Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ንግግሮች

ር. ሊ. ጳ. ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅድስት መነበር የመማክርት አባላት እና የቅዱስና ማሕበራት ያስተለለፉት መልእክት

ቅዱስነታቸው በቫቲካን የቅድስት መንበር የመማክርት አባላት እና ከቅዱሳን ማሕበራት ተወካዮች ጋር በቫቲካን ተገናኝተው በነበረበት ወቅት - AP

23/12/2017 15:56

­­­­ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በትኃሳስ 12/2010 ዓ.ም. (ከcuria Romana) በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም በቅድስት መነበር ሥር በመሆን ዓለማቀፋዊቷ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መዋቀራዊ የሆነ አስራሩዋን የተቀናጀ አደረጃጀታዊ ስርዓቱን እና ደንቡን በጠበቀ መልኩ እንዲጓዝ መምሪያ የሚሰጡ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የመማክርት ጉባሄ አባላት እና የቅዱስት ማሕበራት ተወካዮችን በታኅሳስ 12/2010 ዓ.ም. በቫቲካን መገናኘታቸው ያስተለለፉትን መልእክት እንደ ሚከተለው እናቀርበዋለን።

የትወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ

የገና በዓል የሰው በኃጢያት እና በለመታዘዙ ምክንያት አጥቶት የነበረውን የልጅነት መብት መልሶ እንዲጎናጸፍ ለማድረግ ስጋ ለብሶ ሰው የሆነው የእግዚኣብሔር ልጅ የሚከበርበት የእምነት በዓል ነው። የገና በዓል በልባችን ውስጥ የሚከበር እኛን ለማዳን ሲል በበረት የተወለደው የእግዚኣብሔር ልጅ የምንቀበልበት በዓል ሲሆን ነብሳችን ለእግዚኣብሔር እንድትገዛ በማደረግ በምስኪንነታችን ውስጥም ሳይቀር ተስፋ ፍቅር እና እምነት እንዲ ያብብ የምናደርገበት በዓል ነው።

ዛሬ እዚህ የተገናኘነው የገናን በዓል አስመልክተን (ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር የገና በዓል በመጭው ሰኞ ይከበራል) እንኳን አደረሳችሁ ለመባባል እና መልካሙን ሁሉ ለመመኘት እንደ ሆነ የሚታወቅ ሲሆን በዚህም የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቴ በቫቲካን የሚሰሩ የተለያዩ ኃልፊዎችን፣ ጳጳሳትን እንዲሁም ሁሉንም በዚህ በቅድስት መነበር መዋቅር ሥር የሚሰሩ ሰዎችን ሁሉ እንኳን ለገና በዓል እና ለአዲስ ዓመት (እንደ አአአ ከ10 ቀናት ቡኃላ የሚከበረውን የምህራባዊያን አዲስ አመት ማለታቸው ነው) አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ። ይህ መጪው የገና በዓል ብኩንነትን፣ ሐሰትን፣ ክፉ የሆኑ ነገሮችን እና ግዴለሽነትን አውልቀን ለመጣል ኣንድንችል ዓይናችን የሚከፈትበት፣ በአንጻሩ ደግሞ በጣም አስፈላጊ እና መሰረታዊ ለሆኑ ነገሮች ትኩረት የምንሰጥበት፣ እውነት የምንናገርበት፣ መልካም መልካም የሆኑ ነገሮችን በሐቀኝነት መንፈስ በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ፣ በድጋሚ መልካ የገና በዓል ይሁንላችሁ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ፣ በቅድስት መንበር ሥር በሚገኙ ሐዋርያዊ ተቋማት ውስጥ የሚታየውን የሥራ ቅጥር አለመስተካከልን ለመዋጋት ህብረት እና ቅን አገልግሎት እንደሚያስፈልግ ለቅድስት መንበር የመማክርት ጉባኤ አባላት አስገነዘቡ።

የብርሃነ ልደቱን በዓል ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ ንግግራቸው፣ ብርሃነ ልደት የእምነታችን በዓል ነው፣ ስለዚህ ዓይኖቻችንን ከፍተን ሃሰተኛ የሆኑ ነገሮችን በመመልከት፣ መልካም እና የሚጠቅመንን እውነተኛ መንገድን መከተል ያስፈልጋል ብለዋል።

ይህ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት አስተንትኖ፣ ባሁኑ ወቅት በቅድስት መንበር ሥር በተካተቱ መሥሪያ ቤቶች መካከል በመካሄድ ላይ ያለዉን የተሃድሶ ሂደት ያማከለ እንደሆነም ታውቋል።

የቅድስት መንበር ረጅም ታሪክ ያለው ጥንታዊ ሐዋርያዊ ተቋም እንደመሆኑ መጠን፣ የሚፈለገውን ተሃድሶ ለማምጣት ትእግስትን፣ ብልሃትን እና ጥንቃቄን እንደሚያሻ ገልጸዋል። በተጨማሪም ተቋሙ የተለያዩ ባሕሎች፣ ቋንቋ እና አስተሳሰብ ያላቸውን ሰዎች የያዘ በመሆኑ ጥንቃቄን ያስፈልገዋል ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በማከልም፣ የቅድስት መንበር፣ የሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ አገልግሎትን ያማከለ፣ በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት የበላይነት የሚመራና እና የቅዱስ ወንጌልን መልካም ዜና ማብሰር ቀዳሚ ዓላማ ያደረገ ተቋም እንደሆነም አስረድተው፣ ይህ ባይሆን ኖሮ ጠንካራ መሰረት አይኖረውም ነበር ብለዋል።

ይህን መሠረትዊ የሆነ ሐዋርያዊ አገልግሎት በማስመልከት፣ የቤተክርስቲያኒቱን ሐዋርያዊ መግለጫ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው፣ የስሜት ሕዋሳቶቻችን ከተቀረው የአካል ክፍሎቻችን ጋር ግንኙነት እንዲኖረን የሚያደርጉ ቀዳሚ መልዕክተኞች እንደሆኑ ሁሉ አንድ ዲያቆንም ለጳጳሱ፣ በቤተክርስቲያን ዉስጥ የሚከናወነውን ሁሉ ተከታትሎ የሚያሳውቅ የቅርብ አገልጋይና መልእክተኛ እንደሆነ አስታውሰዋል።

በሠራተኞች መካከል ይህን የመሰለ መልካም ግንኙነትና የአገልግሎት ቅንነት ካለ፣ በቤተክርስቲያን ተቋሞችና እንዲሁም በሠራተኞቿ መካከል ሊከሰቱ የሚችሉ ጥቃቅን አለመግባባቶችንና እንቅፋቶችን ማለፍ ወይም ማስወገድ ይቻላል። ነገር ግን እንቅፋቶችን ማለፍ ካልተቻለ፣ ከወንጌል የሚገኘው ደስታ ሊቀንስ ወይም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለን ግንኙነት፣ ስለ እርሱ ለመመስከር ያለን ፍቅር፣ ጥሪያችንም ሊቀንስ ይችላል ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሌላው የሥራ እንቅፋት ነው ያሉት፣ ታማኝነትን ማጉደልና ጥቅማ ጥቅምን ፈልጎ ወደ ቤተክርስቲያን መጠጋት ሲሆን ይህንንም ሲያስረዱ፣ በቤተክርስቲያኒቱ እየተካሄደ ያለውን የተሃድሶን እንቅስቃሴ ለማሳካት ተብሎ በጥንቃቄ የተመለመሉ እና እምነት የተጣለባቸው ሰዎች እያወቁ ወደ ጥፋት መሄዳቸውና ይህም ሳያንሳቸው ባጠፉት ጥፋት ተጸጸተው ይቅርታን ከመጠየቅ ይልቅ ጥፋታቸውን ወይም ስህተታቸውን በሌላን ሰው መጫንን ይመርጣሉ ።

ይህን የመሰለ እንቅፋት ቢኖርም፣ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን በመቀጥል፣ በቅድስት መንበር ጳጳሳዊ ተቋማት ውስጥ የተሰጣቸውን ሃላፊነት በታማኝነት የሚወጡ፣ ሥራቸውን በትጋት፣ በብቃት፣ በታማኝነትና በቅድስና የሚያከናውኑ ብዙሃኑን ክፍል መዘንጋት የለብንም ብለዋል። ቅዱስነታቸው በማከልም የእግዚአብሔርን ሕዝብ ለማገልገል ቆርጦ ለተነሳ ሰው ተሐዝዞ የመጀመሪያው መርህ ሊሆን ይገባል። እንደዚሁም በቅድስት መንበር የሥራ ተቋማት ውስጥ ለተሰማራ ማንም ሠራተኛ ከቅዱስ ጴጥሮስ ሐዋርያዊ አገልግሎት እና ከሥራ ባልደረቦቹ ጋር የጠበቀ ሕብረት እንዲኖረው ይገባል ብለዋል።

በቅድስት መንበር በታቀፉት ሐዋርያዊ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች፣ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን እና የአለቆቻቸውን ፍላጎት በታማኝነት የሚፈጽሙ፣ የመላዋ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንን ጥያቄ፣ ድምጽ፣ ደስታንና ሐዘንን ለሮማው ጳጳስ ለሆኑት ማለትም ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ማሳወቅ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ በቅድስት መንበር ለመማክርት ጉባኤ አባላትና ለጳጳሳዊ ምክር ቤቶች ተወካዮች ባስተላለፉት መልዕክታቸው፣ የቅድስት መንበር የምታከናውናቸው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ሥራዎች በርካታ እንደሆኑ አስታውሰዋል። ከእነዚህም መካከል አንዱና መሠረታዊ የሆነው የውጭ ግንኙነት እንደሆነ ጠቅሰው፣ ከውጭ መንግሥታት ጋር ሊኖር የሚገባውን ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን ማጠናከር የመላዋ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ተግባር እንደሆነ አስታውቀዋል። ቅድስት መንበር ዘላቂና ግልጽ የሆኑ ጥናቶችን በማድረግ ከተለያዩ አገሮች መንግሥታት ጋር መልካም ግንኙነት እንዲኖር ለማድረግ ሰላምንና የውይይት መድረኮችን ታመቻቻለች ብለዋል። ቅዱስነታቸው አክለውም፣ ቅድስት መንበር ይህን ሁሉ ስታደርግ ከማንኙውንም ዓይነት ዓለማዊና ቁሳዊ ፍላጎቶች ራሷን ነጻ በማድረግ ነው ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በንግግራቸው ቅድስት መንበር በዓለም ዙሪያ ካሉት ሀገረ ስብከቶችና እያንዳንዱ ቁምስናዎች ጋር ያላትን የጠበቀ ግንኙነት አስታውሰዋል። ቅድስት መንበር እምነት በተሞላበት አካሄድ ራሷን ከተቀሩት መላዋ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ ሥራዎች መምሪያ ጽሕፈት ቤቶች ጋር በእኩል ዓይን በመመልከት፣ በመተጋገዝ ትሰራለች ብለዋል። ይህን በማድረግ ለውይይትና ለርስ በርስ ግንኙነት መልካም ዕድሎችን ትከፍታለች ብለዋል። ቅዱስነታቸው ንግግራቸው በመቀጠል ቅድስት መንበር በመላዋ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኙትን የምስራቅ ቤተክርስቲያናት አስታውሰው የላቲን ስርዓት ከምትከተል የሮማ ቤተክርስቲያን ጋር በስርዓተ አምልኮ ግንኙነትና ሌሎች መንፈሳዊ ትምህርቶችን በመጋራት የጠበቀ ግንኙነት እንዲኖር ጥረት ታደርጋለች ብለዋል።

ቅድስት መንበር ትኩረት ከሰጠችባቸው ሥራዎች መካከል አንዱ ወጣቶችን የሚመለከት ሲሆን ቅዱስነታቸው፣ መላዋ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ወጣቶችን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ትኩረትን በመስጠት ክትትል እንደምታደርግ አስታውሰዋል። ይህን በተመለከተ በጥቅምት ወር 2011 ዓም ሊካሄድ የታቀደውንና በዋናነትም ወጣቶች፣ እምነታቸው እና ጥሪያቸው በሚሉ ርዕሠ ጉዳዮች ላይ የሚመክር የጳጳሳት ሲኖዶስ ሊካሄድ ዝግጅት በመደረግ ላይ እንዳለ አስታውሰዋል። ቅድስት መንበር፣ የየአገራቱ የጳጳሳት ጉባኤና መላዋ ቤተክርስቲያን ወጣቶችን በሚመለከቱ አስቸኳይ ጉዳዮች ላይ ልዩ ትኩረትን በመስጠት፣ ባዲሱና ባለፈው ትውልድ መካከል ያለውን ግንኙነት በማጤን፣ ሊያገኙ የሚገባቸውን ቤተሰባዊ፣ ሐዋርያዊና ማሕበራዊ አገልግሎቶችንም በስፋት ይመለከታል ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ንግግራቸውን በመቀጠል፣ ቅድስት መንበር በአቢያተ ክርስቲያናት መካከል ውይይት በማድረግ መቀራረብን ለማምጣት በሕብረት መጓዝ እንደሚያስፈልግ አሳስበው፣ እስካሁን ክርስቲያኖችን አራርቆ የቆዩ ስነ መለኮታዊ ልዩነቶችም ቢሆኑ በውይይት ሊፈቱ እንደሚችል ተናግረዋል። ቅድስት መንበር ከአብያተ ክርስቲያናት ጋር ያላትን ግንኙነት ያስታወሱት ቅዱስነታቸው፣ በአብያተ ክርስቲያናት መካከል ግንኙነትን የበለጠ  ለማጠናከር ብቸኛው አማራጭ ልዩነቶችን ማጥበብ ነው ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በንግግራቸው ማጠቃለያ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ልደት፣ እንድንጠነክር፣ እንድናድግ እና እንድንለመልም የሚያደርገን እምነት እንዳለን ያስታውሰናል ብለዋል። እምነትም ልባችንን፣ ሕይወታችንንና ሙሉ ማንነታች አንድ ማድረግ የሚችለው እግዚአብሔር በልባችን ዉስጥ በየጊዜው እንዲወለድ ሲያደርግ፣ በድሆችና በትሁቶች መካከል መወለድን ወደ መረጠው የእግዚአብሔር ልጅ  ወደ ሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ሲመራን ነው ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በመጨረሻም ለቅድስት መንበር የመማክርት ጉባኤ አባላትና የቅድስት ማህበራት ተወካዮች በሙሉ፣ በብጹዕ አባ ማርያ ኤውጀኒዮ የተጻፈውና እግዚአብሔርን ለማየት እመኛለሁ” በሚል አርዕስት የሚታወቀውን መጽሐፍ በስጦታ መልክ አቅርበውላቸዋል።                                    

             

 

23/12/2017 15:56