2017-12-04 16:47:00

ቅዱስ ኣባታችን በባንግላደሽ ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ከወጣቶች ጋር ተገናኝተው በለገሱት ቃለ ምዕዳን አጠናቀቁ


ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በባንግላደሽ ያካሄዱትን ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ልክ በምያንማር እንዳደረጉት ከአገሪቱ ወጣቶች ጋር ዳካ በሚገኘው ኖትረ ዳመ ካቶሊካዊ መንበረ ጥበብ ውስጥ ባለው የስፖርት ሜዳ ተገናኝተው በለገሱት ቃለ ምዕዳን ማጠቃለላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ አስታውቋል።

ካቶሊኮች ብቻ ሳይሆኑ ሙስሊም እና የሌሎች ሃይማኖት ተከታይ ወጣቶች በጠቅላላ 7 ሺሕ የሚገመቱ ወጣቶች ቅዱስ አባታችን በባህላዊ ሸብሸቦ እና በመዝሙር በተሸኘ ስነ ሥርዓት ደማቅ አቀባበል ካደረጉላቸው በኋላ በለገሱት ቃለ ምዕዳን፥

የወጣቱ ትኩስ ኃይል ተስፈኛነት እና የጋለውን ስሜት ስመለከት፥ ከወጣቶች ጋር ስገናኝ በእውነቱ የወጣትነት መንፈስ ይሰማኛል በማለት ለሁሉም ሰላታን በማቅረብ፥ ወጣቱ በሕይወት ጎዳና እንዲጓዝ፡ ወቅታዊ ችግር በሚያስከትልባችሁ ተስፋ መቁረጥ ፈተና የአእምሮ ጫና እግዚአብሔር ከአድማሱ የተሰወረ በሚያስመስል ችግሮ ሁሉ ሳትደናገጡ አደራ ዘወትር ወደ ፊት አቅኑ። በዓለማ የለሽ መንገድ ካለ ምንም እቅድ ከመመላለስ ይልቅ ቅኑ መንገድ ምረጡ፡ ይኸን መንገድ ለመምረጥም ከእምነት የሚወለደው ጥበብ ያስፈጋል። እምነት ልክ እግዚአብሔር ለማመዛዘን እና ለይተን የምንከተለውን መንገድ ለማወቅ እንድንችል በውስጣችን እንዳስቀመጠው በኮምፒዩተረ እንዳለው ሶፍትወር (የኮምፒዩተር ማዘዣ) ነው፡ በውስጣችን ያኖረው መለኰታዊ መርሐ ግብሩን የምናነብበት እና ይኸንን መርሐ ግብር ቃሉን በማንበብ ለይተን በማወቅ ተግባሪያን የሚያደርገን ኃይል ነው፡ ሕይወት አቅጣጫ ቢስ ሳይሆን እግዚአብሔር የተሰጠ ዓላማ አለው።

ይኽ ደግሞ እነዚያ በእግዚአብሔር በመታመናቸው እምነትን ከተቀበሉት ከቀደሙት አበው ከአያቶች እና ከወላጆች ዓይን ቀርበን የምያስተውለው እውነት ነው፡ ዓለምን የእኛን ሁኔታ ችግሮቻችንን ሁሉ በእግዚአብሔር ዓይን መመልከት፤ ሌሎችን በገዛ እራሳችን ሳይሆን በእግዚአብሔር ጆሮ ማዳመጥ፡ በእግዚአብሔር ልብ ማፍቀር፡ እሴቶቻችን በእግዚአብሔር እሴት መመዘን ማለት ነው።

የእግዚአብሔር ጥበብ ያንን ደስታ መሳይ የሆነው ወደ እራስ ወዳድነት ብቻ የሚመራው ኃሰተኛውን ደስታ እንድናገል በማድረግ ከእኛ የተለየ አመለካከት ያላቸውን እኛ የምንከተለውን የትግባሬ መንገድ የማይከተሉትን እንድናስተናግድ እንድንቀበል ይረዳናል። ስለዚህ በዚያ ትንሽ ዓለም በሆነው በገዛ  እራስ፡ እኔ እንዳልኩት ካልሆነ ያገናኘን ብሎ ለመሰናበት በሚቃጣው  መንፈስ ውስጥ ዝግታሞች አንሁን፡ አንድ ሃይማኖት ወይንም ኅብረተሰብ በገዛ እራሱ ትንሽየ ዓለም ውስጥ የሚዘጋ ሲሆን እኔ ብቻ ነኝ ደግ ሊላው ክፉ ነው  ከሚለው እራስ ከማብለጥ እብሪተኛነት መጠንቀቅ አለብን፡ እራስን ክፍ ማድረግ ሳይሆን በኃይማኖት በባህልም ባስተሳሰብም የተለየውን መቀበል።

ቅዱስ አባታችን ቃለ ምዕዳንን ከመለገሳቸው በፊት ኡፓሳ እና አንቶንይ ባስደመጡት ንግግር አቅርበዉት የነበረውን ጥያቄ መለስ ብለው በማንሳት፡ የእግዚአብሔር ጥበብ ለሌሎች ክፍት ተቀባዮች አስተናጋጆች እንድንሆን ያደርገናል፡ ከዚያ ለእራሴ ይመቸኝ ከሚለው ግላዊ ዋስትና ያለው ከሚመስለው ሌሎችን እና አበይት ግቦችን እንዳናይ ዓይነ ስውራን ከሚያደርግ ከተሳሳተ አመለካከቶች በላይ የመጠቀ ማየት እንዲኖረን ያደርጋል።

ካቶሊክ ወጣቶች ከሌሎች ኃይማኖቶች ተከታይ ወጣቶች ጋር ተገናኝተው ኅብረአዊነት ሲኖር ማየታቸው እጅግ እንዳስደሰታቸው ሲናገሩ፥ እንዲህ የመሰለው ኅብረአዊነትን ባብሮነት ሲገለጥ  ምንም በኃይማኖት የተለያያችሁ ብትሆኑ የተግባባ ለዘኛ ስምምነት በኅብረተሰብ ውስጥ እንዲነቃቃ የምታደርጉ መሆናችሁ ሳይ እጅግ ደስ ያሰኛል  ያሉት ቅዱስ አባታችን ይኸንን ለዘኛው ኅብረአዊነት በልዩነት፥ በቦኖስ አይረስ አማኝ ካቶሊኮች፡ ወጣት ኮሚኑስቶች፡ የአይሁድ እምነት ተከታዮች በጠቅላላ አለ ምንም ልዩነት ለጋራ ጥቅም በጋራ በሚል ዓላማ ማኅበራዊ ወዳጅነት በዚያ ድኽነት በሚታይበት ዳርነት ሁሉ በመገኘት ለመገንባት ባህል የሚያደርጉት የጋራ ጥረት ጋር የሚመሳሰል ገጠመኝ መሆኑ አብራርተው። እነዚህ ወጣቶች ያንን ልዩነት ሃብት ሳይሆን የመከፋፈል መሣሪያ ለማረግ ለሚራወጥ አላማ እምቢ በማለት እርስ በእርስ እንዲደጋገፉ እንዳደረጋቸውም ገልጠው፥ አደራ እናንተም ምንም ዘርፈ ብዙ ልዩነት ያላችሁ ብትሆኑም ቅሉ ለጋራ ጥቅም በጋራ ትጉዎች ሁኑ፡ ልዩነት ሃብት መሆን ያስተዋለ የሚጸናው ለዘኛ ውህደት እንዴት ደስ ያሰኛል። ይኸንን ነው በባንግላደሽ ያየሁት።

የእግዚአብሔር ጥበብ፤ ያለህ የባህል ሃብት የተስተዋለ ግንዛቤ ትሰጠው ዘንድ ያደጋል። የእናንተ ባህል አዛውንቱን በእድሜ የገፋውን መከበር እንዳለበት ያስተምራል። አደራ ሌላውን ካንተ ውጭ የሆነውን ችላ በማለት ቀኑን ምሉ በእጅ ለፎን ላይ ተለጥፋችሁ እትዋሉ። ንግግራችሁ ውሎአችሁ በእጅ ስልክ ላይ ችክ ያለ አይሁን። ይልቁንም የጥንቱን ጉዞ ቤተኛ እናድርግ። ማለትም ተጨባጩ ሁነት ከእኛ በላይ እጅግ ከፍ ያለ መሆኑ እናስተውል፡ ከወላጆች ከጎረቤቶች ከሌሎች ጋር፡  ከአያያቶች ጋር መገናኘት እና መነጋገር ያስፈልጋል፡ ክርስቲያኖች ይኸንን የግኑኝነት ወይንም የመገናኘት ባህል በጸሎት፡ በቅዱሳት ሚሥጢራት በኩል በድኾች በተናቁት በታመሙት ውስጥ ከኢየሱስ ጋር ይገናኛሉ። በኢየሱስ የእግዚአብሔር አሳቢነትን ደጋፊነትን ተባባሪነትን ኅብረትን እናገኛለን።

ፊታችሁ ሳይ ምሉእ ደስታ እና ተስፋ እመለከታለሁ። ሃሴት እና ተስፋ የታተመባችሁ መሆናችሁ እረዳለሁ። ይኽ ደግሞ ለአገራችሁ ለቤተ ክርስቲያናችሁ ለማኅበረሰባችሁ ነው፡ ያሉት ቅዱስ አባታችን ንግግራቸውን ሲያጠቃልሉ፥ እግዚአብሔር ባግላደሽን ይባርክ እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ፥ ቅዱስ አባታችን ከመለገሳቸው ቀደም በማድረግ ከወጣቶች ጋር ባካሄዱት ግኑኝነት ቅዱስ አባታችን ስለ ጎበኙን ለእኛ ያለዎት ፍቅር በመግለጥዎት ምክንያት ትልቅ ደስታ ይሰማናል፡ በሰላም በፍቅር ላይ የጸና ለዘኛ የጋራ ኑሮ እንድንኰተኵት የሚያበረታታ ቃል ለግሰውልናል የሚል ቃል ያማከለ የምስጋና ቃል ማሰማታቸውንም ገልጠዋው፡ በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን ንግግራቸውን እንዳጠቃለሉ በሁሉም በባንግላደሽ በምትገኘው በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያ ስም፡ በአገሪቱ ሕዝብ ስም፥

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. 21ኛው ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን በባንግላደሽ አጠቀው ወደ ሓዋርያዊ መንበራቸው ተመለሱ

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ዳካ በሚገኘው በኖትረ ዳም መንበረ ጥበብ ባለው የስፖርት ሜዳ ከወጣቶች ጋር ተገናኝተው በለገሱት ምዕዳን በማንግላደሽ ያካሄዱት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ግቡኝት አጠናቀው ልክ በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ 11 ሰዓት ከዘጠኝ ደቂቃ ላይ ዳካ ከሚገኘው ያየር ማረፊያ እንደ ደረሱ የባንግላደሽ መራሔ መንግሥት ሸይክህ ሃሲና የሽኝት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም ቅዱስነታቸው በዚህ በ21ኛው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው የሸኙዋቸው ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ልኡካን ጋዜጠኞን ሰላምታቸው ካቀረቡ በኋላ ከጋዜጠኞቹ የቀረበላቸው ጥያቄዎችን ላይ ተንተርሰው፥

ያካሄድኩት ሓዋርያዊ ጉዞ የምፈልገው ከእግዜብሔር ሕዝብ ጋር ከተጨባጩ የሕዝቦች ሕይወት ጋር መገናኘን ነው፡ እርግጥ ከአገር መሪዎች ከፖለቲካ አካላት ጋር የሚያገናኝ አጋጣሚም ነው፡ ከሁሉም ኃይማኖት መሬዎች ጋር በመገናኘትም የሕዝቦች መቀራረብ ብዙህነት ለለዛኛው ውህደት መሠረት መሆኑ እመሰክራለሁ። ስለዚህ ከዚህ አንጻር ስመለከተው በምያንማር እና በባንግላደሽ ያካሄዱኩት ሐዋርያዊ ጉዞ እግዚአብሔር ይመስገን የተዋጣለት ነበር ለማለት እደፍራለሁ።

 ባሰሙዋቸው ንግግሮች እና ባካሄዱዋቸው ግንኙነቶች ሁሉ የሰው ልጅ ክብር ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ ዙሪያ፡ የሁሉም የበላይ እና ተገዥ የሌለበት ሰው ሰው እንደ መሆኑ መጠን ለሰብአዊ ክብር የተገባ መሆኑ ገልጫለሁ። ማንም የማይነጥል ስደተኛውም ይሁን አገሬውም ሁሉንም የሚያቅፍ የሚያስተቃቅፍ አገር። ሁሉንም የተለያዩ ሃማኖቶችን የሚያስተናግድ ኅብረተሰብ፤ ፖለቲካ እና ኤኮኖሚ እንዲሁም በተለያዩ ኃይማኖቶች መካከል የሚከናወነው ግንኙነት የሰላም መሠረት መሆኑ ገልጫለሁ፡ የስደተኞች የተፈናቃዮች ሰብአዊ መብትና ክብር መከበር ዙሪያ መናገር ቀላል አይደለም። ስለዚህ በምያንማር ያለው ሁኔታ ተስፈኛ ነው፡ ለሮሂንግያ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ቅርበታቸውን እንደገለጡ እና የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብም ለእነዚህ ወድሞቻችን እና እህቶቻችን ቅርብ እንዲሆኑም ጥሪ ማቅረባቸውን አብራርተዋል።

ሌላው በቻይና ይፋዊ ጉብኝት ለማካሄድ እቅድ አለዎት ወይ የሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፥ ወደ ቻይና ይፋዊ ጉብኝት ለማካሄድ የሚል ቅድመ ዝግጅት አስከ አሁን ድረስ የለም። ቻይናን ብጎበኝ ደስ ባለኝ። ከቻይና ጋር ያለን ግኑኝንት ባህል ጉዳይ የሚመለከተ ነው፡ እየተካሄደ ያለው ባህላዊ ፖለቲካዊ ውይይት አመርቂ ነው። በተለይ ደግሞ ከቻይና ብሔራዊቷ ቤተ ክርስቲያን ጋር የሚመለከት መሆኑ ጠቅሰው፡ ይኽ ጉዳይ ብዙ ትዕግስት የሚጠይቅ ጉዞ ነው፡ ሆኖም ልብን ከፍቶ መቀብል የሚጠይቅ ጉዳይ ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አስስታወቁ።

 

ቅዱስ አባታችን ልክ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ታህሳስ 2 ቀን 2017 ዓ.ም. ሮማ በሚገኘው ፊውሚቺኖ አየር ማረፊያ ደርሰው በሰላም አገረ ቫቲካን ገብተዋል።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም ቅዱስ አባታችን ለይፋዊ ጉብኝት ሲነሱ እና ሓዋርያዊ ጉብኝቱን አጠናቀውም ሲመለሱ እንደ ሚያደርጉት ሁሉ ሮማ ወደ ሚገኘው ር.ሊ.ጳጳሳዊ ቅድስተ ማርያም ታልቅ - Santa Maria Maggiore ባዚሊካ በመሄድ በቅድስተ ማርያም መድህነ ሮማ ቅዱስ ምስል ፊት የምስጋና ጸሎት አሳርገዋል።

ቅዱስ አባታችን ወደ ሐዋርያዊ መንበራቸው ለመመለስ በጉዞ ላይ እያሉ ትዊተር በተሰየመው በማኅበራዊ መረብት ባለው አት ፖንቲፈክስ በተሰየመው አድራሻቸው አማካኝነት፥ ውዶቼ  የሚያንማር እና የባንልጋሽድ ሕዝቦችና መንግሥታት ላደረጋችሁልኝ መስተንግዶ አመሰግናለሁ። በእናንተ ላይ የሰላም እና ተስማሚ ውህደትን ከእግዚአብሔር እማጸናለሁ የሚል መልእክት መልቀቃቸው ደ ካሮሊስ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.