Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ንግግሮች

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፥ የውጭ አገር ሰዎችን የመጥላት ስሜት ክርስቲያን በሆኑት አገሮች ጭምር የሚታይ አደጋ ነው

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፥ የውጭ አገር ሰዎችን የመጥላት ስሜት ክርስቲዿን በሆኑት አገሮች ጭምር የሚታይ አደጋ ነው ማለታቸው ተገለጸ - AP

07/11/2017 09:12

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ከህዳር 1 ቀን እስከ ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም. ተፈናቃዮችና ስደተኞች በዚህ ዓለማዊነት ትሥሥር በተረጋገጠበት ዓለም፡ የመናብርተ ጥበብ ኃላፊነት እና ምላሽበሚል ርእስ ሥር በጳጳሳዊ ግረጎሪያና መንበረ ጥበብ አዘጋጅነት በተሄደው ዓለም አቀፍ ዓውደ ጉባኤ የተሳተፉትን አገረ ቫቲካን በሚገኘው በብፁዓን ካርዲናላት የጉብኤ አዳራሽ ተቀብለው፥ ተጨባጭ ዓለማዊ ትሥሥር መልክ የያዘው እና እጅግ የተወሳሰበውን የዘመኑ የስደተኞች ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ለመስጠት የካቶሊክ መናብርተ ጥበብ አብነት በመከተል ለዚያ የስደት ክስተት ካለ ማወቅ ምክንያት የሚሰጠው ቅድመ ፍርድ እና ፍርሃት ማሸነፍ በርግጠኝነት የሚቻል ነው የሚል ሃሳብ ያማከለ ምዕዳን መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞናኮ አስታወቁ።

ቅዱስነታቸው በለገሱት ቃለ ምዕዳን፥ እነዚህ የካቶሊክ መናብርተ ጥበብ ማኅበራዊ ክስተት የሆነውን የህዝቦች መፈናቀል የስደተኞች ጸአት ተገቢ መልስ የመጀመሪያ እርዳታ በማቅረብ የሚጠቃለል ሳይሆን፤ ያንን በሁሉም ሰው ዘንድ በኑባሬ ያለውን ብሩህ መጻኢ የመሻቱ ግፊት መልስ ለመስጠት የሚችል ጭምር መሆን አለበት። ስለዚህ ከተስተናገደበት አገር ጋር እራሱን አስተዋውቆ አስተናጋጁን አገር አውቆ ተዋኅዶ እንጂ ባስተናጋጁ አገር ባህል ቋንቋ እና ሃይማኖት ተመስጦ እንዲኖር መገደድ የለበትም። ባንጻሩ ስደተኛው የተስተናገደበትን አገር ባህል ሃይማኖት አክብሮ መኖር ግዴታ አለበት ያሉት በዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ በማለት ባስተላለፉት ቃል ምዕዳን ቀደም በማድረግ በተጋባእያኑ ስም በቅዱነታቸው ፊት ተጋባእያኑን በማስተዋወቅ ንግግር ላስደመጡትና ቅዱስነታቸው ቃለ ምዕዳን ለመለገስ መገኘታቸው የምስጋና ንግግር ላስደመጡት ለዓለም ዓቀፍ የካቶሊክ መናብርተ ጥበብ ፈደሬሽን ሊቀ መንበር አመስግነው፡ ይኽ ማሕበር ካቶሊካዊ ሕንጸት በማነቃቃት የፍጥረትና የተፈጥሮ ጥበቃና እንክብካቤ የሁሉም ሰብአዊ ፍጥረት ኃላፊነት መሆኑ ገልጠው፥ ሰብአዊነት የተካነ ማኅበራዊ ቅንና ፍትሐዊ ዓለም ለመገንባት በሚደረገው ጥረትና በሚሰጠው አገግሎት በተቀዳሚነት የሚጠቀስ ማኅበር ነው እንዳሉ ሎሞናኮ ገልጠዋል።

የምንኖርበት ዓለም ዓለማዊ ትሥሥር የሚረጋገጥበት የተወሳሰበ ማኅበራዊና ሰብአዊ ችግሮች የስደተኞች ጸአት የተሰኙት ተግዳሮቶች የሚታይበት ነው፡ እነዚህን ተግዳሮቶችን በቤተ ክርስቲያን ጠመቅ የማኅበራዊ ትምህርት፡ በቲዮሎጊያና በሌሎች በሚሰጡት የትምህርት ዘርፎች አማካኝነት ገጥሞ ተገቢ ምላሽ ለመስጠት በሚደረገው ጥረት የካቶሊክ መናብርተ ጥበብ እንደ አብነት ለመጥቀስ ይቻላል። የተካሄደው ዓውደ ጉባኤ የሚያረጋግጠው እውነት ነው፡ ስደተኛ በተስተናገደበት አገር የተለየ የሚያስብለው ያጋጣሚ መሆናውያን በሆኑት በቋንቋው በባህልም በሃይማኖት ምክንያ ነው፡ ይኽ ልዩ የሚያደርገው ክስተት ለሚያስከትለው ቅድመ ፍርድና ፍርሃት ለማሸነፍ እነዚህ መናብርተ ጥበብ የሚሰጡት አገልግሎት የሚመሰገን ነው እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሎሞናኮ አያይዘው፥ ካቶሊካያን መናብርተ ጥበብ እምነትና ስነ ምርምር በሚያወያይ ስልት እምነትና ስነ ምርምር የሚሟሉ እንጅ አንዱን ሌላውን የሚክድ እንዳልሆነ በማብራራት፡ የስደተኛው ሁነት በዚህ ስልት በማንበብ ለስደት የሚዳርጉትን ችግሮ በመለየት ተጨባጭ መፍትሔ እንዲያገኝ ምን መደረግ እንዳለበት ተጨባጭ ሃሳብ ያቀርባሉ። ይኽ ደግሞ መጻእተኛው የመጥላት ዘረኝነት የመሳሰሉትን ችግሮች እንዲወገድ ያደርጋል።

ቤተ ክርስቲያን በስደተኛው ላይ ክርስቶስን ነው የምታስተነትነው። …. እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛል (አስተናዳችሁኛ) (ማቴ. 25. 35 … ተመል.)  ስለዚህ ይኽ ደግሞ ለእምነታችን እና ለክርስቲያዊ ኑሮአችን አቢይ ተጋርጦ ነው፡ ካንተ በተለየው ሰው ዘንድ ሊገናኝህ የሚመጣውን ክርስቶስ ማወቅ እንዳሉ አስታውቋል።

ሰው በእግዚአብሔር አርአያና አምሳያ የተፈጠረ ነው በሚል እውነት ላይ የጸና የስነ ሰብእ ትምህርት በሕንጸት ዘርፍ ማስፋፋት ስደተኛው እና ተፈናቃይ ዜጋ ትምህርት የማግኘት ሰብአዊ መብቱ ጭምር እንዲከበርለትም ያነቃቃል። ለመናብርት ጥበብ በሚሰጠውም ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አማካኝነት ይበረታታል።

የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መናብርተ ጥበብ ልክ እንደ ሁሉም የመንግሥት ተቋሞች የሕዝቦችን ችግር የእራሳቸው በማድረግ መፍትሔ እንዲያገኝ ችግሩን በጥልቀት በማጥና መፍትሔው በቃልና በሕይወቱ የሚያመላክቱ ናቸው ያሉት ቅዱነታቸው መልእኽታቸውን ሲያጠቃልሉ፡ እ.ኤ.አ. በ 2018 ዓ.ም. ታስቦ ለሚውለው ዓለም አቀፍ የስደተኞችና ተፈናቃዮች ቀን ምክንያት ቀድመው ባስተላለፉት መልእክት፥ ስደተኛውን የማስተናገድ እና የመከላከል ተግባር በማነቃቃት በተስተናገደበት አገር ተዋህዶ እንጂ ተመስጦ እንዳይኖር የሚያስችለው እድል መፍጠር ያስፈልጋል ያሉትን ጠቅሰው፡ ዕለቱም የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ካርሎ ቦሮመዮ ያከበረችበት ዕለት መሆኑ ዘክረው የቅዱስ ቦሮመዮ እምነትና ትህትናውን ሊቅነቱም በሥነ ምርምርም ሆነ በማሕብራዊ የአገልግሎት ዘርፍ ድጋፍ ይሁንልን ብለው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሎሞናኮ አስታወቁ።

07/11/2017 09:12