2017-11-07 09:14:00

ቅዱስ አባታችን እ.ኤ.አ. በዚህ በተገባው ወርሐ ህዳር በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን እስያ የጸሎት ሓሳብ ትሁን አሉ


በዚህ እ.ኤ.አ. 2017 ዓ.ም. ወርሐ ህዳር በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የእስያ ማኅበረ ክርስቲያን የጸሎት ሃሳብ እንዲሆን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ዓለም አቀፍ የጸሎት ሐሳብ መረብት አማክኝነት ባስተላለፉት የድምጸ ርእየት መልእክት አማካኝነት ይፋ ማድረጋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጋብረኤላ ቸራዞ አስታወቁ።

ይኽ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የጸሎት ሐሳብ በአገረ ቫቲካን የቴሌቭዥን ጣቢያ ጭምር መሰራጨቱ ሲታወቅ። በእስያ በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የጋራ ውይይት እንዲበረታ በማሳሰብ፡ የውይይት የሰላም እና የእርስ በእርስ መግባባት በተለይ ደግሞ በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ውይይት እንዲጸና ማድረግ ለማኅበራዊ ሰላም መሰረት ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ቸራዞ ገለጡ።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም ቅዱስ አባታችን በዚህ እ.ኤ.አ. 2017 ዓ.ም. ወርሐ ህዳር በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የእስያ ማኅበረ ክርስቲያን የጸሎት ሃሳብ እንዲሆን በማለት ባስተላለፉት የድምጸ ርእየት መልእክት በማስደገፍ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት የመላ እስያ አገሮች የብፁዓ ጳጳሳት ጉባኤዎች ፍደራላዊ ጉባኤ ሊቀ መንበር በህንድ የቦምበይ ሊቀ ጳጳሳ ብፁዕ ካርዲናል ኦስዋልዶ ግራዚያስ በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ ውይይት በእስያ እጅግ አስፈላጊ ነው፡ እንዲህ በመሆኑም ያች በእስያ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በውይይቱ ረገድ የነቃች ቀዳሜም ነች። የውይይት ባህል የሚያበረታቱ የተለያዩ ጅምሮችንም በማከናወን ማኅበረ ክርስቲያን በዚህ ባህል በማነጽ ሰላማዊ ያብሮ መኖር ታነቃቃለች ብሏል።

ከምስልምና ከቡድሃ ከሲክ እና በጠቅላላ በእስያ ከሚገኙት ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር ውይይት ታነቃቃለች። የጋራ ውይይት ማነቃቃት ሌላው የሚከተለው ሃይማኖት እንዲክድ መወትወት ማለት ሳይሆን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንደሚሉት፡ አብሮ መጓዝ ማለት ነው፡ ውይይት አብሮነትን ያበረታታል። ስለዚህ ሁሉም ሃይማኖቶች ሰላምና መግባባት በማነቃቃቱ ረገድ አብረው እንዲጓዙ የሚል ነው ያሉት ብፁዕነታቸው ቤተ ክርስቲያን በእስያ የሚያስፈልጋት የክርስቶስ መልክ በመሆን ይኸንን ገጽ ለሕዝብ ማቅረብ ነው። ይኽ ደግሞ ለተናቁት ለተረሱት በዳርነት ለሚኖሩት ቅርብ ሆና እንድትኖር የሚል ነው፡ ምግባረ ብልሽት ሙስና የመሳሰሉት ሕዝብን ለስቃይ የሚዳርጉ ግድፈቶች ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ ተጋርጦ ነው። ይኸንን በቃልና በሕይወት ወንጌልን በመመስከር የቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ትምህርት በማስፋት ክርስቶስ በሰጠው ተስፋ ላይ ካለ ምንም መጠራጠር በምትኖረው እምነት እንደምታሸንፈውም የታወቀ ነው ብሏል።

ቅዱስ አባታችን በዚህ ወር ማብቅያ በባንግላደሽና በምያንማር ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ዑደት ይፈጽማሉ። ይኽ ደግሞ በእነዚያ ሁለቱ አገሮች ለሚኖሩት ውሁዳን ማኅበረ ክርስቲያን የሚያበረታታ እና በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የጋራው ውይይት የሚያነቃቃ ነው። በዚያ ክልል የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አናሳ ብትሆንም ብርቱ ነች፡ እርሷን በእምነት ለማጽናት የሚገበኙዋትን ቅዱስ አባታችንን ለማስተናገድ ቅድመ ዝግጅቱ በማከናወን ላይ ትገኛለች በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.