2017-11-09 11:22:00

“ ደኃንነት ነጻ የእግዚኣብሔር ስጦታ ነው” ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ጥዋት በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ለሚሰበሰቡ ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን መስዋዕተ ቅዳሴ እንደ ሚያሳርጉ ያትወቃል። የዚህ መርሀግብር አንዱ አካል በሆነው በትላንትናው እለት ማለትም በጥቅምት 28/2010 ዓ.ም ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “መወደዳችሁን የሚገልጽ ስሜት በፍጹም አትጡ፣ ይህንንም ስሜት መልሳችሁ ለመጎናጸፍ ሞክሩ፣ ይህን የመወደድ ስሜት ካጣችሁ ግን ሁሉንም ነገር እንዳጣችሁ ቁጠሩ” ማለታቸውም ተገልጹዋል።

የዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በእለቱ በላቲን ስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት ከሉቃስ ወንጌል (14:15-24) ላይ ተወስዶ በተነበበውና ከኢየሱስ ጋር በማእድ ከተቀመጡት ሰዎች መካከል አንዱ “በእግዚኣብሔር መንግሥት ቀርቦ በማእድ የሚበላ ብፁዕ ነው” ብሎ በተናገረበት ወቅት  ኢየሱስም “ከእናንተ መኃል አንዱ ታላቅ የሆነ ግብዣ አዘጋጅቶ ሰዎችን ወደ ቤቱ በሚጠራበት ወቅት ብድሩን ለመክፈል የማይችሉ ሰዎችን መጥራት እንዳለበት” ኢየሱስ እንደ መከረው ቅዱስነታቸው ገለጸዋል።

“አንድ ሰው ትልቅ ግብዣ አዘጋጅቶ ብዙ ሰው ጠራ” በማለት የሚጀምረው የእለቱ ወንጌል  “የግብዣውም ሰዓት በደረሰ ጊዜ ተጋባዢ እንግዶች ግን ለእራት ግብዣ፣ ለተጋበዙ ሰዎች፣ እራቱንም ለጋበዛቸው ጌታ ምንም ደንታ አልንበራቸውም ነበር፣ ምክንያቱም ከግብዣው በላይ የበሆነ መልኩ በእየራሳቸው የግል ተግባራት ተጠምደው ስለነበረ መሆኑን ቅዱስ ወንጌል ላይ መጠቀሱን በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው፣ አንደኛው፣ ‘ገና አሁን መሬት ስለ ገዛሁ ሄጄ ማየት አለብኝ፤ እባክህ፣ ይቅርታ አድርግልኝ’ አለው  “ሌላኛውም፣ ‘አምስት ጥማድ በሬዎች ገዝቻለሁ፤ እነርሱን ልፈትናቸው ስለ ሆነ እባክህ ይቅርታ አድርግልኝ’ አለ፣  “ሌላው ደግሞ፣ ‘ገና ሙሽራ ስለ ሆንሁ ልመጣ አልችልም’  በማለት እንደመለሱለት ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል። ይህንን ግብዣ አልቀበልም ያሉበት ዋንኛው ምክንያት ግን አሉ ቅዱስነታቸው፣ ከብዣው በተሻለ መልኩ በግል በተሰማሩበት የሥራ መስክ የበለጠ ትርፋማ እንደ ሚሆኑ ሰለሚያውቁ እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው “እነርሱም ብዙ ምርት አምርቶ ትልቅ የማጠራቀሚያ ጎተራ ሰርቶ ለራሱ ሀብት ያጠራቀመውን፣ ነገር ግን በዚያች ማታ ያጠራቀመውን ሀብት ሳይበላ የሞተውን ሰው እንደ ሚመስሉም ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

ከግል ጥቅማቸው ጋር በከፍተኛ ሁኔታ ተቆራኝተው ስለነበር ይህም ቁርኝታቸው የዚህ ስሜት ባሪያ እንዲሆኑ ስላደረጋቸው “የግብዣው ጥሪ በነጻ እንደ ነበረ እንኳን እንዳይረዱ አድርጎዋቸው” እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

“እግዚኣብሔር የሚጋብዘን ግብዣ በነጻ መሆኑን የማንረዳ ከሆንን፣ ከዚህ የተሻሉ ነገሮችን በፍጹም መረዳት አንችልም ያሉት ቅዱስነታቸው እግዚኣብሔር በራሱ ተነሳሽነት ሁል ጊዜም ቢሆን የነጻ ግብዣ ነው የሚያዘጋጅልን ብለዋል። ነገር ግን ወደ እዚህ ግብዣ ለመሄድ ምን መክፈል ይኖርብናል? በማለት ጥያቄን በማንሳት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ወደ እዚህ ግብዣ የመግቢያ ትኬት ለማግኘት በሽተኛ፣ ድኸ፣ ኃጢኣተኛ ወዘተርፈ መሆን ይኖርብናል ካሉ ቡኃላ የመጊቢያ ትኬት የሚሰጣቸው ሰዎች የሥጋ ወይም የነብስ ፈውስ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች እንደ ሆኑም ገልጸው ነገር ግን ፈውስ ለማግኘት ከተፈለገ ግን ፍቅር ሊኖረን ይገባል ብለዋል።

በዚህ ረገድ ሁለት ባሕሪያት ይገኛሉ፣ በመጀመሪያ ደረጃ ምንም ነገር ሳያስከፍል ወደ ገብዣ ስፍራ ለመጥራት አስቦ አገልጋዩን “ቶሎ ብለህ ወደ ከተማው አውራ ጐዳናዎችና መተላለፊያ መንገዶች ውጣ፤ ድኾችንና አካለ ስንኩሎችን፣ ዐይነ ስውሮችንና አንካሶችን ወደ እዚህ አስገባቸው’ ብሎ መናገሩ እግዚኣብሔር የሚሰጠን የነጻ ስጦታ ምንም ገደብ እንደ ሌለው ያሳያል ካሉ ቡኃላ እግዚኣብሔር ሁሉንም እንደ ሚቀበል ያሳያል ብለዋል። በሌላ በኩል የምናገኘው ሁለተኛው ባሕሪ ደግሞ በቅድሚያ ወደ ግብዣው የተጠሩ ሰዎችን ሲሆን እነርሱም ግብዣው በነጻ እንደ ነበረ እንዳልተረዱ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህም ጠፍቶ የተገኘው ልጅ ታላቅ ወንድም አባቱ ያዘጋጀውን ግብዣ ዋጋ ያልተረዳውን ሰው ዓይነት ባሕሪ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

እንደ እነዚህ ዓይነት ሰዎች ድኅንነት በነጻ የሚሰጠን የእግዚኣብሔር ስጦታ መሆኑ የማይገባቸው ሰዎች እንደ ሆኑ በመግለጽ ስብከታቸውን የገቀጠሉት ቅዱስነታቻው አንድ አንድ ሰዎች ደኅንነት “እኔ እከፍላለሁ አንተ ደግሞ አድነኝ” በማለት የከፈልነው ክፍያ ውጤው ወይም ፍሬ አድርገው እንደ ሚቆጥሩ ቅዱስነታቸው ገለጸው ነገር ግን ደኃንነት ነጻ የእግዚኣብሔር ስጦታ መሆኑን እና ለዚህም ምላሽ የሚሰጠውን ልባችንን ወደ እርሱ በማቅረብ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን አስተንትኖ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.