2017-11-17 16:08:00

ቅዱስ ቦናቨንቱራ ላይ ያተኮረ ለዓለም አቀፍ ዓውደ ጥናት የቅዱስነታቸ ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ መልእክት


የቅዱስ በኖናቨንቱራ የቲዮሎጊያና የፍልስፍና ምርምርና ጥናት ወቅታዊነት፥ Deus summe cognoscibilis - በጣም ልቆ ከሁሉም በላይ የሚታወቅ እግዚኣብሔር በሚል ርእስ ዙሪያ የሚወያይ በጳጳሳዊ ግረጎሪያን መንበረ ጥበብ እ.ኤ.አ. ከህዳር 15 ቀን እስከ ህህዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም. ወደ ተከናወነው ዓለም አቀፍ ዓውደ ጥናት ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ መልእክት አስተላልፈው እንደነበር የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞናኮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

በነዲክቶስ 16ኛ ባስተላለፉት መልእክት የዚሁ ዓለም አቀፍ ዓውደ ጥናት መርሐ ግብር የቅዱስ ቦናቨንቱራ ምርምርና ጥናት ምንኛ ጥልቅ እና ሰፊ መሆኑ የሚያስገነዝብ ብሎም በዚህ ለምንኖርበት ወቅታዊ ታሪክ ማናችንም ከሚገምተው በላይ የሚናገር እግዚአብሔር በማወቅ ዙሪያ ለሚደረገው ቲዮሎጊያዊም ይሁን ፍልስፍናዊ ምርምር እና ጥናት በነበረት ዘመን ያመላከተው ህልዮ ወቅታዊነት ያለው መሆኑ የሚያረጋግጥልን ነው እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሎሞናኮ አያይዘው የቅዱስ ቦናቨንቸር ላይ ያተኮረ ቀዳሚው ዓለም አቀፍዊ ዓውደ ጥናት እ.ኤ.አ. በ 1974 ዓ.ም. የተካሄደው ሲሆን ይኽ ሁለተኛው ደግሞ  ቅዱስ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ ቦናቨንቱራ የተወለደበት ስምንት መቶኛው ዓመት በሚዘከርበት ወቅት የተከናወነ ዓውደ ጥናት ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ 48 ምሁራን ያሳተፈ እንደነበርም ገልጠዋል።

የቅዱስ ቦናቨንቱራ ወቅታዊነት

ይህ የ 2017 ዓ.ም. ዓውደ ጥናት የዚያ የመጀመሪያው በ 1974 ዓ.ም. ተካሂዶ የነበረው ዓውደ ጥናት ማእቅፍ ያደረገ ቅዱስ ቦናቨንቱራ በፍልስፍና በቲዮሎጊያ እና በሥነ መንፈሳዊነት ዘርፍ ያመላከታቸው መንገዶች ሁሉ በወቅታዊው ዓለም ተክፋይ የሚያደርገው ለወቅታዊው ፍልፍስናዊ ቲዮሎጊያዊ እና መንፍሳዊ ተግዳሮት የሚናገር ያደርገዋል እንዳሉ ያስታወሱት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሎሞናኮ አያይዘው ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ቅዱስ ቦናቨንቸር “የግልጸት ግንዛቤ እና የታሪክ ቲዮሎጊያ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ሁለተኛው መድብላዊ መጽሓፍ ለመጀመሪያ ጊዜ በጣልያንኛ ቋንቋ የታተመው ለንባብ የበቃበት ዓውደ ጥናት መሆኑም ይጠቁማሉ።

የተካሄደው ዓውደ ጥናት የሦስት መናብርተ ጥበብ ትብብር እውን ያደርገው ሲሆን፡ እንደ መርሐ ግብሩ መሰረትም በመጀመሪያው የዓውደ ጥናት ውሎው፡ ቲዮሎጊያና እና የግልጸት ስልት የሚል፡ የሁለተኛው ቀን ውሎው ደግሞ የዘፍጥረት ቲዮሎጊያና የስነ ክርስቶስ ቲዮሎጊያ የመዝጊያው የሦስተኛው ቀን ውሎው የቅዱስ ቦናቨንቱራ የስነ ቤተ ክርስቲያን ቲዮሎጊያ ህልዮ ርእስ ያደረገ እንደነበርም ሎሞናኮ ጠቅሰው፥ የተካሄደው ዓውደ ጥናት ጳጳሳዊ ግረጎሪያ መንበረ ጥበብ የቲዮሎጊያ ቅዱስ ቦናቨንቹር ሰራፊኩም መንበረ ጥበብ እና ጳጳሳዊ አንቶኒያኑም መንበረ ጥበብ ትብብር ውጤት መሆኑም ገልጠዋል።

የቅዱስ ቦናቨንቸር ሕይወት

ጆቫኒ ፊዳንዛ እ.ኤ.አ. በ 1218 ዓ.ም. በኢጣሊያ በላዚዮ ክፍለ ሃገር ቪተርቦ አውራጃ በሚገኘው ባኞረጆ ወረዳ ተወለደ፥ ብዙ የጤና መታወክ የነበረው እና ከቅዱስ ፍራንቸስኮ ጋር በመገናኘትም ፈውስ ታድሎ ከህመሙ በመላቀቁም ምክንያት ሁኔታውን መልካም እድል (Bona ventura) ሲል ሲገልጠው ይህ መልካም እድል ሲል የተናገረው ቃል ምክንያት ቦናቨንቹራ የሚል መጸውዕ ስም የተሰጠው እንዲሆን እድርጎታል። ለእናቱ ቃል እንደገባው መሠረትም የፍራንቸስካውያን ንኡሳን ማኅበር አባል ሆነ።  እ.ኤ.አ. በ 1257 ዓ.ም. የዚህ ማኅበር ጠቅላይ አለቃ በመሆን እንዳገለገለም የቤተ ክርስቲያን የታሪክ ማሕደር ያወሳል።

ቦናቨንቹራ እ.ኤ.አ. በ 56 ዓመት ዕድሜው በ 1274 ዓ.ም. በሰማያዊ ቤት ተወለደ፡ በ 1588 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ሲስቶ አምስተኛ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ ብለው እንዳወጁለትና Itinerarium mentis in Deum - የአዕምሮ ጉዞ ወደ እግዚአብሔር በሚል ርእስ ሥር የደረሰው ሰው ወደ እግዚአብሔር ያቀና መሆኑና ይኸንን ወደ እግዚአብሔር የሚያደርገው ጉዞ ስድስት እርከኖች እንዳሉት በቲዮሎጊያዊ ፍልስፍናዊ እና ሰቂለ ህሊናዊ የምርምር አማካኝነት የሚተነትን ጥናት ዙሪያ የደረሰው መጽሓፉ በስፋት የሚታወቅ ድረሰቱ እንደሆነም የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሎሞናኮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም በቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 ለሚጠራው የቫቲካን ማኅበር ሊቀ መንበር የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛው ወደ ዓውደ ጥናቱ ያስትላለፉት መልእክት ዙሪያ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ጆሰፍ ራትዚንገር (በነዲክቶስ 16ኛ) በቅዱስ በናቨንቱራ ርእስ ዙሪያ ያደረጉት ጥልቅ ምርምርና ጥናት መሠረት የቅዱሱ ፍልስፍናዊ እና ቲዮሎጊያዊ ጥናት የሚያብራራ ለመናብርተ ጥበብ ትልቅ ማጣቀሻ እና ለጥናት እና ምርምር መሠረት ሊሆን የሚችል የደረሱት መጽሓፍ በቅዱስ ቦናቨንቸር ምርምርና ጥናት ላይ ያላቸው ጥልቅ እውቀት ያመለክትልናል። ዓውደ ጥናቱም በቦናቨንቱራ ዙሪያ በቅርቡ በጣልያንኛ ቋንቋ የታተመው መጽሓፍ ለንባብ የበቃበት ውይይትም ተካሂዶበታል ቅዱስነታቸው በቅዱስ ቦናቨንቱቸር ዙሪያ ሦስት የረቡዓዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሰጥቷል። ለቅዱስ ቦናቨንቱር ያላቸው ትልቅ ፍቅር ምክንያትም እ.ኤ.አ. መሰክረም 9 ቀን 2009 ዓ.ም. በቅዱስ ቦናቨንቸር ከተማ በሆናቸው በባኛረጆ ከተማ ሐዋርያዊ ጉብኝት ኣካሂደው እንደነበር ገልጠው የሰጡት ቃለ መጠይቅ አጠናቋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.