Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስና የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ

"መስዋዕተ ቅዳሴ በክርስቶስ የፋሲካ ምስጢር ተካፋዮች እንድንሆን በማድረግ ከሞት ወደ ሕይወት እንድንሻገርም ያደርገናል"።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ - ANSA

23/11/2017 15:49

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በተለያዩ አርእስቶች ዙሪያ የትምህርተ ክርስቶ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። ከዚህ ቀደም ባሉት ጊዜያት በተከታታይ ያደርጉት የነበረው አስተምህሮ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው የክርስቲያን ተስፋ በሚል ጭብጥ ዙሪያ ላይ ያጠነጠነ እንደ ነበረ በስፋት መግለጻችን የሚታወቅ ሲሆን፣ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ደግሞ በመስዋዕተ ቅዳሴ ዙሪያ ላይ ትኩረቱን በማድረግ በተለይም ደግሞ በቅዱስ ቁርባን ምስጢር ዙሪያ ላይ ያጠነጠነ አስተምህሮ በተከታታይ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

የዚህ መርሃግብር አንዱ አካል በሆነ በሕዳር 13/2010 ዓ.ም. ያደረጉት የጠቅላላ አስተምህሮ በመስዋዕተ ቅዳሴ ዙሪያ ባለፉት 2 ሳምንታት ካደረጉት አስተምህሮ የቀጠለ አስተምህሮ እንደ ነበረ የታወቀ ሲሆን መስዋዕተ ቅዳሴ የክርስቶስ የፋሲካ ምስጢር መታሰቢያ ነው ማለታቸውም ተገልጹዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያደረጉትን አስተምህሮ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

የተወዳዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን ሰነበታችህ!

በመስዋዕተ ቅዳሴ ዙሪያ ጀምረነው የነበረውን የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል  መስዋዕተ ቅዳሴ መስረታዊ ነገሩ ምንድነው? ብለን መጠየቅ እንችላለን። መስዋዕተ ቅዳሴ የክርስቶስ የፋሲካ ምስጢር መታሰቢያ ነው። ይህም እርሱ ኃጢኣትን እና ሞትን ድል አድርጎ የመነሳቱ ተካፋዮች እንድንሆን በማድረግ ለሕይወታችን ምልአት ያለው ትርጉም ይሰጠዋል።

ስለዚህም የመስዋዕተ ቅዳሴን ትክክልኛ እሴት በሚገብ መረዳት እንችል ዘንድ በቅድሚያ “መተሳቢያ” የሚለውን ቃል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉሙን መረዳት ይኖርብናል።  በመጸሐፍ ቅዱስ አገላለጽ መታሰቢያ የሚለው ቃል የአለፉ ነገሮች ትውስታ ብቻ ሳይሆን  እግዚኣብሔር ለሰው ልጆች ያከናወናቸው ታላላቅ ሥራዎች እወጃ ጭምር ነው። እነዚህ ሁኔታዎች ደግሞ በሥርዓተ አምልኮአዊ አከባበር የሚከሰቱ እና የሚጨበጡ ይሆናል። እስራኤላዊያ ከግብጽ ባርነት ነጻ የሆጡበትን ሁኔታ የሚገነዘቡት እንዲህ ነው፣ የፋሲካ በዓል በሚከበርበት በማንኛውም ወቅት፣ ሕይወታችውን ከእርሱ አንጻር ያስተካክሉ ዘንድ በስደት የነበሩበትን ሁኔታ ለምዕመናን በትውስታነት ያቀርባሉ (የካቶሊክ ቤ.ክ. ትምህርተ ክርስቶስ 1363)። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በስቃዩ፣ በሞቱ በትንሳኤው እና በእርገቱ አማካይነት ለፋሲካ በዓል ምልአት እንዲኖረው አድርጉዋል። ስለዚህም መስዋዕተ ቅዳሴ እኛን ከኃጢኣት ነፃ ሊያወጣንና በተስፋ ቃል ወደ ዘላለማዊ ህይወት እንዲንገባ ያደረገልን የእርሱ "ተምሳሌት" መታሰቢያ ነው። ይህም መታሰቢያ ብቻ አይደለም፣ በፍጹም! ከሃያ ምዕተ ዓመታት በፊት የተከሰተውን ነገር አሁን እንደ ተከሰተ አድርጎ ማሰብ ነው።

ቅዱስ ቁርባን ሁልጊዜም ወደ እግዚአብሔር ደኅንነት ተራራ እንድንወጣ ያደርገናል፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እራሱን እንደ እንጀራ አድርጎ እንድንበላው ለእኛ በማቅረብ ምሕረቱን፣ ፍቅሩን ልክ በመስቀል ላይ እያለ እንዳደረገው ማለት ነው፡ ሙሉ በሙሉ በእኛ ላይ ያዘንባል፣ በዚህም መልኩ ልባችንን፣ ኑሮዋችንን፣ የአኗኗር ዘይቤያችንን ሳይቀር በማደስ ከእርሱ ጋር እና ከወንድሞቻችን ጋር እንድንቀራረብ ያደርገናል።

እያንዳንዱ መስዋዕተ ቅዳሴ በሚቀደስበት ወቅት ከሞት የተነሳው እና መቼም ቢሆን የማይጠልቀውን የክርስቶስ ኢየሱስን ብርሃንን ያስታውሰናል። መስዋዕተ ቅዳሴን በተለይም ደግሞ በእለተ ሰንበት መሳትፍ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ መሳተፍ፣ በእርሱ ብርሃን መድመቅን ያመጣል። በቅዱስ ቁራባ አማካይነት መነፍስ ቅዱስ የመለኮታዊ ሕይወት ተካፋዮች እንድንሆን በማድረግ ሟቾች እንድንሆን የሚያድርጉንን በሕሪዎቻችንን በመቀየር አዲስ ሰዎች ያደርገናል። ኢየሱስ ከሞት ወደ ዘልዓለም ሕይወት  ያደርገው የመሸጋገሪያ ጉዞ እኛንም ቢሆን በመማረክ የእርሱ ፋሲካ ተካፋዮች እንድንሆን ያደርገናል። መስዋዕተ ቅዳሴ በሚደረግበት ወቅቶች ሁሉ የፋሲካ በዓል ይከበራል። እኛም በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ከሞተው እና ከሙታን በተነሳው ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በመሆን ወደ ዘለዓለም ሕይወት እንድናመራ ይማርከናል። በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ከእርሱ ጋር ሕብረትን እንፈጥራለን፣ ክርስቶስ በእኛ ውስጥ ይኖራል እኛም በእርሱ እንኖራለን ማለት ነው። “ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ፤ ከእንግዲህ እኔ አልኖርም፤ ነገር ግን ክርስቶስ በውስጤ ይኖራል። አሁንም በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን አሳልፎ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለኝ እምነት ነው” ይላል ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ገላቲያ በጻፈው ምልእክቱ 2፡19-20)።

የፈሰሰው የእርሱ ደም ከሞት እና ሞት ከፈጠረብን ፍርሃ ነጻ የወጣናል። ከአካላዊ ሞት ብቻ ሳይሆን ብዙን ጊዜ እኛን ብቻ ሳይሆን ሌሎችን ሰዎች ሳይቀር ወደ ጥፋት ጎዳና እንዲያመሩ ከሚያደርገው ከክፉ ነገር፣ ከኃጢኣት ከመንፈሳዊ ሕይወትም ሞት ነጻ ያደርገናል።

አዎን! አሁን መስዋዕተ ቅዳሴን በምናደርገብት ወቅት የፍሲካን በዓል በመታሰቢያነቱ ብቻ ሳይሆን አሁን፣ በአሁኑ ወቅት እያከበርነው የምንገኝ ወቅታዊ በዓል እንደ ሆነ የገባችሁ ይመስለኛል። የመስዋዕተ ቅዳሴ በክርስቶስ የፋሲካ ምስጢር ተካፋዮች እንድንሆን በማድረግ ከእርሱ ጋር ከሞት ወደ ሕይወት እንድንሻገርም ያደርገናል። መሳዋዕተ ቅዳሴ አንድ ለየት ያለ ትይንት ሳይሆን ኢየሱስ ያለፈበትን ሳቅይ አሁን የምናስታውስበት ምስጢር ነው። አመሰግናልሁ!

 

23/11/2017 15:49