2017-12-23 13:59:00

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ በስብከታቸው "ደስታ በዋነኛነት የሚመነጨው ከሦስት ነገሮች እንደ ሆነ" ገለጹ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ጥዋት በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት በትላንታንው እለት ማለትም በታኅሳስ 12/2010 ዓ.ም. ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ክርስቲያኖች በፈገግታ የተሞላ ፊት እና ይቅርታ የሚያደርግ ልብ ሊኖራቸው ይገባል ካሉ ቡኃላ በተጨማሪም ክርስቲያኖች ነቅተው መጠበቅ ይኖርባቸዋል ብለዋል። ቅዱስነታቸው በእለቱ ያደርጉት ስብከት በኃጢያት ርስዔት ምክንያት እና ጌታን በምንቀርብበት ወቅት በሚገኘውን ደስታ ዙሪያ ላይ ያተኮረ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን በተለይም ደግሞ በእለቱ ከሉቃስ ወንጌል 1:39-45 ላይ በተጠቀሰው ቃል ላይ ተመርኩዘው እንደ ገለጹት ማሪያም ኤልሳቤጥን ለመጎብኘት በሄደችበት ወቅት ማሪያም ኤልሳቤጥ በደስታ መሞላቱዋን ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

የዚህን ዜና ሙሉ ዝርዝር ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ደስታ በዋነኛነት የሚመነጨው ከሦስት ነገሮች እንደ ሆነ በመግልጸ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በመጀመሪያ ደረጃ እና በዋነኝነት ደስታ የሚመነጨው ከይቅርታ እንደ ሆነ ገለጸው “ጌታ ኃጢኣትህን ይቅር ብሎልኃል” መባል ከፍተኛ የሆነ ደስታን የሚፈጥር ነገር መሆኑንም ቅዱስነታቸው ገለጸዋል። ስለዚህም ሁላችንም ለኃጢኣታችን ስርዔት በማግኘታችን የተነሳ  ለብ ያለ ስሜታችንን አስወግደን ደስታኞች ልንሆን ያስፈልጋል ካሉ ቡኃላ ይህም “የክርስቲያኖች የደስታ ምንጭ ነው’’ ብለዋል። እስቲ የእስር ቅጣቱ የተቃለለትን አንድ እስረኛ ወይም አንድ ከበሽታው የተፈወሰ ሰው ያላቸውን ደስታ እስቲ ለፍታ አስቡት በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ስለዚህም እኛ ኢየሱስ ስላመጣው መቤዠት ማውቅ በጣም አስፈላጊ ነው ብለዋል።

አንድ በእግዚኣብሔር የማያምን ፈላስፋ ክርስቲያኖችን በመንቀፍ “ክርስቲያኖች አንድ አዳኝ አለን ብለው ያምናሉ፣ እኔ በዚህ አዳኝ በተባለው ሰው የማምነው ግን ክርስቲያኖች ነን የሚሉ ሰዎች መዳናቸውን በሚገባ የሚገል ነገር በፊታቸው ገጽታ ላይ ሲታይ ብቻ ነው፣ ማዳናቸውንም የሚገልስ ደስታ በፊታቸው ላይ ሲታይ ብቻ ነው” ብሎ መናጉርን አስታውሳለሁ። ነገር ግን አንተ /ወይም አንቺ በሐዘን ድባብ የተሞላ ፊት ካለህ ወይም ካለሽ አንተ/አንቺ መዳንሽን እንዴት ማመን ይችላሉ፣ ኃጢኣትህ/ሺ መሰረዩንስ እንዴት ሊያምኑ ይችላሉ? ይህም የመጀመሪያው እና ዋንኛው ነጥብ ነው፣ እያንዳንዳችን ይቅርታ ደርጎልናል ኃጢኣታችንም ተሰሪዮልናል ይህም የዛሬውም ስርዓተ አምልኮ ዋንኛው ምልእክት ነው ብለዋል።

“እግዚኣብሔር የይቅርታ አምላክ ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንን እግዚኣብሔር የሚሰጠንን ይቅርታ ተቀብለን ወደ ፊት በደስታ መጓዝ ይኖርብናል ካሉ ቡኃላ ምክንያቱም ደካሞች በመሆናችን የተነሳ እያንዳንዳችን የምንሰራቸውን ኃጢያቶች ሁል ጌታ ይቅር እንደ ሚለን ልናምን ይገባናል ብለዋል።

“ሁል ጊዜም ቢሆን ጌታ ከእኛ ጋር እንደ ሚጓዝ ማመን ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ ደስተኛ እንድንሆን የሚያደርገን ጉዳይ መሆኑን በመጥቀስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በድክመታችን፣ በሚስኪንነታችን፣ በመከራችን በደስታችንም ውስጥ ሳይቀር በሁለነተናችን ጌታ ከእኛ ጋር በመሆን እንደ ሚጓዝ ገልጸው በዛሬው እለት ውሎዋችን ጌታ ከጎናችን እንደ ሆነ ማስተዋል ይኖርብናል ብለው፣ እግዚኣብሔር ከእኛ ጋር እንደ ሚጓዝ ማሰብ ደግሞ ደስታን ከሚፍጥሩብን ነገሮች አንዱ እና ዋነኛው ነው ብለዋል።

በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ ለፍርሃት እጃችንን መስጠት ወይም መብረክረክ የለብንም የሚለው አቋም የደስታችን ምንጭ ሊሆን ይገባል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ ይሚከተለውን ብለዋል፡

ሁል ጊዜ ምጥፎ የሆኑ ነገሮች መልካም የሆኑትን ነገሮች ያሸንፋሉ የሚል አስተሳስብ ለክርስቲያኖች ጠቃሚ የሆነ ሐሳብ አይደለም፣ የእዚህ ዓይነት ሐሳብ ያለው ሰው ኃጢያቱ እንደ ተሰረየለት የማያውቅ ሰው ብቻ ነው፣ በትጨማሪም ይህ ሐሳብ የሚመነጨው እግዚኣብሔር መኃሪ እንደ ሆነ ካማያውቅ ወይም ይህ ስሜት ከማይሰማው ሰው ብቻ ነው። ዛሬ የተነበበል ቅዱስ ወንጌል፣ (ሉቃስ 139-45) ውስጥ የዚህ ዓይነቱ ደስታ ምን ማለት እንደ ሆነ ማየት ይቻላል፣ማርያምም በዚያው ሰሞን በፍጥነት ተነሥታ ወደ ደጋው አገር፣ ወደ አንድ የይሁዳ ከተማ ሄደችበማለት ይናገራል፣ ደስታ ሁል ጊዜም ቢሆን በፍጥነት እንድንጓዝ ያደርገናል፣ ምክንያቱም በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የሚገኝ ጸጋ ቀስ እያሉ ማዝገምን አያውቅም እና ነው፣ መንፈስ ቅዱስ ሁልጊዜም ቢሆን በፍጥነት እንድንጓዝ ያደርገናል፣ ልክ ንፋስ አንድ ጀልባን ወደ ፊት በመግፋት እንድጓዝ እንደ ሚያደርግ ሁሉ መንፈስ ቅዱስም እኛ ወደ ፊት በፍጥነት እንድንጓዝ ይገፋናል ብለዋል።

ኤልሳቤጥም የማርያምን የሰላምታ ቃል በሰማች ጊዜ፣ በማሕጸኑዋ የነበረ ጽንስ በደስታ እንደ ዘለለ በስብከታቸው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል፥

ቤተክርስቲያን ለእኛ ሁላችን የምታስተላልፈው መልእክት ይህ ነው እባካችሁን እኛ የተጠራነው ደስተኛ የሆንን ክርስቲያኖች እንደ ሆነ አትዘንጉ፣ ያለንን ሁሉ አቅም ኣና ጉልበት ተጠቅመን መዳንችንን ማሳየት እና ጌታ ሁላችንን እንደ ማረን ማሳየት ይኖርብናል። ምን አልባት በኃጢኣት ውስጥ ተነሸራተን በምንዝፈቅበት ወቅትም ሳይቀር እርሱ ኃጢኣታችንን ሁሉ ይቅር እንደ ሚል ማመን ይገባናል ምክንያቱም እርሱ የይቅርታ አማልክ ነውና፣ ሁልጊዜም በመካከላችን ሆነ ይጓዛል እና እርሱ በፍጹም እንድንወድቅ አይፈልግም እና ነገር ግን እጁን ዘርጎት ሊያድነን ሁሌም ቢሆን እንደ ሚመጣ ማመን ይኖርብናል። የዛሬው የእግዚኣብሔር ቃል የሚያስተምረንም ይህንኑ ነው፣ በወንጌል ውስጥ ኢየሱስ በሽተኞችን ተነስ እና ተራመድ ሲል ሰምተናል፣ እነርሱም በደስታ ሲፈነጩም ሰምተናል፣ ከልብ የመነጨ የምስጋና መዝሙር ለእርሱም ሲያቀርቡ በወብጌል ውስጥ መጠቀሱን እናውቃለን። ስለዚህም ደስተች ለመሆን እንሞክር ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.