Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ሐዋርያዊ ጉዞዎችና ጉብኝቶች

ቅዱስ አባታችን በምያንማ፡ ሰላም ለማረጋገጥ ፍትሕ እና የሰብአዊ መብት አክብሮት ወሳኝ ነው ማለታቸው ተገለጸ

ቅዱስነታቸው ከምያንማር ርዕሰ ብሔር ሂትን ኪያው ጋር በተገናኙበት ወቅት - EPA

29/11/2017 16:08

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከምያንማር ርእሰ ብሔር ህቲን ክያው ጋር ቀጥለውም ከመንግሥት አማካሪ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒ. ኡውንግ ሳን ሱ ክዪ ጋር ያካሄዱት ክሌአዊ ግንኙነት ካጠናቀቁ በኋላ ከቤተ መግንሥት ተሰናብተው ከአገሪቱ የመንግሥት አካላት ከሲቪል ማኅበራት ወኪሎች፡ በምያንማር የውጭ አገር ልኡካነ መንግሥታት ከርእሰ ብሔር ሕንፃ 11 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደ ሚገኘው በዓለም አቀፍ የሸንጎ ማእከል ባለው የጉባኤ አዳራሽ ተገኝተው የመጀመሪያው ይፋዊ ንግግራቸው አሰምቷል ያሉት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ማሶቲ አያይዘው፥

ቅዱስነታቸው ሰላምታቸውን በማስቀደም ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው፡ በምያንማር መገኘቴ ለዚያ በአገሪቱ ለሚገኘው በቁጥር አናሳ ነገር ግን ለእምነቱ ቀናኢ ለሆነው ካቶሊክ ምእመን በእምነት ለማጽናት እና ለአገሪቱ እድገት በጽናት ለጋራ ጥቅም ዓላማ ተነሳስቶ የሚያበረክተው አስተዋጽዖ ለማበረታታት ነው፡ ይህ ጉብኝቴም መላው የአገሪቱን ሕዝብ የሚያቅፍ  ሆኖ በዚያ ቅን የታረቀ ማንንም የማያገል ሁሉን አቀፍ ማኅበራዊ ሥርዓት ለማስፈን ለሚተጉት ሁሉ የማበረታታቻ ቃል ለማቅረብም ያለመ ነው፡ ሲሉ በቅርቡ እ.ኤ.አ. ግንቦት 4 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቅድስት መንበር ጋር ክሌአዊ ግንኙነት በጀመረቸው አገር የሚያካሂዱት የሐዋርያዊ ጉብኝት ጥልቅ ትርጉሙን ገልጠው፡ ይኽ ደግም ቅዱስነታቸው የአገሪቱ ግንባታ በልባቸው ያለ ጉዳይ መሆኑ ያረጋግጣል ሲሉ ማሶቲ ገልጠዋል።

ምያንማር እጅግ በሚያስደንቅ መልከዓ ምድራዊ ውበት የተዋበች በተፈጥሮ ሃብት የታደለች ሆኖም እጅግ የላቀው ሃብቷ ያ ብዙ ስቃይና መከራ ያሳለፈው ገና ባላበቃለት ጥልቅ መከፋፈል በሚወልደው ግጭት ሳቢያ በስቃይ ላይ ያለው ሕዝቧ ነው። ቢሆንም አገሪቱ ይኸንን ሁሉ ስቃይ ችላ ከዚህ ማጥ ለመውጣት ሰላም መልሶ ለማረጋገጥ ግጭቱ የከሰተው ዘርፈ ብዙ ተድዳሮቶች ሁሉ ፖለቲካዊ እና መንፈሳዊ ፈውስ እንዲያገኝ ተግታ በመሥራት ላይ ትገኛለች። መንግሥት በዚህ ዙሪያ ኃይሉን አቅሙን አጣምሮ እያከናወነው ያለው ጽኑ የአገር እና የሰላም ግንብታ የሚደነቅ ነው፡ ይኽ ሂደት ወደ ፊት ለማለት የሚችለው ፍትሕና የሰብአዊ መብት አክብሮት መሠረት ሲያደርግ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኵላዊ የሰብአዊ መብትና ክብር ድንጋጌ ጠቅሰው፡ ይኽ ውሳኔ በዓለም ፍትሕ ሰላም እድገት እና ልማት ለማረጋገጥ የሚችለው በጦር መሣሪያ ሳይሆን በጋራ ውይይት አማካኝነት መፍትሔ እንዲያገኝ በሚደረገው ጥረት መሠረት ነው እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ማሶቲ ይጠቁማሉ።

የምያንማር መጻኢ ሰላም መሆን አለበት፡ በመከባበር የእያንዳንዱ የኅብረትሰብ ክፍል አባላት የሁሉም ጎሳዎች ባህሎች የማንነት መለያዎችን የሁሉም ሰብአዊ መብትና ክብር አክብሮት በማረጋገጥ፡ የሕግ ሉአላዊነት ብሎም ሁሉም እያንዳንዱ የአገሪቱ ብሔር ብሔሮችን መብትና ክብር የሚዋስ የዴሞክራሲው ሥርዓተ ደንብ አማካኝነት የጋራ ጥቅም የሚያስጠብቅ አስተዋጽዖ እንዲያበረክት በማድረግ ነው። በዚህ ብዙ ተግዳሮት በተሞላው ጉዞ ሁሉም ሃማኖቶች አቢይ ሚና አላቸው፡ እርሱም የግጭቶ መንስኤ የሆነውን ሁሉ ነቅሎ ለማጥፋት አገናኝ ድልድይ በመገንባት ፍትሕ በመሻት ለሚሰቃዩት ሁሉ ነቢያዊ ድምጽ ሆኖ በመገኘት ነው፡ ስለዚሁ ለዚህ ዓይነቱ ጉዞ ልዩ አስተዋጽዖ አላቸው።

የሃይማኖት ልዩነት የመከፋፈልና ለእርስ በእርስ ችላ መባባል ተግባር ምክንያት ሊሆኑ አይገባም። ባንጻሩ ለውህደት ለእርቅ ይቅር ለመባባል ለመከባበር እና ለመቀባበል ለበሳል የአገር ግንባታ ኃይል መሆን ይገባቸዋል። ለአንድ አቢይ የተስፋ ምልክት ጥረት የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖት መሬዎች ለሰላም ድኾችን ለመደገፍ ለእውነተኛ የሃማኖታዊ እና የሰብአዊ እሴት ሕንጸት አገልጋዮች መሆንና ለጋራ ጥረት መሻት አብነት ሆነው መገኘት ይጠበቅባቸዋል። በእነዚህ እሴቶች ላይ የጸና መጻኢ መገንባት፡ ወጣቱን ትውልድ ለቅንነት ለተሟላ እድገት እና ለተባባሪነት ማነጽ፡ ይኽ ደግም የተረጋገጠ የአንድነት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሁሉም ማኅበራዊ ደረጃ ለሰላም እድገት ዋስትና ነው ያሉት ቅዱስ አባታችን ያስደመጡት ንግግር ሲያጠቃልሉ፥ የምያንማር ካቶሊክ ማኅበረሰብ በሰብአዊ እና በፈጠራ ተግባሮች አማካኝነት ከተለያዩ የሃማኖት ተከታዮች ጋር እንዲሁም መልካም ፈቃድ ካላቸው ሰዎች ጋር አንድ አዲስ ስምምነት እና መግባባት የሰፈነበት የዚህች የተወደደቸው አገሮች ሕዝቦች እድገት ለማስጨበት በሚደረገው ጥረት እንዲተጉ ማበረታታቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ማሶቲ አያይዘው፥ የአገሪቱ መንግሥት አማካሪ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒ. አውን ሳን ሱ ክዪ ያስደመጡት ንግግር ሲያጠቃለሉ፤ በጣልያንኛ ቋንቋ፥ ቅዱስነትዎ በእማኔ አብረን በጋራ መጓዙን እንቀጥልበት እንዳሉ አስታውቋል።

29/11/2017 16:08