Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስና የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ባደረጉት የጠቅላላ አስተምህሮ " መስዋዕተ ቅዳሴ ከሁሉ የሚበልጥ ትልቁ ጸሎት ነው" አሉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ - ANSA

15/11/2017 14:13

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በተለያዩ አርእስቶች ዙሪያ የትምህርተ ክርስቶ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። ከዚህ ቀደም ባሉት ጊዜያት ማለትም ከሁለት ሳምንታት በፊት በተከታታይ ያደርጉት የነበረው አስተምህሮ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው የክርስቲያን ተስፋ በሚል ጭብጥ ዙሪያ ላይ ያጠነጠነ እንደ ነበረ በስፋት መግለጻችን የሚታወቅ ሲሆን፣ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ደግሞ በመስዋዕተ ቅዳሴ ዙሪያ ላይ ትኩረቱን በማድረግ በተለይም ደግሞ በቅዱስ ቁርባን ምስጢር ዙሪያ ላይ ጠነጠነ አስተምህሮ በተከታታይ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

የዚህን ዝግጅት ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

የዚህ መርሃግብር አንዱ አካል በሆነ የዛሬው እለት ማለትም በሕዳር 6/2010 ዓ.ም. ያደረጉት የጠቃላላ አስተምህሮ በመስዋዕተ ቅዳሴ ዙሪያ ባለፈው ሳምንት ካደረጉት አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረ የታወቀ ሲሆን መስዋዕተ ቅዳሴ በጣም ትልቅ ከሁሉም በላይ የሆነ ጸሎት ነው በማለት አክለው ገልጸዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እን የሀገር ጎብኚዎች ያደረጉትን የጠቅላላ አስተምህሮ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

የቅዱስ ቁርባንን ማራኪነት እና ውበቱን ለመረዳት፣ ይህንንም በጣም ቀለል ባለው ሁኔታ ለመግለጽ በማሰብ እንዲህ በማለት እጀምራለሁ፡ መስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ነው፣ በእርግጥም ከሁሉም የሚበልጥ፣ የልዕልና፣ ግርማ ሞገስ የተሞላ ጸሎት ነው፣ በተመሳሳይ መልኩም በጣምተጨባጭ” የሆነ ጸሎት ነው። በዚህም የተነሳ መስዋዕተ ቅዳሴ በእርግጥ ከእግዚኣብሔር ፍቅር ጋር በቃሉ፣ በክርስቶስ ሥጋ እና በደም የምንገናኝበት ምስጢር ነው።

ነገር ግን አንድ ጥያቄ በእርግጠኛነት መመለስ ይኖርብናል።  ጸሎት ምን ማለት ነው? ጸሎት ከእግዚኣብሔር ጋር መወያየት ማለት ነው፣ ከእግዚኣብሔር ጋር የግል ግንኙነት መፍጠር ማለት ነው። የሰው ልጅ የተፈጠረው ከእርሱ ጋር መገናኘት እንዲችል በመሆኑ የተነሳ ምልዐት ያለው ግንኙነት ደግሞ ልኖረው የሚችለው ከፈጣሪው ጋር ሲገናኝ ብቻ ነው።

የኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ የሰው ልጅበእግዚኣብሔር መልክ እና አምሳል” እንደ ተፈጠረ ያረጋግጥልናል፣ በዚህም አብ እና ወልድ እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ ፍጹም በሆነ ፍቅር ሕብረት ፈጥረዋል። ከዚህም እኛ ሁላችን የተፈጠርነው ፍጹም በሆነ ፍቅር ዝምድናን እንድንፈጥር መሆኑን በመረዳት በዚህም መልኩ እርስ በእርስ በመሰጣጣት እና በመቀባበል ሕልውናችንን ምልዕት የተሞላው እንዲሆን ማድረግ ይኖርብናል።

ሙሴ ቁጥቋጦ በመቃጠል ላይ በነበረበት ወቅት የእግዚኣብሔርን ጥሪ በሰማ ጊዜ የጠራው አካል ማን እንደ ሆነ በጠየቀው ወቅትእኔ፣ ያለሁና የምኖር ነኝ” (. ዘጸዐት 3:14) በማለት ምላሽ ሰጥቶት ነበረ። ይህ አባባል የእግዚኣብሔርን በእዛ ሥፍራ መኖር በማረጋገጥየአባቶቻችሁ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ የሆነው እግዚአብሔርበማለት በመቀጠልም በተመሳሳይ መልኩም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን በጠራበት ወቅት ከእርሱ ጎን እንዲሆን አስስቡዋቸው ነበር። ይህም ከሁሉም የሚበልጥ ፀጋ ነው፡ ቅዱስ ቁራባን ከኢየሱስ ጋር በመሆን በእርሱ አማክይነትም ከእግዚኣብሔር እና ከወንድሞቻችን ጋር ግንኙነታችንን የምናጠናክርበት ምስጢር በመሆኑ እድለኞች እንድንሆን ያደርገናል።

መጸለይ ማለት እንደ ማንኛውም ውይይት፣ በጸጥታ መከታተል ማለትም ነው፣ ከኢየሱስ ጋር በዝምታ የምንሆንበት ጊዜ ሊሆንም ይገባል። ከዚህ ምስጢራዊ ከሆነው የእግዚኣብሔር ዝምታ ውስጥ በልባችን ውስጥ የሚመላለስ ወይም የሚብሰለሰል ቃል ይፈልቃል። በእርግጥ  ከእግዚኣብሔር ጋር እንዴት  መሆን እንደ ምንችል ኢየሱስ በጸሎቱ ያስተምረናል። ቅዱስ ወንጌል ኢየሱስ ብቻውን ለመጸለይ እንደ ሄደ ይነግረናል፣ ደቀ መዛሙርቱም ይህ ኢየሱስ ከአባቱ ጋር ያለው ጥብቅ የሆነ ግንኙነት በማየት፣ በዚህም መልኩ እነርሱም የመሳተፍ ምኞት ስላደረባቸውጌታ ሆይ! መጸለይ አስተምረን!” (ሉቃስ 111) በማለት ይጠይቁታል። ኢየሱስም ጸሎት ለማድረግ ከሁሉም በቅድሚያ አባት ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ ማወቅ እንደ ሚኖርባቸ ገልጾ ይህም የልጅነት መንፈስ በውስጣቸው በእርግጠኛነት እንዲኖር ስለ ሚረዳ መሆኑ ነግሮዋቸው ነበር። ነገር ግን ይህንን ለመማር ትህትና በተሞላው መልኩ ይህንን ልያስተምረን የሚችል መሪ እንደ ሚያስፈልገን በማወቅ አሁንም በትህትና ጌታ ሆይ! መጸለይ አስተምረንብለን ልንጠይቀው ይገባል።

ትህትናን መላበስ፣ የእርሱ ልጆች መሆናችንን መረዳት፣ በእግዚኣብሔር አብ እቅፍ ውስጥ ገብቶ ማረፍ፣ በእርሱም መተማመን የሚሉት በቀዳሚነት ሊቀመጡ የሚገባቸው ነጥቦች ናቸው። ወደ እግዚኣብሔር መንግሥት ለመግባት ከፈለግን ራሳችንን እንደ ሕጻናት የዋሕ አድርገን ማቅረብ ይኖርብናል። ይህንንም መረዳት የሚኖርብን ሕጻናት መተማመን ይችሉበታል፣ ምን እንደ ሚበሉ፣ ምን እንደ ምለብሱ እነዚህን እና እነዚህን የምሳስሉ ነገሮችን የሚያሟላላቸው ሌላ ሰው ስለእነርሱ እንደ ሚጨነቅላቸውም በሚገባ ይገነዘባሉ።  ሕጻናት በቤተሰቦቻቸው ላይ ያላቸውመተማመንንበማነጻጸር እግዚአብሔር  ሁል ጊዜም ቢሆን እንደ ሚያስታውሰን  እና እኛን እንደ ሚንከባከበን ማወቅ የሚለው በቀዳሚነት ሊኖረን የሚገባ ባሕሪ ነው።

በመቀጠልም ልክ እንደ ሕጻናት ሊኖረን የሚገባው ዝንባሌ መደነቅ የሚለው ባሕሪ ሊኖረን ያስፈልጋል። ሕጻናት ሁል ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ጥያቄዎችን በማቅረብ ዓለምን ለማወቅ ይጥራሉ፣ ሁሉም ነገር ለእነርሱ አዲስ ስለሚሆንባቸው ትንሽ ነገር ባወቁ ቁጥር በጣም ይደነቃሉ። ወደ እግዚኣብሔር መንግሥት ለመግባት ከፈለግን ሁልጊዜም ቢሆን መደነቅ ይኖርብናል። ከጌታ ጋር ያለን ግንኙነትና ጸሎት እንድንገረም ወይም እንድንደነቅ አድርጎን ያውቃል ወይ? ምክንያቱም ከእግዚኣብሔር ጋር የሚደረግ ማንኛውም ግንኙነት አዲስ በመሆኑ የተነሳ ልያስገርመን ወይም ልያስደንቀን ይገባል።

ቅዱስ ወንጌላችን አንድ ኒቆዲሞስ የሚባል በእድሜ የገፋ፣ ስልጣን የነበረው እስራሄላዊ ሰው ኢየሱስን ለማወቅ ፈልጎ ወደ እርሱ መሄዱን እና ኢየሱስም ባየ ወቅትበድጋሚ መወለድ እንደ ሚኖርበት (ዩሐንስ 31-12) ይተርክልናል።  ነገር ግን ይህዳግም መወለድየሚለው ቃል ምን ማለት ነው? ትክክለኛውን መንገድ፣ ደስታ፣ አስገራሚ የሕይወት ገጽታን ለመያዝ መመለስ ይችላል ወይ? ይህም የእመንታችን መስረታዊ ጥያቄ እና የእያንዳንዱ እውነተኛ የሆነ ምዕመን ፍላጎት ነው፣ እንደ ገና የመወለድ ምኞት፣ ሕይወትን በአዲስ መልኩ የመጀመር ደስታ፣ የእያንዳንዱ ምዕመን ፍላጎት እና ምኞት ነው።  እናንተስ ይህ ምኞት አላችሁ ወይ? በእርግጥ ይህን ፍላጎት በቀላሉ ማጣት እንችላለን ምክንያቱም በእየቀኑ ብዙ የሆኑ የተለያዩ ተግባራትን በመፈጸም ስለምንውል፣ ተግባራዊ ማድረግ የሚገባን ብዙ እቅዶችም ስላሉን በእነዚህ እና እነዚህን በመሳሰሉ ምክንያቶች በጣም ጥቂት የሚባል ጊዜ ብቻ ስላለን እና በሕይወታችን ውስጥ በጣም መሰረታዊ የሆነውን መንፈሳዊ ሕይወታችንን ስለምንረሳም ነው።

በእውነት ደካሞች መሆናችንን እያወቀም እንኳን ስለሚወደን ጌታችን ሁል ጊዜ በዚህ ተግባሩ እንድንደነቅ ያደርገናል።ኢየሱስ ክርስቶስ  የኀጢአታችን ማስተስረያ ነው፤ ይኸውም ለዓለም ሁሉ ኀጢአት እንጂ ለእኛ ብቻ አይደለም” (1 ዩሐንስ 22) ይህ ጸጋ እውነተኛ የመጻንኛችን ምንጭ ነው፣ ይህም በቅዱስ ቅርባን አማክይነት ለእኛ ተሰቶናል፣ በዚህም ሙሽራው ባዘጋጀው ግብዣ ላይ በሚሆነበት ወቅት ሙሽራው ደካሞች የሆንን እኛን በመገናኘትበእግዚኣብሔር መልክ እና አምሳልወደ ተፈጠርንበት  ቀደም ሲል ወደ ተጠራንበት ሥፍራ ይወስደናል። ይህንንም የሚያደርገው በቅዱስ ቁራብን አማካይነት ነው፣ ይህም ትልቁ ጸለት ነው።

 

15/11/2017 14:13