Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ንግግሮች

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ፥ ቤተ ክርስቲያን ሱታፊያዊ ኅብረት በእጅጉ ያስፈልጋታል

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ፥ ቤተ ክርስቲያን ሱታፊያዊ ኅብረት በእጅጉ ያስፈልጋታል - ANSA

17/11/2017 16:05

ዓለም አቀፍ የካህናት ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገግሎት ጥምረት፥  እ.ኤ.አ. ከህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም.  ጀምሮ የካህናት ሚና በአካባቢያዊት ቤተ ክርስቲያን በሚል ርእስ ዙሪያ ያስተነተነው ዓውደ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ህዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ተጋባእያኑን ተቀብለው መለገሱት ምዕዳን መጠናቀቁ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋንቲ አስታወቁ።

ዛሬ በቤተ ክርስቲያን እና በዓለም ውስጥ ኅብረት ከምን ጊዜም በላይ እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡ ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እንዳሉት የሰበካ መፈሳዊነት ያንን በቅድስት ሥላሴ ያለው ኅብረት አብነት ያደረገ የኅብረት መንፈሳዊነት ነው፡ ይህ ተቻይ የሚሆነው ደግሞ ወደ ክርስቶስ በመለወጥ ለመንፈስ ቅዱስ እራስን ምቹ አድርጎ በማቅረብ እና ወንድሞችን በማስተናገድ ብቻ ነው። ስለዚህ ይኽ ሁሉ ተቻይ የሚሆነው ቅዱስ በመሆን ነው የሚለው ጥልቅ ሃሳብ ማእከል ባደረገው ቃለ ምዕዳናቸው፥

ዛሬም እንደ ጥንቱ የፍቱን እና ስኬታማ ወንጌል አብሳሪያን ቅዱሳኖች ናቸው። ምሥጢረ ጥምቀት የተቀበለ ሁሉ ከፍ ላለ፡ ለላቀ የክርስትና ሕይወት የተጠራ ማለትም ለቅድስና የተጠራ ነው፡ እንዲህ ከሆነ ካህናትን በበለጠ ተቀድሰው የሚቀድሱ መሆን እንዳሚገባቸው የማያጠያይቅ ንው። የዓለም የመሆን ጉዳይ ሳስብ፡ የዓለም የመሆን የሚኖር መንፈሳዊነት እርሱም ብዙውን ጊዜ በግትርነት ጠባይ ውስጥ የሚደበቅ ነው፡ የዓለም የመሆን መንፈሳዊነት እና ግትርነት ተያይዘው የሚሄዱ ፈተናዎች ናቸው እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋንቲ አያይዘው፥

እረኞች የተጠሩት የአገልግሎት ፎጣ ታጥቀው ያንን በማኅበረሰባቸው ወይንም በማኅበራቸው የሚኖሩትን፡ በተያያዘ መልኩም ወቅታዊ የሕዝበ እግዚአብሔር ታሪክ ኑሮውን ደስታውን ስቃዩን ሁሉ እንድትገነዘብ የሚያድርግ ጎንበስ ብሎ ለማገልገል ነው፡ ጎንበስ ብሎ ማገልግለል ተጨባጩን ሁነት ትረዳም ዘንድ መሰረት ይሆናል፡ ካህናት የጋራ ወንድማዊ ሕይወት መኖር ይጠበቅባቸዋል። ማለትም በሰበካቸው ባለው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ጉዞ በጋራ ተሳታፊዎች መሆን አለባቸው፡ በሰበካዎች በሚታቀደው በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት እንደየ የኃላፊነቱ ከሰበካው አቡን ጋር ኅብረት በመኖር መሳተፍ አለበት። የሰበካ አቡን ለአንድ ሰበካ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ችላ የማይባል ማጣቀሻ መሆኑ ግድ ነው። በሁሉም የሰበካው የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እቅድ በሁሉም በሰበካው በሚገኙት የተለያዩ ማኅበራት እና እቅስቃሴዎች ሁሉ ግዜ እራሱን ፊተኛ ማድረግ ይጠበቅበታል።

ይኽ የኤጰስ ቆጶሳቱ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ኅብረት የቤተ ክርስቲያን አንድነት፤ ኅብረት፤ ሱታፌነትን ያጸናል። ይህ ኅብረትቤተ ክርስቲያናዊ አኃድነትበአንድ ውሉደ ክህነት ሲዘነጋ ወይንም አልፎ አልፎ በተፋረቅ ሲታይ እጅግ ያሳዝናል። ኅብረት በሌለበት ውሉደ ክህነት ሐሜት ያንሰራፋል፡ ስም የማጠልሸት ተግባር የነገሰበት ይሆናል። አሉ ባልታ፡ መተማማት ሰበካዎችን፡ የውሉደ ክህነት አንድነትን ማለትም በካህናት መካከል ያለው እንዲሁም ካህናቱ ከአቡናቸው ጋር ያላቸውን አንድነት ያወድማል። ብዙውን ጊዜ ዓይኖቻችን መጥፎውን ነገር ለማያት የፈጠኑ እንዲሆን እናዛለን፡ አይኖቻችን መጥፎውን ለማየት ያከቦከቡ ናቸው፡ ቢሆን ግን አደራ ከሐሜትና ስም ከማጠልሸት ትቆጠቡ ዘንድ አምክራችኋለሁ። ምክንያቱን ማማትና ማጠልሸት ግብረ ሽበራ ነው፡ ማሸበር ማለት ነው፡ ስለዚህ አሸባሪያን አንሁን እባካችሁ፡ ሐሜትና አሉባልታ ልክ እንደ አንድ ተወርዋሪ ቦምብ ነው፡ የሚታማውን ሰው የሚገድል ነው። አሉባልታ የቤተ ክርስቲያን የሰበካ ባጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን የአኃድነትን ማእቅፍ ወይንም ኅብረህዋስ የሚወድም ነው።

በዚያ በሐዋርያዊ አገልግሎት ኅብረት ሁሉም ካህናት በጳጳሳቸው ዙሪያ የሚኖሩት ኅብረት የቤተ ክርስቲያን ኅብረት ያጸናል። ያንን የቤተ ክርስቲያን አንድነት ላይ እንድናተኵር የሚደርገን እስትንፋስ ሊኖረን ይገባል። በተለያዩ ክልሎች የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ለመንፈስ ቅዱስ ሥራ ተገዥ እና ታዛዥ በመሆን ለክልሉ ጳጳስ ታዛዥ በመሆን በካህናቶች መካከል ትብብር የሚኖርባት መሆን ግድ ነው፡ ይኽ ታዣዥነትና ትብብርም ያንን ሰበካዎች የአገሮችን አጥር ሰገር የሆነውን የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን አባልነት ይመሰክራል ይኽ ምስክርነትም የኵላዊነት ወገን መሆንህ የተገነዘበ መሆን አለበት። ካህን ወደ ዓለም የሚላክ እንጂ ለዓለዊነት የተላከ አይደለም። ስለዚህ ተልእኮ የእያንዳንዱ መልካም ፈቃደኛነትን እና ለጋስነትት ብሎም ግላዊ ምርጫ ሳይሆን ለሁሉም ሰው ዘር ወንጌልን ለማበሰር ተወናያን የሚያደርግ በክልሎች የምትገኘው ቤተ ክርስቲያን ምርጫ ነው። በማለት ያስደመጡት ንግግር ማጠቃለላቸው ገለጡ።   

17/11/2017 16:05