ የተነሳ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1947 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይህንን ግጭት ያስቆማል በሚል ሕሳቤ 55% የእየሩሳሌም ግዛት የአይሁዳዊያን የተቀረው በምስርቅ በኩል የሚገኘው እና 45% የሚወክለው ግዛት ደግሞ የፍልስጤም እንዲሆን ተወስኖ እንደ ነበረም አይዘነጋም።

የዚህን ዝግጅት ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በተለይም ደግሞ በእየሩሳሌም ከተማ ውስጥ በጥንታዊነት በሚታወቀው ስፍራ ላይ የሚገኘው እና በተባበሩት መንግስታት የባህልና የቅርስ ተቋም በሆነ UNESCO ተመዝግቦ የሚገኘው እና 35 ሄክታር ያህል ስፋት ያለው ስፍራ ይገኝበታል፣ በዚሁ ስፍራ የእመነት አባት በመባል የሚታወቀው አብራሃም የእመነታችን ስር መስረት ነው የሚሉ የክርስትና፣ የአይሁድ እና የእስልምና እምነት ተከታዮች ቅዱስት ሥፍራዎች ይገኛሉ። በእንግልዜኛው “dome of the Rock” በማባል  የሚታወቀው የአይሁድ ቤተ መቅደስ የሚገኝበት  እንዲሁም አል አክሳ በመባል የሚታወቅ መስጊድ የሚገኝበት ስፍራ ነው፣ ከዚያም ባሻገር የተለያዩ የክርስትና እምነት ማካሄጃ ቅዱስን የሆኑ ስፍራዎችንም አቅፎ የያዘ ስፍራ ነው።

በዚሁ ምክንያት ነው እንግዲህ እየሩስላኤም አይሁድ እና ፍልስጤም ሁለቱ ሀገራት በጋር የሚያስተድድሩዋት ከተማ እንድትሆን የዓለም ማኅብረሰብ የወሰነውም በዚሁ ምክንያት ነው። ይህም ነባራዊ ሁኔታ ለዘመናት ተጠብቆ የቆዬ እና እስራኤል እና ፍልስጤም ለሚያደርጉት ፍጥጫ በመፍትሄነት የተቀመጠ መርዕ እንደ ሆነም ያታወቃል።

በቅርቡ የአሜርካው ርዕሰ ብሔር የሆኑት ዶናልድ ትራንፕ እየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ ብቻ ናት፣ በማለት መወሰናቸው ውዝግብ አስነስቶ የነበረ ሲሆን ይህንንም ጉዳይ  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውሳኔ እዲሰጥበት በተለያዩ ሀገራት ጥሪ በመቅረቡ የተነሳ በቅርቡ የተባበሩት መንግሥታት ባደርገው ስብሰባ 158 ሀገራት ይህንን ውሳኔ ተገቢ አይደለም በማለት የተቃወሙት ሲሆን 35 ሀገራት የታቅቦ ድምጽ ቀሪዎቹ 9 ሀገራት ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ ይህንን ውሳኔ ተቃውመውታል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ቀደም ባሉት አመታትም ሳይቀር እየሩሳሌም የሁለቱ ሀገራት ማለትም የእስራኤል እና የፍልስጤም የጋራ ግዛት ናት የሚለውን የዓለማቀፉ ማኅበረሰብ የተቀበለውን የውሳኔ ሐሳብ ቫቲካን የምትቀበለውና የምታንጸባርቀው እውነታ እንደ ሆነ መግለጻቸው የሚታወቅ ሲሆን እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሰኔ 8/2014 ዓ.ም የእስራኤል ፕሬዝዳንት የሆኑትን ሲሞን ፔረዝን እና የፍልስጤም ጠቅላይ ሚንስቴር የሆኑት ማሙድ አባስን ወደ ቫቲካን ጋብዘው ሁለቱም ሀግራት ግጭቶችን አስወግደው ለሕዝቦቻቸው እድገት እንዲሰሩ ጥሪ ማቅረባቸው ያታወሳል።

ይህ በቅርቡ የተነሳው ውዝግብ በሰላም ይፈታ ዘንድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ጥሪ ባለፈው ማክሰኞ እለት የዮርዳኖሱ ንግሥ አብደላ 2ኛ ጋር ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በተወያዩበት ወቅት ቫቲካን የዓለማቀፍ ማሕበርሰቡ የሚቀበለውን እየሩስሌም የፍልስጤም እና የአይሁድ የጋራ ግዛት ናት የሚለውን መርዕ እንደ ምትቀበል እና በአከባቢው ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ ከተፈለገ ይህንን እውነታ መቀበል እንደ ሚገባ አስረግጠው መናግራቸውን መዘገባችን ያታወሳል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በቅርቡ በእዚሁ አንገብጋቢ ጉዳይ ላይ በተሰበሰበበት ውቅት የቫቲካን ተወካይ የቅድስት መነበርን ሐሳብ አንጸባርቀው እንደ ነበረ ከቅድስት መነበር የሕትመት እና የዜና ክፍል የደረሰን ዜና የገለጸ ሲሆን በቅርቡ የአሜርካው ርዕሰ ብሔር የሆኑት ዶናልድ ትራንፕ እየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ ብቻ ናት በማለት ያቀረቡትን ሐሳብ በአከባቢው ሁከት እና ግጭት የሚፈጥር ተግባር በመሆኑ የተንሳ ቫቲካን ይህንን ሐሳብ በመቃውም በተቃራኒው እየሩሳሌም የእስራኤልና የፍልስጤም የጋራ ግዛት ናት የሚለውን አቋም ከዓለማቀፉ ማሕበረሰብ ጋር በመሆን ማስተጋባታቸውን ከቅድስት መነበር የህትመት እና የዜና ተቋም ከደረሰን ዜና ለመረዳት ተችሉዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.