2017-11-23 15:54:00

ርዕዮታዊ አስተሳሰቦችን በሌሎች ላይ ለመጫን መሞከር ሁሉም ነገር ወጥ በሆነ መንገድ እንዲከናወኑ በማስገደ ስደትን ያስከትላል።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮ ዘወትር ጥዋት በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴን እንደ ሚያሳርጉ የሚታወቅ ሲሆን የእዚሁ መርሀ ግብር አንዱ አካል በሆነው በሕዳር 12/2010 ዓ.ም. በሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት በእለቱ ከሁለተኛው መጽሐፈ ማቃቢያን ከምዕራፍ 6፡18-31 ተወስዶ በተነበበው የመጀመሪያ ምንባብ ላይ በተገለጸው “አልዓዛር የሚባል አንድ በጣም እጅግ የተከበረ አዛውንት የሕግ ሰው አፉን በግድ ከፍተው የአሳማ ሥጋ እንዲመገብ አደረጉት፣ እርሱም ይህንን ከመቀበል ይልቅ የተከበረ መስዋዕትነትን መቀበል ፈለጎ መስዋዕት ወደ ሚሆንበት ቦታ በፈቃደኝነት መሄዱን” በሚገልጸው ምንባብ ላይ ተመርኩዘው እንደ ገለጹት ባሕልን እና ርዕዮታዊ አስተሳሰቦችን በሌሎች ላይ በግድ ለመጫን መሞከር ሁሉም ነገሮች ወጥ በሆነ መንገድ እንዲከናወኑ ስለሚያስገድድ በአማኞች ላይ ከፍተኛ ስደትን ሊያስከትል ይችላል ማለታቸው ተገለጸ።

ሦስት ዓይነት መሰረታዊ አስገዳጅ የስደት ዓይነቶች እንዳሉ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በሃያማኖት ላይ የሚቃጣው ስደት የመጀመሪያ ዓይነት ስደት መሆኑን ገልጸው ፖሌቲካዊ እና ሃይማኖታዊ ይዘት ያለው ስደት ደግሞ ሁለተኛው ዓይነት ስደት ነው ሦስተኛው እና የመጨረሻው አስገዳጅ የስደት ዓይነት ደግሞ በባሕል ላይ በሚደረግ ጥቃት የተነሳ የሚከሰት የስደት ዓይነት መሆኑን ቅዱስነታቸው አብራርተዋል።

በአሁኑ ጊዜም ቢሆን ይህንን እና ይህንን የመሳሰሉ በባህል ላይ የሚቃጡ ከፍተኛ ጥቃቶች እንዳሉ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው ባሕልን፣ እማነትን እና ሕግጋትን ሙልጭ አድርጎ ለማጥፋት ሌት ተቀን የሚኳትኑ ሰዎች እንዳሉ ጠቅሰው ይህም በስመ ዘመናዊነት የሚከናወን እና ሁሉን ነገር በአዲስ ለመተካት በማሰብ የሚደረግ የማሳደድ ተግባር እንደ ሆነ በአጽኖት ገልጸው ይህም አዲስ የርዕዮተ ዓለም ቅኝ ግዛት ውስጥ ብዙኃኑን እየከተተ መሆኑን፣ አንድ አንድ ሰዎችም ባሕላቸውን እና እምነታቸውን በመተው በዚህ አሁን እየተፈጠረ በሚገኘው ለየት ባለ አዲስ ባሕል ውስጥ መኖር እንደ ሚፈልጉ ገለጸዋል።

ነገር ግን በዚህ ሂደት ውስጥ ትክክለኛውን የሕዝቡን ባሕል ለመጠበቅ በሚደረገው ተግባ ውስጥ ግብግቦች እንደ ሚፈጠሩ የገልጹት ቅዱስነታቸው በዘመናዊንት ስም እየተፈጠረ የሚገኘውን ባሕል በመቃወም ሂደት ውስጥ ስደት እንደሚፈጠር ገልጸው ይህም የርዕዮተ አለም ቅኝ ግዛት ሁሉንም ነገሮች ወጥ በሆነ መልኩ ለማካሄድ ያቀደ እና በልዩነቶች የማያምን በመሆኑ የተነሳ ስደትን እንደ ሚያስከትል ገልጸዋል።

ይህም ማለት አዳዲ ነገሮችን ሁሉ መቀበል የለብንም ማለት አይደለም በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በወንጌል ውስጥ ኢየሱስ አዳዲስ ነገሮችን ይዞልን መምጣቱን አስታውሰው በዚህም መሰረት አዳዲ ነገሮችን ጠቃሚነታቸውን ለይቶ የማወቅ ችሎታ ያስፈልጋል ብለዋል።

“አዳዲስ ነገሮች በሚከሰቱበት ወቅት ሁሉ ይህ አዲስ ነገር የመጣው ከጌታ፣ ከመንፈስ ቅዱስ ወይም ደግሞ በእግዚኣብሔር ላይ ስር መሰረቱን አድርጎ ነው ወይስ? መጥፎ፣ ክፉ እና የተዛባ መሰረት ነው ያለው? በማለት በጥንቃቄ መመልከት ያፍልጋል ብለዋል።

“ድሮ ድሮ ቀደም ባለው ጊዜያት ጽንስ ማስወረድ በጣም ትልቅ የሆነ ኃጢኣት ተደርጎ የቆጠር ነበር፣ አሁን ግን ሲደረግ እናያለን፣ ድሮ ድሮ ቀደም ባሉት ጊዜያት ነገሮች እግዚኣብሔር በፈጠራቸው መልኩ በግልጽ ተለይተው ይታወቁ እና ይከበሩ ነበር፣ ነገር ግን ዛሬ እኛ ትንሽ ዘመናዊ የሆንን ስለመሰለን ሁሉንም ነገር አንድ ለማድረግ በማሰብ ነገሮችን ሁሉ በመቀላቀል ላይ እንገኛለን፣ ክፉ የሆነ ሥር መሰረት ያለው የተዛባ ባሕል የምላችሁ  ይህንን  እና ይህንን የመሳሰሉ ተጋብራትን ነው፣ ከእግዚኣብሔር የሚገኙ አዳዲ ነገሮች በምንም መልኩ ለድርድር የሚቀርቡ ነገሮች አይደሉም ምክንያቱ እንድናድግ የመጪውን ጊዜ እንድንመለከት የሚያደርጉን መልካም ነገሮች በመሆናቸው ይተነሳ ነው” ብለዋል።

“አዳዲስ የሆኑ የርዕዮተ ዓለም  ቅኝ ግዛት ውስጥ ሊዘፍቁን  የሚፈልጉ አስተሳሰቦች እና ባሕሎች ያለፈውን  ጊዜ ባሕል የሚክዱ፣ የመጭውን ጊዜ የማይመለከቱ፣ ነገር ግን የአሁኑን ጊዜ ብቻ አትኩረው የሚመለከቱ በመሆናቸው የተነሳ ጎጂ የሆኑ ባሕሎች ናቸው” ያሉት ቅዱስነታቸው የሚኖሩት የአሁኑን ጊዜ ብቻ እንጂ በጊዜያት ውስጥ ያሉትን ነገሮች በትኩረት የሚመለከቱ ባለመሆናቸው የተነሳ ተስፋ የሚሰጡን ነገሮች አይደሉም ብለው በዚሁ ሁሉንም ባሕል ወጥ እንዲሆን በሚያደርግ ጸባያቸው የተነሳ በጣም አጸያፊ የሆኑ ኃጢኣቶችን ይፈጽማሉ በእግዚኣብሔር ላይም የእርግማን መኃት ያወርዳሉ ብለዋል። 

በዛሬው መጀመሪያ ምንባብ ላይ (2ኛው መጽሐፈ ማቃቢያን 6፡18-30) ከተጠቀሰው ከአልዓዛር ታሪክ የምንማረው ጊዜያዊ የሆኑትን ጥቅማጥቅሞች ብቻ መመልክት ሳይሆን የወደፊቱን ሁኔታ መመልከት እንደ ሚገባን ያስተምረናል ያሉት ቅዱስነታቸው ይህም ለመጪው ትውልድ ገንቢ እና ፍሬያማ የሆኑ ነገሮችን ማወረስ እንደ ሚኖርብን ያስተምረናል ያሉት ቅዱስነታቸው መልካም የሚባሉ እሴቶችን በመጠበቃችን ለሎችም ሕይወት ያገኙ ዘንድ ክፍተኛ አስተዋጾ ያደርጋል ካሉ ቡኃላ ዛሬ በመጀመሪያው ምንባብ ውስጥ የተጠቀሰው የአልዓዛር መልካም ምሳሌ አሁን ባለንበት ዘመን እየተቃጣብን ከሚገኘው ባሕልን እና ሐያማኖትን በርዕዮተ ዓለም ቅኝ ግዛት ሥር ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት መቋቋም እንችል ይረዳን ዘንድ እና ለሕይወታችን ትምሕርት እና ተነሳሽነትን በመስጠት ይህንን አድጋ መቋቋም እንችል ዘንድ እንድረድን መማጸን ያስፈልጋል ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.