2017-11-13 15:07:00

ከጌታ ጋር ለመገናኘት የምናደርገው ዝግጅት በእመንት ላይ የተመሰረተ ብቻ ሳይሆን፣ በፍቅር የሞላበት ሕይወት በመኖርም ጭምር ነው


ርዕሰ ሊቃን ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር እሁድ በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ አስተንትኖ እንደ ሚሰጡ ያትወቃል። የዚህ መረሃ ግብር አንዱ አካል በሆነው የትላንትናው እለት ማለትም የሕዳር 3/2010 ዓ.ም. የቅዱስ ወንጌል አስተምህሮዋቸው ትኩረቱን አድርጎ የነበረው በእለቱ በላቲን የስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት ከማቴዎስ ወንጌል 25:1-13 ላይ ተወስዶ የተነበበው እና የዐስር ልጃገረዶች ምሳሌ ዙሪያ ላይ ያጠነጠነ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያደረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የዛሬ ሰንበት ቅዱስ ወንጌል (ማቴዎስ 25:1-13) ወደ እግዚኣብሔር መንግሥት ለመግባት መድረግ የሚጠበቅብንን ቅደመ ሁኔታዎችን ይጠቁማል። ይህንንም ሙሽራውን የመቀበል ኃላፊነት የተጣለባቸውን እና በዚያን ዘመን የሰርግ ስነ-ስረዓት ይካሄድ የነበረው በማታ በመሆኑ የተነሳ ኩራዛቸውን ይዘው በማታ የወጡትን ዐስር  ልጃገረዶች ምስሌ በመጥቀስ ያስረዳል።

የዛሬ የወንጌል ምሳሌ ከእነዚህ አዐሥሩ ሴቶች መካከል 5 አስተዋዮች አምስቱ ደግሞ ዝንጉዎች መሆናቸውን በመገልጽ፣  ዝንጉዎቹ መብራት ይዘው መጠባበቂያ ዘይት አልያዙም ነበር። አስተዋዮቹ ግን ከመብራታቸው ጋር መጠባበቂያ ዘይት በማሰሮ ይዘው ነበር። ሙሽራው በዘገየ ጊዜ፣ ሁሉም እንቅልፍ ተጫጫናቸውና ተኙ። እኩለ ሌሊት ላይ፣ሙሽራው እየመጣ ነው፤ ወጥታችሁ ተቀበሉት!’ የሚል ጥሪ ተሰማ።

በዚህን ጊዜ ልጃገረዶቹ ሁሉ ተነሥተው መብራቶቻቸውን እየተረኰሱ መዘጋጀት ያዙ። ዝንጉዎቹ አስተዋዮቹን፣መብራታችን ሊጠፋብን ስለ ሆነ፣ ከዘይታችሁ ስጡንአሏቸው። “አስተዋዮቹ ልጃገረዶች ግን መልሰው፣ያለን ዘይት ለእኛም ለእናንተም ላይበቃ ስለሚችል፣ ሄዳችሁ ከሻጮች ለራሳችሁ ግዙአሏቸው።ዘይት ሊገዙ እንደሄዱ፣ ሙሽራው መጣ፤ ተዘጋጅተው የነበሩት ልጃገረዶችም ወደ ሰርጉ ግብዣ አብረውት ገቡ፤ በሩም ተዘጋ።ዘግየት ብለው ሌሎቹ ልጃገረዶች መጥተው፣ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤ በሩን ክፈትልንአሉ። “እርሱ ግን መልሶ፣እውነት እላችኋለሁ፣ አላውቃችሁምአላቸው።

በዚህ ምሳሌ ኢየሱስ እኛን ምን ማስተማር አስቦ ነበር? እርሱን ለመገናኘት ሁል ጊዜ ተዘጋጅተን መኖር እንዳለብን ያስተምረናል። ብዙን ጊዜ ኢየሱስ በወንጌል ውስጥነቅታችሁ ጠብቁ” ይለናል፣ እንዲሁም ዛሬ በዚህ የዐሥሩ ልጃገረዶች ምሳሌ ማብቂያ ላይምእንግዲህ ቀኑን ወይም ሰዓቱን ስለማታውቁ ተዘጋጅታችሁ ጠብቁበማለት ያሳስበናል። በዚህ ምሳሌ ነቅታችሁ ጠብቁ የሚለው ቃል እንቅልፍ አለመተኛት ማለት ብቻ አይደለም ነገር ግን ተዘጋጅቶ መጠበቅ ማለት ነው እንጂ። በእርግጥ እነዚህ ዐሥር ልጃገረዶች  ሙሽራው ከመምጣቱ በፊት ሁሉም ተኝተው ነበረ፣ ነገር ግን ሙሽራው በመጣበት ወቅት ገሚሱ ነቅተው ተዘገጅተው ይጠበቁ ነበረ፣ ገሚሱ ደግሞ ነቅተዋል ግን ዝግጁ አልነበሩም። እዚህ ጋር ነው እንግዲህ አስተዋይ እና ጠንቃቃ ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ ከዚህ መረዳት እንችላለን፣ ይህም ከእግዚኣብሔር ፀጋ ጋር የምንተባበረው በመጨረሻው የሕይወታችን ሰዓት ላይ መሆን እንዳልሆነ ነገር ግን ከአሁኑ መጀመር እንደ ሚገባን ያስገነዝበናል።

በምሳሌ ውስጥ የተጠቀሰው መብራቱ የሕይወታችንን ብርሃን የሚያበዛው የእምነት ምልክት ሲሆን ዘይት ተብሎ የተጠቀሰው ደግሞ የበጎ አድራጎት ምልክት ተምሳሌት ሲሆን ይህም እምነታችን ፍሬያማ እና ታማዕኒ እንዲሆን ያደርገዋል። ከጌታ ጋር ለመገናኘት የምናደርገው ቅድመ ዝግጅት በእመንት ላይ የተመሰረተ ብቻ ሳይሆን፣ እርስ በርስ ፍቅር የሞላበት ክርስቲያናዊ ሕይወት በመኖርም ጭምር ሊሆን ይገባል። ለኛ የሚስማማን እና ምቾት የሚሰጡን ነገሮች በመከተል የራሳችንን ፍላጎቶች እና ጥቅሞች ብቻ በማሳደድ በምንሯሯጥበት ወቅት ሁሉ ሕይወታችን መካን ይሆናል፣ ለእምነታች ብርሃን የሚሰጠውን ዘይት የማከማቻ ሰዓት እናጣለን፣ ስለዚህ እመነታችን መብራት ጌታ ከመምጣቱ በፊት ይጠፋል ማለት ነው። ነገር ግን በተቃራኒው ነቅተን የምንጠብቅ ከሆንን እና መልካም ተግባራትን እያከናወንን የምንኖር ከሆንን፣ ይህንንም በፍቅር፣ ካለን ባማካፈል፣ በችግር ውስጥ የሚገኙትን ባልንጀሮቻችንን በማገዝ የምንኖር ከሆንን ግን ሙሽራው በሚመጣበት ሰዓት ተረጋግተን መቀበል እንችላለን፣ ጌታ እኛ ባልጠበቅንበት ሰዓት ሊመጣ ይችላል፣ ሞትም እንኳን ሊወስደን በሚመጣበት ሰዓት ምንም ነገር አያስፈራንም፣ ምክንያቱም መጠባበቂያ የሆነ ዘይት ስለያዝን ነው ይህም በመላካም ተግባራችን ያጠራቀምነው በእየቀኑ ያከናወነው መልካም ሥራችን ከእኛ ጋር ስለሚኖር ነው።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም እምነታችንን ሁል ጊዜ በመላክም ተግባራት የታጀበ እንዲሆን ትርዳን ምክንያቱ የእኛ የእምነት ብራሃን እዚሁ በምድራዊ ሕይወታችን እያለን በደንብ እንዲበራ እና ከዚያም ቡኃላ ደግሞ በመግሥተ ሰማይ ሙሽራው በሚያዘጋጀው ድግስ ላይም እንዲያበራ ትርዳን አሜን!

 








All the contents on this site are copyrighted ©.