Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ ግብረ ሠናይና ትብብር

ብፁዕ ካርዲናል ፊሎኒ፡ የእግዚአብሔር ፍቅር ለተናቁት ፍትሕ ነው

ብፁዕ ካርዲናል ፊሎኒ፡ የእግዚአብሔር ፍቅር ለተናቁት ፍትሕ ነው - RV

31/10/2017 09:43

የአስፍሆተ ወንጌል ለአሕዛብ ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ፈርናንዶ ፊሎኒ እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምረው የካምፓላ ርእሰ ሰበካ ቅዋሜ ዝክረ 50ኛው ዓመት ምክንያት በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ስም ሐዋርያዊ ጉብኝት አያካሄዱ መሆናቸው የገለጡት የቫቲካን ርዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋንቲ፥  ብፁዕነታቸው እ.ኤ.አ. ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም. ካምፓላ በሚገኘው በኡጋንዳስ ሰማዕታት ቅዱስ ሥፍራ ተገኝተው ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ መጠናቀቁ አስታወቁ።

በላቲን ሥርዓት የዕለተ ሰንበት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም. ከኦሪት ዘጸኣት ምዕ. 22 ከቁ. 20-26፤ 1ተሰሎንቄ ምዕ. 1. 5-10፤ ከማቴዎስ ምዕ. 22. ከቍ 34-40 በተወሰዱት ምንባባት ላይ ተንተርሰው ባስደመጡት ስብከት፥ እግዚአብሔር እምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህ በፍጹም አሳብህ ውደድ የሚለው ከሁሉም በላይ የሆነው ቀዳሚው ትእዛዝ ቀጥሎም ይኽ ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር የምንገልጥበት የምንኖበት፤ ሰውህ ሁሉ እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ የሚለውን ቃል ጠቅሰው የድኾችን ጩኸት እምባ የተናቁትን ለተረሱትን ለተገለሉትን ለስደተኞችን ለተፈናቀሉትን ሁሉ ቀረቦ በመደገፍ ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር እንግለጥ፡ እኔ አልነካውን አልደርስበትን አልበድለውም እኔ ባለሁበት እርሱ ባለበት ብሎ ክፉ አልማድረግ ይበቃል ብሎ ባሉበት መቆም ክርስቲያናዊ ተግባር አይደለም።  ይኸንን እማ የማያምኑትም ሁሉ ያደርጉታል። አነዚህ በችግር ላይ የሚገኙት የኅብረተሰብ ክፍል ቅርብ ሆኖ መሠረታዊ ጥያቄአቸው መልስ እንዲያገኝ ማድረግና መልስ መስጠት፡ ፍላጎታቸውን ማሟላት ያስፈልጋል።

 በመካከላችን እርስ በእርሳችን የምንገላለጠው ፍቅር ለዚያ ለምናመልከው ለምንቀድሰው እግዚአብሔር ያለን ፍቅር መመዘኛ ነው። ነገር ግን እንግዚአብሔር ሳናፈቅር ወንድማችንን ለማፍቅረ የማይቻል መሆኑ አውቀን በሽተኞች በጦርነትና በድኽነት የሚሰቃዩትን ስደተኞችን በተለይ ደግሞ ከተለያዩ የአፍሪቃ አገሮችና ከኡጋንዳ ክልል ተሰደው ካምፓላ ለገቡት ወንድሞቻችና እህቶቻችን ቅርብ እንሁን፡ የሁሉም ጩኸት ሰምቶ መልስ መስጠት ለኢየሱስ ቃል ምላሽ መስጠት ይሆናል። የምንሰጠው መልስ እግዚአብሔርን ከማፍቅርና ይኸንን ፍቅር በተግባር ድኾችን የተናቁት ስደተኞችን አለ ምንም የሃይማኖትና የጎሳ ልዩነት በማፍቅር የሚገለጥ ፍቅር ነው፡

ኢየሱስ የሚጠይቀን ፍቅር በግለ ሰቦች መካከል የሚሟጠጥ ሳይሆን ከዚህ በዘለ በማኅበርሰብ ዘንድ የሚኖር ማኅበራዊ ፍቅር ሆኖ በፖለቲካው ዓለም የሁሉም የጋራ ጥቅም በመሻት ተግባር ጭምር የሚገለጥ ፍቅር ነው። ስለዚህ ይኽ ዝክረ 50ኛው ዓመት የርእሰ ሰበካው ቅዋሜ በዓል በኡጋንዳ ካቶሊካዊው እምነት በፍቅር ላይ ጸንቶ በዚህ ክርስቶሳዊ ጥሪ እራሱን አድሶ በአንዲስ መንፈስ ክርስትናን በቃል እና በሕይወት እንዲያበስር ክርስቲያናዊ ጥሪ የሚታደስበት ወቅት ነው። ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ቤተ ክርስቲያን በአፍሪቃ የተሰየመው የቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሓዋርያዊ ምዕዳን ከዛም የአፍሪቃ መሓላ የተሰየመው የቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሓዋርያዊ ምዕዳን ጠቅሰው፥ በሁሉም ሥፍራ ወንጌል በሰዎች ውስጥ በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ እንዲሰርጽ ለማድረግ ተጠርተናል ስለዚህ ወንጌላዊ ቁርጠኝነት ለእስፍሆተ ወንጌል ያለው አስፈላጊነት በቃልና በሕይወት ይተርጎም አድራ በማለት የለገሱት ምዕዳን ማጠቃለላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ አመለከቱ።

31/10/2017 09:43