2017-11-29 16:41:00

ቅዱስነታቸው በምያንማር ከሚገኙ ከተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት ከተውጣጡ 17 ተወካዮች ጋር ተገናኙ


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በማክሰኞ በኅዳር 19/2010 ዓ.ም. የምያንማር ውሎዋቸው እረፋዱ ላይ 17 ከሚሆኑ ከተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር ተገናኝተው መክረዋል። በዚሁ ግንኙነታቸው “ሰላም የሚገኘው ሁሉም ሰዎች ወጥ የሆነ ሐይማኖት እና ባሕል እንዲይዙ በማድረግ ሳይሆን ልዩነቶችን ማዕከል ያደርገ አንድነት መፍጠር ሲቻል ብቻ መሆኑን” አጥብቆ አሳስበዋል። ቅዱስነታቸው በዚሁ ቆይታቸው 17 ከሚሆኑ ከቡዳ፣ ከሙስሊም፣ ከሂንዱ፣ ከአይሁድ፣ ከካቶሊክ እና ከተለያዩ የክርስቲያን ማኅበርሰብ ተወካይ መሪዎች ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸውም ተገልጹዋል።

የቅድስት መነበር የዜና እና የሕትመት ክፍል አፈቀላጤ የሆኑት አቶ  ግሬግ ቡርክ ቅዱስነታቸው ከተለያዩ የሐያማኖት ተቋማት ጋር ለ40 ደቂቃዎች ያህል አድርገውት የነበረውን ውይይት አስመልክተው እንደ ገለጹት በሀገሪቷ የሚገኙ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍሎች በሀገሪቷን ለመገንባት እንዲሠሩ አጥብቀው ማሳሰባቸውን ገለጸው በመካከላቸው በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ክርክር ቢፈጠር እንኳን ክርክራቸውን በጠላትነት ሳይሆን በወንድማማችነት መነፍስ በማድረግ በስተመጨረሻም እርቅ የመፈጥረ በሕላቸውን እንዲያስድጉ ቅዱስነታቸው መምክራቸውን ገለጸዋል።

“አንድነት ማለት ሁሉንም ነገር ወጥ በሆነ መልኩ ማከናወን ማለት አይደለም” በማለት በውይይቱ ወቅት የተናገሩት ቅዱስነታቸው “ወንድሞች ተስማምተው በአንድነት ሲኖሩ፣ ማየት እንዴት መልካም ነው! ምንኛስ ደስ ያሰኛል!” የሚለውን ከመዝሙር 133፡1 በመጥቀስ ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው አንድ መሆን ማለት ሁሉንም ነገር እኩል ወይም ወጥ ማድረግ ማለት እንዳለሆነ ገልጸው በሐያማኖት ተቋማትም ውስጥ እንኳን ቢሆን አንድነት ማለት ሁሉንም ነገር ተመሳሳይ ማድረግ ማለት አለመሆኑን ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው ምክንያቱን ስያብራሩ “ እያንዳንዱ ነገር የራሱ የሆነ እሴት፣ ቱባ የሆነ ባሕል እና እንዲሁም ጉድለት አለው በመሆኑ የተነሳ ሁላችንም ልዩ ነን” ያሉት ቅዱስነታቸው ይህንን መልካም የሆነ ቱባ ባሕላችንን እና እሴቶቻችን ለሌሎች ማካፈል ይምንችለው “ ሰላም” ሲኖር ብቻ መሆኑን ገልጸዋል። ሰላም ደግሞ ሊረጋገጥ የሚችለው በልዩነቶች ላይ የተመሰረተ አንድነት ሲኖረን ብቻ ነው በማለት አክርለው ገልጸዋል።

ሁሉንም ነገር ወጥ ለማድረግ መስራት አደገኛ ነገር መሆኑን የገለጹት ቅዱስነታቸው "ሰላም ሕብረትን ያመጣል አሁን በዚህ ባለንበት ዓለማችን የሚታዩ አደጋዎች እየተፈጠሩ የሚገኙት ሁሉንም ሰው እኩል ለማድረግ ሁሉንም ነገር ወጥ ማድረግ ያስፈልጋል ብሎ በማሰብ በሚደረጉ እንቅስቃሴ የተነሳ መሆኑን” ገልጸው በአሁኑ ወቅት ሁሉንም ነገር ወጥ በሆነ መንገድ ለማስኬድ የሚደረገውን የርዕዮተ ዓለም ቅኝ ግዢ አስተሳሰብ በከፍተኛ ሁኔታ አውግዘው "ሰላም የሚከበረው በሰላማዊ መንገድ ብቻ ላይ በተመሠረተ መልኩ ነው" ብለዋል።

“ከሁሉም በላይ ደግሞ የተለያዩ የሐያማኖት ተቋማት መሪዎች ልዩነታችን ውበት መሆኑን መረዳት ይኖርብናል” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “በዘር፣ በሐይማኖት እዲሁም እኔ ታዋቂ ነኝ አንተ ግን አይደለህም በሚሉትን ዓይነት አስተሳሰቦች ምክንያት የሚነሱ ክርክሮች በውይይት ብቻ መፈታት እንዳለባቸው” ቅዱስነታቸው ጠቁመዋል።

“ምያንማር ተፈጥሮ በሰጠቻት ጸጋ የተነሳ በጣም ሃበታም የሆነ ሀገር ነው፣ መልካ ምድሯም ሳይቀር በጣም የተለያየ በመሆኑ የተንሳ ይህ የመልካምድር ልዩነት እና አቀማመጥ ውበትን ለሀገሪቷ እንዳላበሳት” የጠቀሱት ቅዱስነታቸው “ሁላችንም አንድ አባት ያለን በመሆናችን የተነሳ ወንድማማቾች ሆነናል፣ ይህንንም የወንድማማችነት መንፈስ ጠብቀን መጓዝ ይኖርብናል” ብለዋል።

“ቅድስናን የተሞላ አንድነት መፍጠር የሚቻለው በልዩነታችን ስናምን ብቻ ነው” ያሉት ቅዱንስነታቸው “ልዩነታችን ውበት መሆንን ሁል ጊዜ ልብ ማለት ያስፈልጋል” ካሉ ቡኃል ንግግራቸውን ደምድመዋል።

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.