2017-11-07 09:34:00

"ክርስቲያኖች የጌታችን የኢየሱስን አብነት በመከተል በተለያየ ደረጃ የተሰጡዋቸውን ኃላፊነት በትክክል መወጣት ይኖርባቸዋል"


ዘወትር እሁድ እለት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ የሚደረጉን አስተንትኖ ለመከታተል በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እንደ ሚሰበሰቡ ይታወቃል። ቅዱስነታቸው ባለፈው እሁድ እለት በእለቱ ወንጌል ላይ ባደረጉት አስተንትኖ ክርስቲያኖች የጌታችን የኢየሱስን አብነት በመከተል በተለያየ ደረጃ የተሰጡዋቸውን የሀላፊነት ድርሻቸውን  ለወንድሞቻችን እና ለእህቶቻችን አገልግሎት በማዋል ማገልገል ይኖርብናል ማለታቸው ተገለጸ።

ክቡራን እና ክቡራት ተዝግጅታችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ባልፈው እሁድ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በእለቱ ቅዱስ ወንጌላ ላይ አድርገውት የነበረውን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ  እንደምን አረፈዳችሁ!

ዛሬ የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል (ማቴ. 23:1-12) ኢየሱስ በመጨረሻው  የሕይወት ዘመኑ ውስጥ እንደ ሚከሰት የጠበቀውና አልፎም ተርፎም በጭንቀት የተሞላ በኢየሩሳሌም ስለተከሰተው ነገር ያወሳል። በአንድ በኩል ኢየሱስ በአይሁዳዊያን እና በፈርሳዊያን ላይ ጠንከር ያለ ትችት ስያቀርብ በሌላ በኩል ደግሞ በሁሉም ዘመን ለሚገኙ ክርስቲያኖች እኛንም ጨምሮ ማለት ነው በጣም አስፈላጊ የሆነ ትምህርት ያስተላልፍልናል።

ኢየሱስ ለሕዝቡና ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ሲል ተናገረ ““የኦሪት ሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ላይ ተቀምጠዋል።ስለዚህ የሚነግሯችሁን ሁሉ አድርጉ፤ ጠብቁትም፤ ነገር ግን እንደሚናገሩት አያደርጉምና ተግባራቸውን አትከተሉ” ይላል። ይህም እነርሱ ከእግዚኣብሔር ሕግ ጋት ጋር የተቆራኜ አስተምህሮ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸው ያሳያል። ከሁሉም በለይ ደግሞ ወዲያሁኑ “ነገር ግን እንደሚናገሩት አያደርጉምና ተግባራቸውን አትከተሉ” በማለት ሲናገር እንሰማለን።

ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ይህም የተለያየ ዓይነት የቤተ ክርስቲያን የሁን በተለያዩ የመንግሥት የሥልጣን ባለቤት በሆኑ ሰዎች ላይ የሚታይ ሲሆን ይህም በሌላ ነገሮች ላይ በመጠመድ የተሰጣቸውን የኃልፊነት በትግባር ላይ ሳያውሉት ይኖራሉ። ሁለት ዓይነት ሕይወት ይኖራሉ። ለዚህም ኢየሱስ “ከባድ ሸክም አስረው በሰዎች ትከሻ ላይ ይጭናሉ፤ ራሳቸው ግን በጣታቸው እንኳ አይነኩትም” በማለት የተናገረውም በዚሁ ምክንያት ነው። የዚህ ዓይነት ባህሪ ኃላፊነትን በአግባቡ መልካም ምስሌን በማሳየት ከመወጣት ይልቅ ኃላፊነትን ያለአግባብ የመጠቀም በጣም መጥፎ የሆነ በህሪ ነው። ኃላፊነት መልካም የሆነ አብነትን በመውለድ፣ ሌሎች መልካም የሆኑ ነገሮችን በተግባር እንዲያውሉ፣ ግዴታቸውንም እንዲወጡ በማገዝ፣ መልካም የሆኑ ነገሮችን በተግባር ላይ በሚያውሉባቸው ወቅቶች ሁሉ በዚህ መልካም በሆነ መንገድ ላይ ሊገጣማቸው የሚችሉትን መሰናክሎች በብቃት መወጣት ይችሉ ዘንድ ማብቃት ማለት ሊሆን ይገባል። ኃላፊነት እገዛ ማድረግ ማለት ነው፣ ነገር ግን ያላአግባቡ በምንጠቀምበት ወቅት ሌሎችን መጨቆን ሊያመጣ ይችላል፣ ሰዎችን ከማሳደግ ይልቅ አለመተማመንን እና ታማኝነት እዳይኖር በማድረግ ወደ ሙስናም ሊመራን ይችላል።

ኢየሱስ ዛሬ በግልጽ እንደ እነዚህ ያሉትን አፍራሽ የሆኑ የአንድ አንድ የፈሪሳዊያን እና አይሁዳዊያንን ባህሪ “በግብዣ ቦታ የከበሬታ ስፍራ፣ በምኵራብም የመጀመሪያውን መቀመጫ መያዝ ይወዳሉ። እንዲሁም በገበያ መካከል ሰላምታ መቀበልንና በሰዎች አንደበት ‘መምህር’ ተብለው መጠራትን ይሻሉ” በማለት” (ማቴ 6.7) በግልጽ ሲያወግዝ እንሰማለን። ይህም ሁል ጊዜ በአሸናፊነት ልንወጣው የሚከብደን ከሰዎች ህብሪት የሚመነጭ ፈተና ነው። ከዚያም በመቀጠል ኢየሱስ ለሐዋሪያቶቹ “እናንተ ግን ‘መምህር’ ተብላችሁ አትጠሩ፤ አስተማሪያችሁ አንድ ብቻ ነው፣ እናንተ ሁላችሁም ወንድማማቾች ናችሁና። በሰማይ ያለ አንድ አባት ስላላችሁ፣ በምድር ማንንም ‘አባት’ ብላችሁ አትጥሩ። መምህራችሁ አንዱ ክርስቶስ ስለ ሆነ፣ ‘መምህር’ ተብላችሁ አትጠሩ። ከመካከላችሁ ከሁላችሁ የሚበልጠው አገልጋያችሁ ይሆናል” በማለት ያሳስብቸዋል።

እኛ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የሆንን ሁላችን የክብር መጠሪያ ሥም የሆኑትን፣ ሥልጣን ወይም የበላይ ለመሆን መፈለግ የለብንም። እኔ በበኩሌ በግሌ ስልጣን ለማግኘት የክብር ቦታ ለማግኘት የሚሩሯጡ ግለሰቦችን ማየት ያሳዝነኛል። እኛ የኢየሱስ ደቀመዛሙርት የሆንን ሰዎች ሁሉ እንደ እዚህ ያሉትን ነገሮች በፍጹም መመኘት የለብንም፣ በተለይም ደግሞ በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት የወንድማማችነት እና በየዋህነት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ነው ልኖረን የሚገባው። ሁላችንም ወንድማማቾች በመሆናችን የተነሳ በምንም ዓይነት መልኩ ራሳችንን ከሁሉም በላይ ማድረግ እና ሌሎችን የበታች አድርገን ማየት የለብንም። በፍጹም። ሁላችንም ወንድማማቾች ነን። ከሰማያዊ አባታችን የተቀበልነው መልካም ነገር ካለ፣ ለወንድሞቻችንን አገልግሎት ማዋል እንጂ ለግል ፍላጎቶቻችንና እርካት ብቻ በአጠቃላይ ለግል ፍሎጎቶቻችን ብቻ ማዋል የለብንም። ራሳችንን ከሌሎች የበላይ አድርገን ማየትም የለብንም፣ በልብ የዋህነትና በትህት ለማገልገል እንጂ ለመገልገል የመጣውን ከኢየሱስ አስተምህሮ ጋር የሚመጣጠን ሕይወት ሊንኖር ይገባል።

የዋህ እና ከፍጡራን ሁሉ በላይ የሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በእናትነት አማላጅነቷ ከኩራት እና ከትዕቢት ፈተናዎች እንድንርቅ እንድትረዳን በአንጻሩም ከእግዚኣብሔር ዘንድ የሚመነጨው የዋህነት እና የልብ ቅንነት በመጎናጸፍ ለወንድሞቻችን እና ለእህቶቻችን አገልግሎት እንድናውል ትረዳን ዘንድ መጸለይ ይገባል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.