Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ቤተ ክርስትያን \ ኢትዮጵያ

የዘመነ ጽጌ 6ኛ ሰንበትን የሕዳር 3 እለተ ሰንበት ቃለ እግዚኣብሔር በክቡር አባ ግርማቸው ተስፋዬ

የዘመነ ጽጌ 6ኛ ሰንበትን የሕዳር 3 እለተ ሰንበት ቃለ እግዚኣብሔር በክቡር አባ ግርማቸው ተስፋዬ - RV

11/11/2017 13:21

የዘመነ ጽጌ 6 ሰንበትን የሕዳር 3 እለተ ሰንበት ቃለ እግዚኣብሔር እና አስተንትኖ በክቡር አባ ግርማቸው ተስፋዬ በኢትዮጲያ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካህን

 

ወደ ሮሜ 11:13-14

ተመልሰው እስከማይድኑ ድረስ ተሰናከሉን? ብዬ እንደ ገና እጠይቃለሁ፤ ከቶ አይደለም፤ ይልቁንም እስራኤልን ለማስቀናት ሲባል በእነርሱ መተላለፍ ምክንያት ድነት ለአሕዛብ መጥቶአል። ነገር ግን የእነርሱ መተላለፍ ለዓለም በረከት ከሆነ፣ ውድቀታቸውም ለአሕዛብ በረከት ከሆነ፣ ሙላታቸውምን ያህል ታላቅ በረከትያመጣ ይሆን? አሕዛብ ሆይ፤ ለእናንተ እናገራለሁ፤ የአሕዛብ ሐዋርያ እንደ መሆኔ መጠን አገልግሎቴን በትጋት እፈጽማለሁ፤ 14ይኸውም የገዛ ወገኖቼን እንዲቀኑ አነሣሥቼ ከእነርሱ ጥቂቱን ለማዳን ተስፋ በማድረግ ነው። 

የዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘተ ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ራዕ 12:13-18

 

ዘንዶው ወደ ምድር እንደተጣለ ባየ ጊዜ፣ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት። ሴቲቱም በበረሓ ወደ ተዘጋጀላት ስፍራ በርራ መሄድ እንድትችል ሁለት የታላቁ ንስር ክንፎች ተሰጣት፤ ይህም የሆነው በዚያ ከእባቡ ፊት ርቃ ለአንድ ዘመን፣ ለዘመናትና ለዘመን እኩሌታ በክብካቤ እንድትኖር ነው። እባቡም ሴቲቱ በጐርፍ ተጠራርጋ እንድትወሰድ፣ እንደ ወንዝ ያለ ውሃ ከአፉ ተፋ። ምድር ግን ሴቲቱን ረዳቻት፤ አፏንም ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠች። ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጣ፤ ከቀሩት ልጆቿም ጋር ሊዋጋ ሄደ፤ እነርሱ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁና የኢየሱስን ምስክር አጥብቀው የያዙ ናቸው።

 

የማቴዎስ ወንጌል

 

“ሌላም ምሳሌ ስሙ፤ አንድ የወይን ዕርሻ ባለቤት ነበረ፤ በዕርሻው ዙሪያ አጥር አጠረ፤ ለወይኑ መጭመቂያ ጕድጓድ ቈፈረ፤ ለጥበቃ የሚሆን ማማ ሠራ፤ ከዚያም ዕርሻውን ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።የመከር ወራት ሲደርስ፣ ፍሬውን ለመቀበል አገልጋዮቹን ወደ ገበሬዎቹ ላካቸው።

“ገበሬዎቹም አገልጋዮቹን ይዘው አንዱን ደበደቡት፤ ሌላውን ገደሉት፤ ሌላውን ደግሞ በድንጋይ ወገሩት። እርሱም ከፊተኞቹ የሚበልጡ ሌሎች አገልጋዮቹን ላከ፤ ገበሬዎቹም ተመሳሳይ ድርጊት ፈጸሙባቸው። በመጨረሻም፣ ‘ልጄን ያከብሩታል’ በማለት ልጁን ላከ። “ነገር ግን ገበሬዎቹ ልጁን ባዩት ጊዜ፣ ‘ይህማ ወራሹ ነው፤ ኑ፣ እንግደለውና ርስቱን እንውረስ’ ተባባሉ። ይዘውም ከወይኑ ዕርሻ ውጭ አውጥተው ገደሉት።

“ታዲያ የወይኑ ዕርሻ ባለቤት ሲመጣ እነዚያን ገበሬዎች ምን የሚያደርጋቸው ይመስላችኋል?” እነርሱም፣ “እነዚያን ክፉዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎ ከወይኑ ዕርሻ ተገቢውን ፍሬ በወቅቱ ለሚያስረክቡት ለሌሎች ገበሬዎች ያከራያል” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈውን አላነበባችሁምን? አላቸው፤

“ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣

የማእዘን ራስ  ወይም የማእዘን ድንጋይ ሆነ፤

እግዚአብሔር ይህን አድርጎአል፤

ሥራውም ለዐይናችን ድንቅ ነው።’

“ስለዚህ እላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ተወስዳ ፍሬዋን ለሚያፈራ ሕዝብ ትሰጣለች፤ በዚህ ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይሰባበራል፤ ድንጋዩ የሚወድቅበት ሰው ግን ይደቅቃል።” አንዳንድ ቅጆች ቍጥር  የላቸውምየካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ምሳሌዎቹን በሰሙ ጊዜ፣ ስለ እነርሱ የሚናገር መሆኑን ዐወቁ። ነገር ግን ይዘው ሊያስሩት ቢፈልጉም ሕዝቡ ኢየሱስን እንደ ነቢይ አድርጎ ይመለከት ስለ ነበር ፈሩ።

 

የሕዳር 3 እለተ ሰንበት ቃለ እግዚኣብሔር እና አስተንትኖ በክቡር አባ ግርማቸው ተስፋዬ በኢትዮጲያ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካህን

የእለቱ ምንባባት

  1. < > 11,13-14< >  1213-18< >  . 111-11< > 2133-46

በክርሰቶስ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ዛሬ እንደ ቤተክርስቲያህናችን አቆጣጠር የዘመነ ጽጌ 6ኛ ሰንበትን እናከብራለን ፡፡ በዚህም ዕለት ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በተነበቡት ንባባት አማካኝነት ለእያንዳንዳችን የሚሆን የሕይወት ስንቅ ይሰጠናል የሕይወት ምግብ ይመግበናል፡፡

በዚህ በመጀመሪያ ንባብ እንደሰማነው ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ በመጀመሪያ በሐዋርያነቱ አረማውያንን ለማገልገል ቢሆንም በአጠቃላይ ለአይሁዳውያን መዳን ያስብና ይጨነቅ በእነርሱም መዳን ተስፋ ያደረግ ነበር፡፡ ምክንያቱም በመጀመሪያ ወንጌል የተሰበከው ለአይሁዳውያኑ ቢሆንም እነርሱ ግን ይህንን ወንጌል ባለመቀበላቸው ምክንያት ይህ ወንጌል ወደ አረማውያን ተሰበከ እነርሱም ወንጌልን ተቀበሉ በጌታችን እየሱስ ክርስቶም አምነው ተጠመቁ፡፡

በዚህ በመጀመሪያው ንባብ ላይ እንደተመለከትነው ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ  አይሁዳውያን አሁን ወንጌልን ባለማመናቸው የአምላክን አንድያ ልጅ ባለመቀበላቸው ቢሳሳቱም፡ የእነርሱ መሠረት ልክ በምሳሌ እንደገለፀው ቅዱሳኖች ነበሩ፡፡ እስራኤላውያን እንደ ባሕላቸው የመጀመሪያ የሆነውን ማንኛውንም ነገር ለእግዚብሔር መሥዋት የሚቀርብ ቅዱስ ሆኖ እንደሚቆጠረው የተረፈውም ሁሉ ቅዱስ እንደሆነ አድርገው ያስቡ ነበር፡፡

ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ  እንደሚለው ከአንድ የተቦከ ሊጥ ተቆንጥሮ የተጋገረ ዳቦ ቅዱስ እንደሆነ ከዛ ሊጥ የተጋገረ ደቦ ሁሉ ቅዱስ ነው፡፡ እንዲሁም የእነዚህ የእስራኤላውያን የቀድሞ አባቶች ቅዱሳን እንደነበሩ እንዲሁም ከእነርሱ የሚመጡ ዘሮች ሁሉ ምንም እንኳን ባለማመናቸው ቢኮነኑም መሠረታቸው ግን በቅዱሳኖች የዘር ሃረግ የበቀለ ነው፡፡

እንግዲህ በዚህ አነጋገር እንደምንረዳው በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረ ሀሉ ቅዱስ ከሆነው ከእግዚአብሔር የሚጋራው ነገር አለና ሁላችንም ቅዱሳኖች ነን፣ ነገር ግን ይህንን ቅድስናችንን ጠብቀን ይዘን ልንጓዝ ይገባል በእንዲህ አኳሃን የምንጓዝ ከሆነ የእግዚአብሔር ርህራኄ ሁልጊዜም ከእኛ ጋር ይሆናል፡፡ ይህንን ቅድሳናችንን ይዘን የማንጓዝ ከሆነ ምንም እንኳን የእግዚአብሔር ርኀራኄ  ከእኛ ጋር ቢሆንም ይህ በላያችን ያለን ርኀራኄ ልንረዳው እንችልም፡፡   

ሰው ቅድስናውን ይዞ እንዳይጓዝ ሰይጣን ሌት ተቀን እንደሚሰራ መዘንጋት የለብንም በዬሐንስ ራዕይ 12፡13-18 እንደተጠቀሰው ሰይጣን ሴቲቱን ለመጉዳት ባለመቻሉ ከልጆቹ ጋር ጦርነት ለማድረግ ሄደ ይላል፡፡ እንግዲህ የሴቲቱ ልጆች ተብሎ የተጠቀሱት እኛ በጌታ እየሱስ ክርስቶስ አምነን የተጠመቅን ሁላችን ነን በመሆኑም ሰይጣን ሁልጊዜ በአጠገባችን በመሽከርከር ይህን ከእግዚአብሔር የወረስነውን ቅድስና ለማደፍረስ ከእግዚአብሔር ያለንን ግንኙነት ለመደምሰስ ይጥራል ነገር ግን እኛ በሮሜ 8፡31 ላይ እንደተጠቀሰው “ከእግዚአብሔር ጋር ከሆንን ማን ሊቃወመን ይችላል” በሚለው ቃል መሠረት ማንኛውንም ዓይነት የሰይጣን ፈተናና ትንኮሳ ሊያሸንፈን እንዲሁም ከእግዚአብሔር እቅፍ ውስጥ ሊያወጣን አይችልም፡፡

በሐዋርያት ሥራ 11፡1-11 ላይ እንደምንረዳው ደግሞ እንዳንድ ጊዜ ሰዎች ከፍቅር ይልቅ ለሕግ ቅድሚያና ቦታ ሲሰጡ ይታያል፡፡ ለዚህም ነው “አይሁዳውያን ከአረማውያን ጋር አይብሉ” የሚለውን የአይሁድ ሕግ ቅዱስ ጴጥሮስ ከአረማውያን ጋር በልቷል በማለት አይሁዳውያን የሚከሱት፡፡

ይህ አካሄድ በተለያየ መልኩ በቤተክርስቲያንም ውስጥ ጭምር ይከሰታል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙ ድንቅ ነገሮችን ሲያደርግ የማይደሰቱ ሰዎች ይኖራሉ፡፡ ምክንያቱም ቅድም እንደጠቀስነው ሰይጣን በተለየ መለኩ መልካም ሥራ ሁሉ የሚቋረጥበትንና የሚጠፋበትን መንገድ ያመቻቻል አንዳንድ ጊዜም በእምነታቸው ያልጠነከሩትን ሰዎች ልብ በመስለብ በእነርሱ አማካኝነት የእግዚአብሔር መልካም ሥራ ለማዳናቀፍ ይጥራል፡፡

ማንኛውም ሰው መልካም ሥራ በመሠራቱ የሚካፋ በተዘዋዋሪ መልኩ በእግዚብሔር ላይ ማመፁንና ማጉረምረሙን መርሳት የለበትም ምክንያቱመ የመልካም ሥራ ባለቤትና አነሳሹ ሁልጊዜም ቢሆን እግዚአብሔር ራሱ ነውና ነው፡፡ እስራኤላውየን በእግዚአብሔር ላይ ማጉረምረማቸውን ተከትሎ እግዚአብሔር ወደ ተሰፋይቱ ምድር እንዳይገቡ እድርጐአቸዋል /ዘኁ 14፡26-30/ እንዲሁ ደግሞ እግዚአብሔር በሰዎች በኩል አድርጐ ለሚያከናውናቸው መልካም ሥራዎች እንቅፋት የሚሆኑት ሁሉ ከዚህ ከተሳሳተ አካሄደቸው ካልተቆቡ ተመሳሳይ ነገር ሊጥማቸው ይችላል፡፡

ማንም ሰው መልካም ሥራን ለመሥራት በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት ሲነሳሳ የሥራው ባለቤት ራሱ እግዚአብሔር ነው ስለዚህ በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት የተጀመረን ሥራ ማንኛውም ዓይነት ኃይል ወይንም ጉልበት ሊቋቋመው አይችልም በዚህ መሰረት ቅዱስ ሐዋርያው ጴጥሮስ ምንም እንኳን ክርስቲያን በሆኑ አይሁዶችና ክርስቲያን ባልሆኑ አይሁዶች ቢከሰስም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ሁሉንም አስረዳቸው አብዛኞቹም አምነው ተጠመቁ እግዚአብሔር ንጹሕ ያደረገውን አንተ ርኩስ ነው ማለት አትችልም በሚለው ቃል ተማምነው እግዚብሔርን አመሰገኑ፡፡

ይህ የማቴወስ ወንጌል ምዕራፍ  21፡33-46 ያለው በትንቢተ ኢሳያስ 5፡1-7 ካለው ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ ይህ ታሪክ በመጀመሪያ ደረጃ የእስራኤልን ሕዝብ ታሪክ ይወክላል፡፡ የንስሃንና የጽድቅን ፍሬ ያገኝባቸው ዘንድ እግዚአብሔር ተራ በተራ የቡልይ ኪዳንን ነቢያት ወደ እስራኤላውያን ሲልክ  ነበር እነርሱ እያንዳንዱን በማግደል እግዚአብሔር አስቀየሙ፡፡ በስተመጨረሻም እግዚአብሔ አንድያ ልጁን ወደ እነዚህ ሕዝቦች ላከ እነርሱም ይህማ ወራሹ ነው ብለው እርሱንም ገደሉት፡፡

እንግዲህ የወይኑ እርሻ ባለቤት ሲመጣ  እነዚያን ገዳዮች በሙሉ ያስወግድና የወይኑን እርሻ ለሌሎች ገበሬዎች ያከራያል፡፡ ይህ ምሳሌ በ70 ዓ.ም. ሮማውያን እየሩሳሌምን በደመሰሉ ጉዜ የተፈፀመ ትንቢት ነው፡፡ ይህም ማለት የእግዚአብሐር ቃል የእግዚአብሔር የማዳን ታሪክ ለእስራኤለውያን ቢሰጥም እነርሱ ግን ይህን ደጋ ለመቀበል የተገቡ አልነበሩምና ይህ ጸጋ ከእነርሱ ተወስዶ ለሌሎች አሕዛብ እንደሚሰጥ ያስረዳናል፡፡ ዛሬም ቢሆን ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ለሁላችን ይህን ጸጋና በረከት በስጥቶናል ነገር ግን እኛም የዚህ ጸጋና በረከት ተጠቃሚዎች ካልሆንን ይህ ጸጋ ከእኛ ተወስዶ ለሌሎች እንደሚሰጥ መረዳት መቻል አለብን፡፡ ዛሬ እያንዳንዳችን እግዚአብሔር ከእነዚያ ክፉ ገዳይ ገበሬዎች ነጥቆ ለሌሎች ገበሬዎች የተባሉትን እንወክላለን፡፡ ስለዚህ በዚህ በወይን እርሻ ውስጥ በሚገባ እንደንስራ ብሎም መልካም ፍሬ እንድንፋፈራ ተጋብዘናል፡፡ ይህ የወይን እርሻ የእያንዳዳችን ሕይወት ነው ስለዚህ በገባንበትና በምንመራው ሕይወት ውስጥ እግዚአብሔርና ሰውን ሁሉ የሚያስደስት ሥራ እንድንሰራ ዘወትር እግዚአብሔር በልጁ አማካኝነት በሰጠን ደጋና ባስተማረን ትምሕርት መሠረት እንደንመላለስ ያስፈልጋለ ይህ ካልሆኘ አሁንም ይህ ደጋ ከእኛ ይነጠቃል ለሌሎችም ይሰጣል፡፡

ይህ የማዕዘን ድንጋይ የሆነ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ዘወትር እርሱ በሰጠን አዲስ እርሻ ውስጥ በሙላት እንድንንቀሳቀስ ዘወትር በኃይሉና በጋው ይጐበኘናልና ልባችንን እንዲሁ ሁለመናችን ለእርሱ በመክፈት የጸጋውና የበረከቱ ተቋዳሽ እንሁን፡፡

11/11/2017 13:21