2017-11-24 15:37:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ድቁና የሚከወነው በቅድሚያ ድኾችን በማገልገል ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ገና የቡዌኖሳይረስ ሊቀ ጳጳስ እያሉ እና የቅዱስ ጴጥሮስ ተክታይ ሆነው ከተመረጡም በኋላ ማዕርግ ድቁናና እንዲሁም ድቁናነት ዙሪያ የሰጡት ትምህርትና በስልጣናዊ ትምህርት ዙሪያ በማስቀመጥ የሰጡት ጥልቅ ትንተና ድቁና በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እሳቤ በሚል ርእስ ሥር  በማጠቃለል በኢጣሊያ ረጆ ካላብሪያ እና ቦቫ ሰበካ ሥር ቋሚ ዲያቆን የኢጣሊያ የቋሚ ዲያቆናት ማኅበር ሊቀ መንበር ዲያቆን ኤንዞ ፒየትሮሊኖ የደረሱት መጽሐፍ በቫቲካን ማተሚያ ቤት ታትሞ ለንባብ መብቃቱ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ ገለጡ፡

የዚህ መጽሓፍ መቅድም በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የተደረሰ መሆኑ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ እያይዘው እንዳመለከቱትም፥ ቅዱስ አባታችን ዲያቆን የአዲስ ፍቅር ስልጣኔ ግንባር ቀደም አቅኚ ነው በማለት ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ያሉትን ሃሳብ በማስቀደም፥ ቤተ ክርስቲያን በዚያ የቋሚ ዲያቆን ጥሪ አማካኝነት የክርስቶስ ዲያቆናዊነት በሰብአዊ ታሪክ አገልጋይነት ማለት መሆኑ  በቃልና በተግባር በማመላከት ለዚህ አገልግሎት መግለጫ እና ህያው ግፊት በመሆን ትኖራለች። በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ቅዱስ ፍራንቸስኮ ዲያቆን እንደነበር ነው የሚነገረው። ስለዚህ ለቋሚ ድቁና ቅዱስ ፍራንቸስኮ እስትንፋስ መሆን አለበት በማለት ቅዱስነታቸው በማብራራት፡ ድቁና ለአስፍሆተ ወንጌል እና በቤተ ክርስቲያን ለጥሪ መበራከት ጸላይ ነው፡ ቤተ ክርስቲያን ስለ አስፍሆተ ወንጌል እና ስለ ጥሪ መሠረት ጸሎት መሆኑ በመኖር እና ይኸንን በማስተጋባት ሁሉም እንደየ ጥሪው አማካኝነትም የጸሎት ሃሳብ ያደርገዋል ይላሉ።

መላው የቤተ ክርስቲያን ዲያቆናዊነት ልበ ትርታዋ በዚያ በቅዱስ ቁርባን ምስጢር ውስጥ ያለ ነው፡ ይኽ ደግሞ እነዚያ ካልአ ክርስቶስ የሆኑትን የክርስቶስ ስቃይ - የድኅነት ኃይል በተጨባጭ ውክልናው እራሱ ክርስቶስ የሰጣቸው ድኾችን በማገልገል የሚኖር ነው፡ ከዚህ እንጻር ሲታይ ሁላችን ዲያቆናት ነን። ሌላው በታሪክ የሚጠቀሰው ሎረንዞ ህይወቱ ከሞት ለማትረፍ ከፈለገ በሚያገለግልበት የሰበካው ያለው ሃብት ለንጉሥ ክብር እንዲያውለው ያዘዋል፡  እርሱ ግን ድኾችን መረጠ፡ ድኾችን በመምረጡ ምክንያትም ሎረንዞ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 12 ቀን 142 ዓ.ም. በንጉሥ አንቶኒኖ ውሳኔ መሰረት የደም ሰማዕትነት ተቀበለ፡ ቅዱስ ሰማዕት ዲያቆን ሎረንዞ የድቁና አብነት ነው ሲሉ፥ የመጽሓፉ ደራሲ ዲያቆን ኤንዞ ፒየትሮሊኖ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ወቅታዊው ተግዳሮቶች፡ ስደተኞች ተፈናቃዮች ናቸው፡ ስለዚህ ይኸንን ድቁና ለእነዚህ ወንድሞቻችን በመኖር በቤተ ክርስቲያን የዲያቆናዊነት ጥሪ አገልግሎት ማለት ነው፡ ወደ ከተሞቻች እና ወደ የህልውና ዳር ያቀና አገልግሎት ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.