Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ሐዋርያዊ ጉዞዎችና ጉብኝቶች

የር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በምያንማር ከኅዳር 17-18 የነበራቸው ቆይታ አጠቃላይ ይዘት

የር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በምያንማር ከኅዳር 17-18 የነበራቸው ቆይታ አጠቃላይ ይዘት - REUTERS

28/11/2017 15:33

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ  በማያንማር (በርማ) እና በባንግላዲሽ ከኅዳር 17-23/2010 ዓ.ም. የሚያደርጉት 21ኛው ሐዋሪያዊ ጉብኝት መርሃግብር

 

VViaggio Apostolico del Santo Padre in Myanmar e Bangladesh (26 novembre - 2 dicembre 2017)

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች በዛሬው እለት ትኩረት ሰጥተን ወደ እናንት የምናደርሰው ዘገባ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በማያንማር (የቀደሞ ስሟ በርማ)እና በባንላዲሽ ከኃድር 17 እስከ ኅዳር 23/2010 ዓ.ም. ድረስ የሰላም ልዑክ በሚል መሪ ቃል የሚያደሩትን 21 ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝት የተመለከቱ ዘገባዎችን በሰፊው ወደ እናንተ እናቀርባለን።

እሁድ ኅዳር 17/2010 ዓ.ም.

.

መነሻ

 

ሰዓት

ርቀት

መድረሻ

1

ከሮም ሊዮናርዶ ዳቪንቺ ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ

 

በኢትዮጲያ የሰዓት  አቆጣጠር

ከምሽቱ 05፡40

8,584 ኪ.ሜ

የ10፡20 ደቂቃ በረራ

የማያማር ዋና ከተማ ያንጎን

በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ 4፡00

 

 

 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በማያንማር እና በባንግላዲሽ ከኅዳር 17 እስከ ኅዳር 23/2010 የሚያደርጉትን ጉብኝት በትላንትናው እለት ማታ ጀመሩ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በማያንማር እና በባንግላዲሽ ከኅዳር 17 እስከ ኅዳር 23/2010 የሚያደርጉትን ጉብኝት በትላንትናው እለት ማታ ጀምረዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ይህንን 21ኛ ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን ከመጀመራቸው በፊት እንደ ተለመደው ማንኛውንም ዓይነት ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማድረግ ከሮም ከተማ በሚወጡበት እና ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን አጠናቀው በሚመለሱበት ወቅት በሮም ከተማ እምብርት ላይ በሚገኘው እና በአውሮፓ በማሪያም ስም ከተሰየሙት ባዚልካዎች መካከል በትልቅነቱ በሚታወቀው፣ በ18ኛው ክፍለ ዘመን ግንባታው እንደ ተጠናቀቀ በሚነገርለት በሳንታ ማሪያ ማጆሬ (Sanat Maria Maggiore) ባዚሊካ ተገኝተው ይህ ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸው የሰመረ ይሆን ዘንድ፣ በሚጎበኝዋቸው ሀገራት ውስጥም ሳይቀር ሰላም እና ፍቅር ይስፈን ዘንድ ጉዞዋቸውን ለማሪያም በደራ በመስጠት የእንደ ሚጀምሩ፣ በተመሳሳይ መልኩም ጉብኝታቸውን አጠናቀው በሚመለሱበት ወቅትም ሳይቀር በዚሁ ቤተክርስቲያን በመገኘት ለእግዚኣብሔር ምስጋናን ያቀርባሉ፣ በዚህም መስረት በትላንትናው እለት አመሻሹ ላይ በዚሁ በሳንታ ማሪይ ማጆሬ ባዚሊካ ተገኝተው ጸልት አድርሰዋል።

ቅዱስነታቸው ባሳንታ ማሪያ ማጆሬ ባዚሊካ ተገኝተው ጸሎት ካደርሱ ቡኃላ በትላንትናው እለት በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 5:40 ላይ በሮም ከተማ ከሚገኘው እና በ15ኛው ክፍለ ዘመን በኖረው የጌታን የመጨረሻ እራት እና ሞናሊዛን በመሳሰሉ ድንቅ በሆኑ ስዕሎቹ በሚታወቀው ብሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ ስም ከተሰየመው ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ማርፊያ በመነሳት ጉዞዋቸውን ጀምረው 8584 ኪሎ መትሮችን በአየር ላይ አቋርተው የ10፡20 ደቂቃ ጉዞ ካደረጉ ቡኃላ በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ 4 ሰዓት ላይ በማያንማር በያንጎን ከተማ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የአየር ማርፊያ ጣቢያ በሰላም አርፈዋል።

ቅዱስነታቸው ወደ ምያንማር ባደርጉት የአይሮፕላን ጉዞ የበረራ የአየር ክልሎቻቸውን ያቋረጡባቸውን አህጉራት፥ ለኢጣሊያ ሪፓሊክ ርዕሰ ብሔር ሰርጆ ማታረላ፡ ለርዕሰ ብሔሩ እና ለኢጣሊያ ሕዝብ ጸሎት ማድረግ እንደ ሚቀጥሉ አረጋግጠው፣ ሕዝብን የጋራ ተጠቃሚ በሚያደርግ የጋራን ጥቅም ያማከል ተግባር እንደ ሚያከናውኑ በመሻት እን ተስፋ በማድረግ “በዚህ ወደ ምያንማር እና ወደ ባንግላደሽ የማደርገው በሁለቱ አህጉራት ለሚገኙት በቁጥር አናሳ የካቶሊክ ምዕመናን በእምነት ለማጽናት እና ለማበረታታት በማለም የሰላም ተጓዢ በመሆን በማደርገው ጉዞ ለእርስዎ ክቡር የኢጣሊያ ርዕሰ ብሔር ሰላምታዬን አቀርባለሁ” የሚል የተሌግራም መእክት እንዳስተላለፉ የቅድስት መንበር የዜናና ህኅትመት ክፍል መግለጫ ያስረዳል። በተመሳሳይ መልኩም የተሌግራም መልእክት የአየር በረራ ክልሎቻቸውን ላቋረጡባቸው ለክሮሺያ፣ ለቦስኒያና ኤርዘጎቪና፣ ለሞንተ ነግሮ፣ ለሰርቢያ፣ ለቡልጋርያ፣ ለቱርክ፣ ለጆሪጂያ፣ ለአዘርባጃን፣ ለቱርክ፣ ለአፍጋኒስታን፣ ለፓኪስታንና ለሕንድ መራሔ መንግሥታት ማስተላለፋቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

 

ቅዱስ አባታችን ... ፍራንቸስኮ ምያንማር ደረሱ

ቅዱስ አባታን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ህዳር 18 ቀን 2010 ዓ.ም. በማያንማር በያንጎን በሚገኘው የአይሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በፊት ልክ 04 ሰዓት ላይ ደርሰው በማያንማር እና በመቀጠልም ወደ ባንግላደሽ የሚያደርጉት 21ኛው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው በይፋ ጀምረዋል።

ቅዱስ አባታችን በአየር ማረፊያው እንደደረሱም ወደ አይሮፕላኑ ውስጥ በመግባት በታይላንድ ካምቦጃ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልዑክ በላኦስ ደግሞ ሐዋርያዊ ወኪል በሆኑት በብፁዕ አቡነ ፓውል ቻንግ ኢን ናም እና የቅድስት መንበር እና የምያንማር የውጭ ጉዳይ ግኑኝነት ሥነ ስርዓት ተጠሪ አማካኝነት ታጅበው  ከአይሮፕላኑ እንደወረዱ እዛው ይጠባበቁዋቸው በነበሩት በምያንማር ረፓብሊካዊት ርዕሰ ብሔር ልዩ ሚኒስትር ህቲን ክያዋ በምያንማር የጠቅላይ ቤተ ክርስቲያን ብፁዕን ጳጳሳት እና ወደ መቶ በሚገመቱ ሕፃናትና ባህላዊ ልብስ በለበሱ የምያንማር ብሔር ብሔረሰቦችን በወከሉት እና በመንግሥት ሰልፈኛው ክቡር ዘብ አቀባበል እንደተደረገላችው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ። ቅዱስነታቸው በቀጥታ ያንጎን ወደ ሚገኘው ወደ ሊቀ ጳጳሳዊ ሕንፃ ደርሰው በግል መሥዋዕተ ቅድሴ አሳርገዋል።

 

ቅዱስነታቸው በማያንማር ለሚያደርጉት ጉዞ የመረጡት አርማ

 

VViaggio Apostolico del Santo Padre in Myanmar e Bangladesh (26 novembre - 2 dicembre 2017)

 

ቅዱስነታቸው በማያንማር ለሚያደርጉት ጉዞ የመረጡት አርማ በልብ ቅርጽ የተሰራ እና በላዩ ላይ ሰላም እና ፍቅር የሚል ጹሑፍ የታተመበት ሲሆን በዚሁ የልብ ቅርጽ ውስጥ ደግሞ በግራ በኩል የማያንማር ሪፖብሊክ የሀገሪቷ ካርታ በቀኝ በደኩል ደግሞ የሰላም ምልክት የሆነውን  ነጭ እርግብ በእጃቸው ላይ በማይዝ ቅዱስነታቸው የተነሱት ፎቶ ታትሞ ይገኝበታል። ይህም አርማ በሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች መካከል ያለውን ልዩነት፣ ይህም ማለት አብዛኛው የማይንማር ማሕበረሰብ የቡዳ እምነት ተከታይ ነው፣ ቅዱስነታቸው የሚወክሉት ደግሞ የክርስቲያን ማሕበረሰቡን ነው፣ በሁሉቱ ማሕበረሰቦች ዘንድ ልብ ለልብ የሚያገናኝ  በፍቅር እና በሰላም የታጀበ ግንኙነት ይኖር ዘንድ ምኞቱን የሚገልጽ እና ይህንንም ምኞት በይፋ የሚያበስር  አርማ ነው።

ኅዳር 18/2010 ዓ.ም.

.

በማያንማር የሰዓት አቆጣጠር

(በማያንማርና በኢትዮጲያ   መካከል የ + 03፡30 ልዩነት አለ)

ክንውን

ቦታ

1

ጥዋት

ከምያንማር የመከላከያ ሰራዊት ጄነራል ጋር ለአጭር ጊዜ ተገናኝተው ሰላምታ እና ስጦታ ተለዋወጡ

በያንጎን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መኖሪያ ቤት

2

 ጥዋት

ከተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር ተገናኝተው ተነጋገሩ

በያንጎን ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ መኖሪያ ቤት

 

 11፡15

መስዋዕተ ቅዳሴ በግል አደረጉ

 በያንጎን ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ መኖሪያ ቤት

3

12፡00

የምሳ ሰዓት

በያንጎን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መኖሪያ ቤት

4

13፡25

የማያንማር ዋና ከተማ ወደ ሆነችው ኖ ፒ ቶ ለማቅናት ወደ ያንጎን የአየር ማረፊያ ተወሰዱ

ያንጎን ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ጣቢያ

5

14፡00

ከያንጎን ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ተነስተው ወደ ዋና ከተማዋ ኖ ፒ ቶ ደረሱ

ኖ ፒ ቶ

6

15፡50

በማያንማር ዋና ከተማ በኖ ፒ ቶ በሚገኘው የሀገሪቷ መርሔ መንግሥት የመኖሪያ ቤት ደርሰው በሀገሪቷ መርሔ መንግሥት በሳን ሱ ኪ እና በሌሎች የዲፕሎማሲ አባላት ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

ኖ ፒ ቶ የርዕሰ ብሔር መኖሪያ ቤት

7

17፡15

ከሀገሪቷ ባለስልጣናት፣ ከሲቪል ማሕበረሰብ ተወካዮች እና ከተለያዩ ሀገራት ከተውጣጡ ልዑካኖች ጋር ተገናኝተወ የመጀመሪያውን ኦፊሴልያዊ ንግግር አደረጉ

ኖ ፒ ቶ የርዕሰ ብሔር መኖሪያ ቤት

8

17፡45

ከሀገሪቷ ባለስልጣናት፣ ከሲቪል ማሕበረሰብ ተወካዮች እና ከተለያዩ ሀገራት ከተውጣጡ ልዑካኖች ጋር ተገናኝተወ የመጀመሪያውን ኦፊሴልያዊ ንግግር ካደረጉ ቡኃላ በኖ ፒ ቶ ወደ ሚገኘው የአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ተወሰዱ

ኖ ፒ ቶ የአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ

9

18፡20

ከኖ ፒ ቶ የውሮፕላን ማረፊያ ተነስተው 341 ኪ.ሜ በአየር ላይ አቋርጠው እና የ1፡05 ሰዓት ጉዞ አድርገው በያንጎን በሚገኘው የአውሮፕላን ማረፊያ ደረሱ

ያንጎን ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ

10

19፡50

በያንጎን በሚገኘው የሊቃነ ጳጳሳት መኖሪያ ቤት ደርሰው በግላቸው የእርት ግብዣ ተደረገላቸው

በያንጎን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መኖሪያ ቤት

         
 

 

 

በቫቲካን እና በማያንማር መካከል ስላለው የዲፕሎማሲ ግንኙነት እና ትብብር

ቫቲካን እና ማያንማር ሪፖብልክ ኦፊሰሊያዊ የሆነ ግንኙነት የጀመሩት እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በግንቦት 4/2017 ዓ.ም. (ከሰባት ወራት በፊ ማለት ነው)በዚሁ ዓመት እንደ ተጀመረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የቅድስት መንበርን በመወከል ከሀገሪቷ ጋር አስፈላጊውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እያደረገች የምትገኘው በአሁኑ ወቅት የታይላንድ፣ የካንቦዲያ እና የላዎስ የቅድስት መነበር አባሳደር በሆኑት በአቡነ ፖል ቻንግ ኢ ናም ለማያንማር የቫቲካን ልዩ ልዑክ በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በአሁኑ ወቅት በማያንማር በቁጥር አናሳ በሆኑ ሮሂንጋያ የሙስሊም ማኅበረሰብ ላይ በአገሪቱ የሚገኙ በአንድ አንድ አካራሪ የቡዳ እምነት ተከታዮች አማካይነት እየተፈጸ የሚገኘውን አሰቃቂ ጥቃት በማውገዝ የሰላም የኖቤል ተሸላሚ ለሆኑት እና በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር ለሆኑት ሳን ሱ ኪ በቁጥር አናሳ በሆኑት የሮሂንጋያ የሙስሊም ማኅበረሰቦች ላይ እየደረሰ ያለውን ጣቅት በማውገዝ ሰላም እና እርቅ እንዲፈጠር በተደጋጋሚ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወቃል።

በዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው ባለፈው ግንቦት ወር ላይ የማያንማር ፕሬዚዳንት የሆኑትን ሳን ሱ ኪ ን በቫቲካን ጋብዘው በሁለቱ ሀገራት የወደ ፊት ግንኙነት እና በእነዚህ በቁጥር አናሳ የሆኑት የሮሂንጋያ የሙስሊም ማኅበረሰብ አባላት ላይ እየተቃጣ የሚገኘው ጥቃት ባስቸኳይ ይቆም ዘንድ እና ብሔራዊ እርቅ ይደረግ ዘንድ ይህንንም በተመለከተ በግል ተገናኝተው መወያየታቸው የሚታወስ ሲሆን በአንድ አንድ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸውን እና ፕሬዚዳንት ሳን ሱ ኪም ቅዱስነታቸውን በኅዳር ወር ውስጥ ማያንማርን እንዲጎበኙ ጥሪ እንዳደረጉላቸው ያታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በማይንማር የሚያደርጉት በ21ኛ ሐዋሪያዊ ግብኝታቸው በአንድ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የተደረገ የመጀመሪያ ታሪካዊ ጉዞ ነው። በዚሁ ግቡኝታቸው ለቅዱስነታቸው ትላቁ ፈታና የሚሆንባቸው ነገር ቢኖር በአሁኑ ወቅት ከ600,000 ሺ በላይ ሰዎችን ለስደት እና ለመከራ የዳረገው በቁጥር አናሳ በሆኑት የሮሂንጋያ የሙስሊም ማሕበረሰቦች ላይ የተቃጣው ጥቃት ነው። ቅዱስነታቸው ይህንን ጥቃት በተደጋጋሚ አውግዘዋል። ነገር ግን አሁን አወዛጋቢ የሚሆነው ጉዳይ “ሮሂንጋያ” የሚለው የእነዚህ በቁጥር አናሳ የሆኑ የሙስሊም ማሕበረሰብ መጠሪያ መጠቀም እንደ ሌለባቸው የማያንማር ባለስልጣናት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱን አሳስበዋል። በሀገሪቷ የሚገኙ ብቸኛው ካርዲናልም ቅዱስነታቸው ይህንን የመጠሪያ ስም ባይጠቀሙ ይሻላ የሚል የበኩላቸውን አስተያየት ሰጥተዋል። ምክንያቱም “ሮሂናጋያ” የሚለው መጠሪያ የአንድ የማያንማር ጎሳ መጠሪያ ነው። ነገር ግን አብዛኛውን በማያንማር የሚኖሩ የቡዳ እምነት ተከታዮች እነዚህ በቁጥር አናሳ የሆኑ በማያንማር የሚኖሩ  የሙስሊም እምነት ተከታዮች በስደት ከባንግላዲሺ ወደ ማያንማር የገቡ በመሆናቸው የተነሳ ይህ “ሮሂንጋያ” የሚለው የማያንማር አንድ ጎሳ መጠሪያ ስም በመሆኑ፣ ለእነርሱ ይህ የመጠሪያ ስም አይገባቸውም በማለት እየሞገቱ ይገኛሉ። በዚህም ምክንያት ቅዱስነታቸው ይህንን የመጠሪያ ስም ከተጠቀሙ በብዙኃኑ የቡዳ እምነት ተከታዮች ዘንድ ቁጣ ይቀሰቅሳል የሚል ስጋት ፈጥሩዋል። ነገር ግን ቀደም ባሉት ጊዜያት ቅዱስነታቸው “በወንድሞቻችን እና በእህቶቻችን የሮሂንጋያ ማሕበረሰብ ላይ የሚደርሰው ጥቃት እና ስደት ይብቃ!” ማለታቸውም ይታወስል።

 

የማያንማር (የቀድሞ ስሟ በርማ) አጠቃላይ ሀገራዊ ሁኔታ በአጭሩ

ማያንማር እንደ የአውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ2015 ዓ.ም. በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ 54.4 ሚልዮን ሕዝብ ብዛት እንዳላት የተገለጸ ሲሆን በዋና ከተማዋ ያንጎን 4,800, 000 ሺ ሰዎች ይኖራሉ። እንደ የአውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር እስከ 2005 ዓ.ም. ድረስ የያንጎን ከተማ የምያንማር ዋና ከተማ ሆና ማገልገሉዋ የሚታወቅ ሲሆን “ያንጎን” የሚለው መጠሪያ ያገኘው እንደ የአውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1755 ዓ.ም. በወቅቱ በሀገሪቷ ሲካሄድ የነበረ የእርስ በእርስ ጦርነትን ማብቂያን አስመልክቶ የተሰጣት ስያሜ ሲሆን ይህም በሀገሪቷ ቋንቋ  “የግጭቶች ማብቂያ” የሚል ትርጓሜ አለው። እንደ የአውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከ2005 ዓ.ም. ጀምሮ ኖ ፒ ቶ የሀገሪቷ ውና ከተማ በምሆን እያገለገለዝ ሲሆን በሁኑ ጊዜ የምያንማር ዋና ከተማ የሀገሪቷ መዲና ከመሆኑዋ ባሻገር ከፍተኛ የሆነ የእንዱስትሪ እና መዋለ ነዋይ የሚንቀሳቀስባት ቦታ እንደ ሆነች ይታወቃል።

አብላጫው የሀገሪቷ ሕዝብ የቡዳ እምነት ተከታይ ሲሆን ኢኮኖሚያቸው መሰረቱን ያደርገው በከፍተኛ ሁኔታ እየተመረተ በሚገኙ የሩዝ፣ የጣውላ እና የመዕድናት ምርት ላይ እንደ ሆነም ለመገንዘብ ችለናል።

በማያንማር ዋና ከተማ በያንጎን የሚገኘው የካቶሊክ ሀገረ ስብከት በይፋ የተመሰረተው እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በጥቅምት 8/1991 ዓ.ም. ሲሆን በዚሁ ርዕሰ ሰባካ (Metropolis) ውስጥ ከሚኖሩ 12,191,500 ሕዝብ ወስጥ 62,490 የካቶሊክ ምዕመናን 42 ቁምስናዎች፣ 8 ትላልቅ አብያተ ክርስቲያናት፣ 89 የሀገረ ስብከት ካህናት፣ 23 ደናግላን 47 የዘርዐ ክህነት ተማሪዎች 72 የተለያዩ ማኅበራት፣ 382 የሴቶች ገዳም አባላት፣ 23 የትምሕርት መስጫ ተቋማት፣ 18 የእርዳታ መስጫ መዕከላት ይገኝእሉ። በዚህ በያዝነው ዓመት ብቻ 1,207 ምዕመናን መጠመቃቸው ታውቁዋል። የሀገረ ስብከቱን በበላይነት የሚመሩትም የ69 አመቱ ሊቀ ጳጳሳት ካርዲናል ቻርለስ ማኡንግ ቦ ናቸው።

 

 

 

28/11/2017 15:33