Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ስብከቶች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ "ቤተ ክርስቲያንን ማነጽ፣ መንከባከብ፣ ማንጻት ያስፈልጋል" ማለታቸው ተገለጸ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት መስዋዕተ ቅዳሴን ማሳረጉበት ወቅት

10/11/2017 15:50

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ጥዋት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስት ማርታ የጸሎት ቤት መስዋዕተ ቅዳሴን እንደ ሚያሳርጉ ይታወቃል። በትላንትናው እለት ማለትም በጥቅምት 30/2010 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ለተገኙ ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን  ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙት ስብከት ትኩረቱን በእለቱ በላቲን የስርዓተ አምልኮ ደንብ አቆጣጠር መሰረት በእለቱ በተከበረው የቤተ ክርስቲያን ሁሉ እናት በመባል የምትታወቀው በሮም ከተማ የሚትገኘው ካትድራል አመታዊ በዓል በተከበረበት ወቅት እንደ ነበረ የታወቀ ሲሆን ቅዱስነታቸው በእለቱ ያሰሙት ስብከት ቤተ ክርስቲያንን ማነጽ፣  መንከባከብ፣ ማንጻት በሚሉ ሦስት አበይት ቃላት ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

በሮም ከተማ የሚገኘውን ካቴድራል አመታዊ በዓል የምናከብረው ይህቺ ካቴድራል የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እናት በመሆኑዋ የተነሳ በኩራት ተሞልተን ሳይሆን ነገር ግን ይህ ካቴድራል ላበረከተው መልካም አገልግሎት እና ፍቅር ያለንን አድናቆት ለመግለጽ ነው ካሉ ቡኃላ የቤተክርስቲያን መሰረት ክርስቶስ መሆኑን አስታውሰው እኛም ቤተክርስቲያንን ለማነጽ የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይገባናል ብለዋል።

“ክርስቶስ የመዕዘን ድንጋይ ነው፣ በርሱ ላይ ነው ቤተክርስቲያን የተገነባችው። ያለ እየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ልትኖር አትችልም። ለምን ይመስላችኃል? ምክንያቱም አንድ እና አንድ ነው፣ ያለ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን መሰረት ሊኖራት አይችልም። አንድ ቤተክርስቲያን ለመገንባት ስንነሳ በምን መሰረት ላይ እንደ ምንገነባ ሳናስብ ቁሳዊ የሆኑ ነገሮችን ብቻ የምናስብ ከሆንን፣ ምን ሊከሰት ይችላል? ይደረመሳል። ሁሉም ነገር ይፈርሳል። ህያው የሆነ ክርስቶስ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሌለ ከሆነ ቤተክርስቲያን ይፈርሳል” በማለት ተግረዋል።

ታዲያ የእኛ ድርሻ ምንድነው? በማለት ጥያቄን በማንሳት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እኛም ብንሆን ሕያው ድንጋዮች ነን፣ ሁላችንም እኩል አይደለንም፣ የተለያዩ ዓይነት ሰዎች ነን፣ ይህ ልዩነት ነው ቤተክርስቲያናንን የሚያበለጽጋት ብለዋል። እያንዳንዱ ሰዎ እግዚኣብሔር በሰጠው የተለያዩ ስጦታዎች ወይም መክሊቶች የራሱን  ገንቢ የሆነ አስተዋጾ ማድረግ ይኖርበታል ያሉት ቅዱስነታቸው አንድ ወጥ የሆች ቤተክርስቲያንን ማለም አይገባንም ሁሉም ነገር አንድ ወጥ የሆነበት ቤተ ክርስቲያን ቤተክርስቲያን ሊባል አይችልም ብለዋል።

ስለዚህ አሉ ቅዱስነታቸው ሰለዚህ “ቤተክርስቲያንን መንከባከብ” ማለት በውስጣችን ያለውን የእግዚኣብሔር መንፈስ በውስጣችን እንዳለ ከግምት በማስገባት ሊሆን እንደ ሚገባ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን  ብለዋል፣

“የዛሬ ክርስቲያኖች ኢየሱስ ክርስቶስ እና እግዚኣብሔር አብ ማን መሆናቸውን በሚገባ ያውቃሉ። ምክንያቱም አባታችን ሆይ! የሚለውን ጸሎት በየቀኑ ስለሚጸልዩ ነው። ነገር ግን ስለመንፈስ ቅዱስ በምንናገርበት ወቅት “በእርግብ አማሳል እንደ ሆነ ብቻ ያወራሉ ከዚያም ዘለል ያለ ነገር አያወሩም በዚያ ያቆማሉ። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ የቤተክርስቲያን ሕይወት ነው፣ የእናንተ ሕይወት የእኔም ሕይወት መሰረት ነው፣ እኛ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያዎች ነን፣ ስለዚህም መንፈስ ቅዱስን መንከባከብ ይኖርብናል፣ ለዚህም ነው ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ በመልእክቱ መንፈስ ቅዱስን ማሳዘን እንደ ማይኖርብን የሚያሳስበው። ይህም ማለት መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን እና በቤተክርስቲያን ሕይወት ውስጣ ከሚጫወተው በጎ ተግባርን በተቃረነ መልኩ ምንም ዓይነት ተግባሮችን መፈጸም የለብንም ማለት ነው። በቤተክርስቲያን እና በእኛ መካከል ሕብረት እንዲኖር የሚያደርገው እርሱ ብቻ ነው። ብለዋል

በመጨረሻም “ቤተክርስቲያን ማንጻት” የሚለውን ቃል ማየት የሚገባን ከራሳችን ሕይወት በመነሳት ነው ያሉት ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል፣

“እኛ ሁላችን ኃጢኣተኞች ነን። እስቲ ከእናንተ አንዱ ኃጢኣት የለብኝም የሚል ካለ እጁን ያንሳ፣ ምክንያቱም የዚህ ዓይነቱን ሰው የማወቅ ጉጉት ስላለኝ ነው።  ለዚህም ነው ቀጣይነት ባለው መልኩ ራሳችንን ማንጻት የኖርብናል የምለው። በተጨማሪም ማሕበረሰቡን፣ ሀገረ ስብከቱን፣ የክርስቲያን ማኅበረሰቡን፣ በዓለማቀፍ ደረጃ የሚገኙትን የክርስቲያን ማሕበረሰቦችን ማንጻት ያስፈልጋል፣ ይህም ለቤተክርስቲያን እድገት መሰረት ነው” ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 

10/11/2017 15:50