Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ስብከቶች

መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ያለውን የእግዚኣብሔር መንፈስ እንዲሰፍ ይረዳን ዘንድ መጸለይ ያስፈልጋል።

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት

17/11/2017 15:29

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትንው እለት ማለት በሕዳር 9/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት የእግዚኣብሔር መንግሥት ትርዕት ወይም ራሱን ማስተዋውቅ የሚወድ ነገር አይደለም ማለታቸው ተገለጸ። ቅዱስነታቸው በእለቱ ባላቲን የስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት ከሉቃስ ወንጌል ከምዕራፍ 17፡20-25 ላይ ተወስዶ በተነበበው እና ፈሪሳዊያን የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ነው የሚመጣው ብለው ኢየሱስን በጠየቁት ጥያቄ ዙሪያ ላይ በመመርኮዝ በዳረጉት ስብከት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት የእግዚኣብሔ ምንግሥት እንዲሰፋ የሚያደርገው እኛ የምናወጣው ሐዋሪያዊ እና መንፈሳዊ የሆኑ ተገባራትን የማከናወኛ እቅዶቻችን ላይ ተመስርቶ ሳይሆን  ነግር ግን የእግዚኣብሔር መንግሥት እንዲሰፋ የምያደርገው ዋንኛው ነገር መንፈሥ ቅዱስ ነው ብለዋል።

የዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከዚህ አታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

የእግዚኣብሔር ምንግሥት መቼ ነው የሚመጣው? የሚለው ጥያቄ በጣም ቀለል ያለ እና ከልብ የመነጨ በወንጌል ወስጥ ብዙ ጊዜ ተጠቅሶ የምናገኘው ቃል ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንም አሳባቸውን ለማጽናት በማሰብ አጥማቂው ዩሐንስ በእስር ቤት በነበረበት ወቅት ደቀ መዛሙርቱን ወደ ኢየሱስ ልኮ ይመጣል የተባለው አንተ ነህ ወይስ ሌላ እንጠብቅ ብሎ መልእክት ልኮ እንደ ነበረ በዋቢነት ጠቅሰዋል። በተመሳሳይ መልኩም መልኩን ቀየር ባደረገ መልኩ ኢየሱስ በመስቀል ላይ በነበረበት ወቅት “አንተ የእግዚኣብሔር ልጅ ከሆንክ  እስቲ ከመስቀል ላይ ውረድ” በማለት በመስቀሉ ሥር የነበሩ ሰዎች ኢየሱስን ያስጨንቁት እንደ ነበረ አውስተው ይህም የእግዚኣብሔርን መግሥት መምጣት በተመለከተ ሁል ጊዜ ቢሆን ጥርጣሬ ወይም ጉጉት በሰዎች ዘንድ እንዳለ ያሳያል ብለዋል።

ነገር ግን ኢየሱስ “የእግዚኣብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ነው” በማለት ለዚህ ዓይነቱ ጣያቄ ቀለል ያለ መልስ ስጥቶ እንደ ነበረ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ይህም ኢየሱስ በምኩራብ ውስጥ ተገኝቶ ከትንቢተ ኢሳያስ መጽሐፍ ውስጥ “ይህ ነገር ዛሬ ተፈጸመ” በማለት ማረጋገጫ ስጥቶ እንደ ነበረም ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

አንድ የተዘራ ዘር በቆልት ማውጣት የሚጀምረው ከውስጡ እንደ ሆነ ሁሉ የእግዚኣብሔር ምንግሥትም እንዲሁ በመካከላችን ተደብቆ ይገኛል” ያሉት ቅዱስነታቸው “እንደ አንድ ወድ እቃ ወይም በቆልት” ትህታናን በተላበሰ መልኩ ተደብቆ የሚገኝ መሆኑንም ጨምረ ገልጸዋል።

“ታዲያ ይህ ዘር እንዲበቅልና እንዲያድግ የሚያድርገው ማነው”? በማለት ጥያቄን በማንሳት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው  በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በውስጣችን በሚገኘው በእግዚኣብሔር ኃይል መሆኑን ገልጸው መንፈስ ቅዱስ የትህትና፣ የየዋህነት፣ የታዛዥነት መንፈስ እንደ ሆነም አብራርተው በውስጣችን የሚገኘውን የእግዚኣብሔር ምንግሥት እንዲያድግ የሚያደርገው ይሄው መንፈስ ቅዱስ ነው ብለዋል። ስለዚህም ነው በውስጣችን የሚገኘውን የእግዚኣብሔር መንግሥት እንዲያድግ የሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ እንጂ እኛ የምናወጣቸው ታላላቅ ሊባሉ የሚችሉ የሐዋሪያዊ እና የመንፈሳዊ ተግባራትን የማከናወኛ እቅዶቻችን አይደሉም የምላችሁም በዚሁ ምክንያት ነው ያሉት ቅዱስነታቸው የሚያሳድገው እና ጊዜው ሲደርስ ፍሬ እንዲያፈራ የሚያደርገው የእግዚኣብሔር መንፈስ ብቻ ነው በማለት በጽኖት ገልጸዋል።

ዛሬ በተነበበልን ቅዱስ ወንጌል ውስጥ ኢየሱስ ““የእግዚአብሔር መንግሥት በሚታዩ ምልክቶች አትመጣም፤ ሰዎችም፣ ‘እዚህ ነው’ ወይም ‘እዚያ ነው’ ማለት አይችሉም፤” በማለት መልሶ እንደ ነበረ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው  የእግዚአብሔር መንግሥት በኩራት ለሰዎች የምናሳየውና በማስታወቅያ መልኩ የሚቀርብ ነገር ሳይሆን በጣም ትሁት እና በድብቅ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት  የሚበቅል እና የሚያድግ መሆኑን ቅዱስነታቸው አስምረውበታል።

እኛ ሁላችን ይህንን የእግዚኣብሔር መንግሥት መንገድ የጥሪ መንገዳችን አድርገን ልንከተለው ይገባል፣ ይህም ለእኛ ፀጋ እና እግዚኣብሔር ለእኛ በነጻ የሚሰጠን ስጦታ መሆኑን ማወቅ እንደ ሚገባን ገልጸው እኛ በምስጢረ ጥምቀት የተዋጀን ሁላችን በውስጣችን መንፈሥ ቅዱስ ይገኛል ታዲያ ከዚህ በውስጣችን ከሚገኘውና የእግዚኣብሔር መንግሥት እንዲሰፋ ከሚያድርገው መንፈስ ቅዱስ ጋር ያለን ግንኙነት ምን ይመስላል? በማለት ጥያቄን አንስተዋል። ይህም ዛሬ እኛ ራሳችንን ልንጠይቅ የሚገባን ትልቁ ጥያቄ መሆን እንደ ሚገባው የጠቀሱት ቅዱስነታቸው በእውነት የእግዚኣብሔር መንግሥት በውስጣችን እንዳለ እናምናለን ወይ? በማለት መጠየቅ ይገባናል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማብቂያ ላይ እንደ ገለጹት መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥም ሳይቀር ተደብቆ የሚገኘውን የእግዚኣብሔር መንግሥት እንዲያድግ እና ትልቅ ዛፍ ሆኖ ለሌሎች መጠጊያ መሆን እንዲችል እንዲረዳን መጸለይ ይገባናል ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ቃለ እግዚኣብሔር አጠናቀዋል።

 

17/11/2017 15:29