2017-11-07 12:08:00

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ "እግዚኣብሔር ዛሬ አንድ ነገር በስጦታ መልክ ሰጥቶን ነገ መልሶ የሚወስድብን አምላክ አይደለም" አሉ


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በጥቅምት 27/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ እንደ ገለጹት እግዚኣብሔር የሚሰጠን ስጦታዎች ሁሉ የማይለወጡ እንዲሁም የማይሻሩ ናቸው ማለታቸው ተገለጸ። እግዚኣብሔር ዛሬ አንድ ነገር በስጦታ መልክ ሰጥቶን ነገ መልሶ የሚወስድብን አምላክ አይደለም ያሉት ቅዱስነታቸው እግዚኣብሔር በሚጠራን ወቅት ያ ጥሪ በዘላቂነት እስከ መጨረሻ የሕይወታችን ዘመን አብሮን የሚቆይ ጥሪ ነው ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በእለቱ ያሰሙት ስብከት “በእግዚኣብሔር መመረጥ” በሚለው ጭብጥ ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በእለቱ በተነበበውና ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ሮም ሰዎች በጻፈው መልእክቱ (11:29-36) ላይ ተንተርሰው እግዚኣብሔር ለእየአንድአንዳችን የተለያየ ዓይነት ምርጫ አለው ብለዋል። በድህንነት ታሪክ ውስጥ እግዚኣብሔር ለሕዝቡ የሚሰጣቸው ሦስት ስጦታዎች እና ጥሪዎች” ይገኛሉ ያሉት ቅዱስነታቸው ይህም “የመመረጥ ስጦታ፣ የተስፋ ስጦታ እና የቃል ኪዳን ስጦታዎች መሆነቸውን”  ቅዱስነታቸው ገልጸዋል። እነዚህ ሁሉ ስጦታዎች የሚቀለበሱ ወይም ደግሞ የሚሻሩ ስጦታዎች ግን አይደሉም ያሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱ እግዚኣብሔር ሁሌም ቢሆን ለቃሉ ታማኝ በመሆኑ ይተነሳ ነው፣ ይህም አብርሃም በሕይወቱ ዘመን ያረጋገጠው እውነታ ነው የተነሳ ለእኛም ለሁላችንም የሚገለጽ እውነታ ነው ብለዋል።

“እያንዳንዳችን በእግዚአብሔር የተመረጠ ሰዎች ነን። እያንዳንዳችን እግዚኣብሔር የሰጠንን የተስፋ ቃል ይዘናል፣ “በእኔ ፊት ተመላለሱ፣ ተደራሽ ሁኑ፣ እኔም የገባውትን ቃል እጠብቃለሁ’። እያንዳንዳችን ከእግዚኣብሔር ጋር ቃል ኪዳን እንሰር። ይህም ነጻ የሆነ ስጦታ ነውና መድረግ እንችላለን። ይህም እውነታ ነው።  ነገር ግን በዚህ ረገድ አንድ ጥያቄ ማንሳት ይገባናል፣ “በእግዚኣብሔር መመረጣችንን እንዴት ማወቅ እንችላለን?’ ወይም ደግም ራሳችንን ድንገት ክርስቲያን እንደ ሆንን አድርገን ነው ወይ የምቆጥረው?’ እንዴት ነው የተገባልኝ ቃል፣ ቃል የተገባልኝን የደህንነት መንገድ በአጠቃላይ እርሱ ለቃሉ ታማኝ እንደ ሆነ እኔም ለተገባልኝ ቃል ኪዳን ታምኝ ነኝ ወይ?’

በዚህ ዘላቂ በሆነ የእግዚኣብሔር ታማኝነት ውስጥ በመሆን ራሳችንን “የእግዚኣብሔር እንክብካቤ፣ ጥበቃ ከእርሱ በምንርቃባቸው ወቅቶች ሁሉ እኛን ሊፈልገን እንደ ሚወጣ  በሕይወታችን ውስጥ እንዳለ ይሰማናል ወይ?  

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት በተደጋጋሚ ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ሮም ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ላይ የተጠቀሰው “በእግዚኣብሔር መመረጥ” የሚለውን ቃል በተደጋጋሚ በመጥቀስ “አለመታዘዝ” እና “ምሕረት” የሚሉትን ሁለት ቃላት በተደጋጋሚ መጠቀማቸውንም ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “አለመታዘዝ” ባለበት “ምሕረት” ይገኛል ይህም የደኅንነታችን መንገድ ነው ብለዋል።

“ይህም ማለት በጥሪ መንገድ ላይ፣ ወደ ተስፋ እና ወደ ቃል ኪዳኑ በምንጓዝባቸው ወቅቶች ሁሉ ኃጢኣትና አለመታዘዝ ይኖራል፣ ነገር ግን በዚህ ያለመታዘዝ ሂደት ውስጥ ሁል ጊዜም ቢሆን የእግዚኣብሔር ምሕረት ይገኛል። ይህም ወደ ጉልምስና የሚደረገውን ተለዋዋጭ ሂደት ይመስላል፣ ሁል ጊዜም ቢሆን ምሕረት አለ፣ ምክንያቱም እርሱ ታማኝ የሆነ እና የሰጠንን ስጦታዎች መልሶ የሚቀማን ባለመሆኑ የተነሳ ነው። የተሰጡን ስጦታዎች የማይሻሩ ወይም የሚቀለበሱ አይደሉም። ነገር ግን ለምን? ምክንያቱም በድክመታችን እና በኃጢኣታችን ፊት ሁሉ የእግዚኣብሔር ምሕረት ስለሚገኝ ነው። በዚህ ረገድ ሐዋሪያው ጳውሎስ በአስተንትኖ አንድ እርምጃ ወደ ፊት በመሄድ  ሐሳቡን በማብራራት ሳይሆን እግዚኣብሔርን ማምለክ እንደ ሚገባ በማሳሰብ ሐሳቡን ይቋጫል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት “በዚህ ያለመታዘዝ እና ከዚህ አለመታዘዝ ነጻ በሚያወጣን የምሕረት ምስጢር ውስጥ’ አምልኮ እና በጸጥታ የሚደረግ ምስጋና አለ” ካሉ ቡኃላ “እነዚህ የማይቀለበሱ ወይም የማይሻሩ መመረጥ፣ ተስፋ እና ቃል ኪዳን የሚባሉት ስጦታዎች በዘላቂነት ከእኛ ጋር የሚኖሩ ስጦታዎች ናቸው ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.