2017-11-24 15:28:00

"ባሕልን በርዕዮተ ዓለማዊ ቅኝ ግዛት ሥር ለማድረግ የሚሠሩ አመላካች ተግሮች በአሁኑ ወቅት ያታያሉ" ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ


ርዕሰ ሊቃን ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መሳዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት በአሁኑ ወቅት በወጣቶች የትምህርት አሰጣጥ ሂደት ውስጥ እየተንጸባረቀ የሚገኘው ርዕዮተ ዓለማዊ ቅኝ አገዛዝ የትምህርት ስርዓቱ ላይ እክል እየፈጠረ ይገኛል ማለታቸው ተገለጸ።

የሰው ልጆችን መብት መግፈፍ፣ ማህደረ ትውስታቸውን እንዲሰርዙ ማድረግ እና ወጣቱን ትውልድ በተሳሳተ አስተሳሰብ እንዲሞላ ማድረግ የሚሉት ሦስት ተግባሮች በአሁን ወቅት በዓለማችን እየታዩ የሚግኙ ባሕልን በርዕዮተ ዓለማዊ ቅኝ ግዛት ሥር ለማድረግ እና በምናባዊ አስተሳሰቦች እንዲሞሉ የሚያደርጉ አመላካች ምልክቶች ናቸው ብለዋል። የቅዱስነታቸው ስብከት የተመረኮዘው በእለቱ በላቲን የስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት ከመጀመሪያ መጽሐፈ መቃቢያን 2፡15-29 ላይ ተወስዶ በተነበበው እና በወቅቱ የአንጾኪያ ንጉሥ የነበረው  ኤፒፋነስ፣ የአባቶቻቸውን ሕግጋት በመጠበቅ በሚታወቁት ማቃባዊያንን ማሳደዱን በሚገልጽ ታሪክ ላይ መሰረቱን ያደረገ ስብከት እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል።

የእግዚኣብሔር ሕዝብ በነበሩት በመቃባዊያን ላይ ደርሶ የነበረው በደል ዛሬም ቢሆን በታሪክ አጋጣሚዎች በባሕል ላይ አባገንን በሚሆኑ እና ባሕልን ለማጥፋት ቀን ከሌሊት በሚተጉ የርዕዮተ አለማዊ ቅኝ ግዛት አስተሳሰቦች የተነሳ ዛሬም ቢሆን እየተከሰቱ የሚገኝ በደሎች ናቸው ብለዋል።

አባገንን በሆኑ እና ባሕልን ለማጥፋት ቀን ከሌሊት በሚተጉ የርዕዮተ ዓለማዊ ቅኝ ግዛት አስተሳሰቦች በባለፉት ዓመታት ይታያሉ፣ በአውሮፓ የተከሰተውን ነገሮች እስቲ ለአፍታ እናስብ? በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “የሃይማኖት ነጻነት ተገፉዋል፣ ታሪክን ሽረው ሌላ ታሪክ ጽፈዋል፣ የወጣቱን ትውልድ ባሕል እና ማህደረ ትውስታቸውን ሳይቀር በመቀየር በወጣቶች የትምህርት አሰጣጥ ሂደት ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተጽኖ ፈጥረዋል ብለዋል።

በአሁኑ ጊዜ ሁሉም የአውሮፓ ሀገራት የሚያደርጉት ይህንኑ ነው ለምሳሌ አንድ ድኸ የሆነ ሀገር ሃብታም የሆነውን ሀገር ብድር በሚጠይቅበት ወቅት እሺ ብድሩን እንሰጥኃለን ነገር ግን በሀገራቸው የትምህርት አሰጣጥ መርሃ ግብር ውስጥ ይሄን እና ያንን ማስገባት ይኖርባችኃል በማለት ከዚህ መጽሐፍ ይሄን ከዚያ መጽሐፍ ውስጥ ደግሞ ያንን ለወጣቶች ማስተማር ይጠበቅብችኃል በማለት የእግዚኣብሔር ሕልውና እና እግዚኣብሔር ዓለምን እንዴት እንደ ፈጠረ የተገለጸባቸውን መጽሐፍት እንዲያስወግዱ ተጽኖ እንደ ሚያደርጉም ቅዱስነታቸው በአጽኖት ገልጸዋል።

በዚህም ተግባራቸው የባሕል ልዩነቶችን በማስወገድ ወጥ የሆነ ባሕል እንዲመጣ ለማድረግ ይተጋሉ፣ ታሪክንም ለመሻር ይሠራሉ፣ ከዛሬ ጀምሮ ሁላችሁም እንዲህ ማሰብ ይኖርባችዋል፣ እንዲህ እንደ እኛ የማያስብ ሰው ግን ይገለላል ስደት መከራም ይደርስበታል በማለት የማስፈራሪያ ቃላትን እንደ ሚሰነዝሩም ቅዱስነታቸው ጠቅሰዋል።

“የመቃባዊያን እናት የነበረችው ሴት ልጆቹዋ የሕይወት መስዋዕትነት የሚያስከፍል አደጋ በሚገጥማቸው ወቅት በዚህ መከራ ፊት ጸንተው ይቆሙ ዘንድ ታበረታታቸው እንደ ነበረ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህም ልጆቹዋ ማሕደረ ትውስታቸውን እና ታሪካዊ የሆነውን ስር መሰረታቸውን እንዲጠብቁ ማስቻሉንም ጨምረው ገልጸዋል።

“ደኅንነታችንንና   የእግዚኣብሔር ልጆች መሆናችንን የሚያስታውሰንን፣ እንዲሁም እምነታችንን በጣም ጠንካራ እንዲሆን የሚረዳውን  ማህደረ ትውስታችንን ጠብቀን በመጓዛችን የተነሳ በባሕል ላይ ርዕዮተ ዓለማዊ ቅኝ ጋዛትን ለመጫን በሚፈልጉ የማኅበረሰብ ክፍሎች ስደት ሊደርስብን እንደ ሚችልም ጨምረው ገልጸዋል።

ማህደረ ትውስታችንን፣ ታሪካችንን፣ ጠቃሚ የሆኑ ሂሴቶቻችንን እና ከቤተስቦቻችን የተማርናቸውን  መልካም ነገሮች ሁሉ እንድናስታውስ በማድረግ ማንኛውንም ዓይነት አሰናካይ ወይም ጠማማ የሆኑ የመማር እና የማስተማር ስርዓቶችን ሁሉ እንድናሸንፍ ይረዳናል በማለት ቅዱስነታች አክለው ገልጸዋል።

በዚህም ረገድ በተለይም እናቶች እና በአጠቃላይ ሴቶች መልካም የሚባሉ የባሕል ሂሴቶች ተጠብቀው ይሄዱ ዘንድ በሚደረገው ሂደት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ አስተዋጾ እንደ ሚያበረክቱ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው በዚህም ተግባራቸው የአንድ ማኅብረሰብ ባሕል እና ታሪክ ተጠብቆ ወደ ፊት እንዲሄድ የራሳቸው የሆነ ከፍተኛ አስተዋጾ ያደርጋሉ ብለዋል።

እስከ ዛሬ ድረስ የእግዚኣብሔር መንግሥ ወደ ፊት መጓዙን የቀጠለው ለልጆቻቸው እምነትን ማስተማር እና ማውረስ በቻሉ በብዙ ሴቶች ድጋፍ የተነሳ መሆኑን የገለጹት ቅዱስነታቸው እናቶች እምነትን ለልጅ ልጆቻቸው የማስተላለፍ ከፍተኛ የሆነ ብቃት እንዳላቸው ገልጸው ጌታ ማሕደረ ትውስታችንን (memory) እንዳናጣ፣ የአባቶቻችንን በሕል ጠብቀን መጓዝ እንድንችል እና በተለይም ደግሞ እምነታቸውን ለልጆቻቸው ማውረስ የሚችሉ በብርታት የተሞሉ ሴቶችን በማኅብረሰቡ እና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይፈጥርልን ዘንድ ጸጋውን እንዲሰጠን ሁል ዲዜም ቢሆን መጸለይ ያስፈልጋል ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.