Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ ግብረ ሠናይና ትብብር

ብፁዕ ካርዲና ፓሮሊን በኖርቺያ፡ ቅዱስ አባታችን በጉዞአችሁ ትበረቱ ዘንድ ስለ እናንተ ይጸልያሉ

ብፁዕ ካርዲና ፓሮሊን በኖርቺያ፡ ቅዱስ አባታችን በጉዞአችሁ ትበረቱ ዘንድ ስለ እናንተ ይጸልያሉ - ANSA

30/10/2017 16:52

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ በሚያጋጥም ችግር ምክንያት ተዘግቶ ከማንባትና ከመውደቅ ይልቅ መጻኢን በተስፋ በመመልከት በጉዞአችሁ በርትታችሁ ወደ ፊት ትሉ ዘንድ በርቱ ስለ እናንተም ይጸልያሉ። ይኸንን ያሉት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓርሊኒ ኖርቺያ በሚገኘው በቅዱስ  በነዲክቶስ ዘኖርቺያ ባዚሊካ እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 26 ቀን እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ባሉት ቀናት ውስጥ በተፈራረቅ በርእደ መሬት ከተጠቃው በኢጣሊያ ፐሩጃ ክፍለ ሃገር በሚገኘው በኖቺያ ወረዳ ሰለባ ለሆኑት ለዝክረ አንደኛው ዓመ ምክንያት ከቅትር በፊት በኢጣሊያ ሰዓት አቆጣጠር 11 ሰዓት ላይ የክልሉ ምእመናን ያሳተፈ መስዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ባሰሙት ስብከት እንደሆነ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ማርኮ ጉወራ አስታወቁ።

በዚያ ኡምብሪያ ማርከና ላዚዮ አውራጃዎችን በሚያገናኘው ክልል ተከስቶ በነበረው ርእደ መሬት የሞት አደጋ ያጋጣማቸው የተጎዱትን ንብረታቸውንና ቤታቸውም ሁሉ የወደመባቸው ዜጎች በማሰብ ቅዱስ አባታችን፥ በሳቸው አማካኝነት የማበረታቻና በኢየሱስ ክርስቶስ በመታመን በቅድስት ድንግል ማርያም እናታዊ ጥበቃ ጽናት የዳግመ በግንባታውን ሂደት እንዲቀጥሉበት ያስተላለፉ መልእክትና ጸሎት እንዲሁም ቡራኬም ማቅረባቸው ጉወራ አስታወቁ።

በኖርቺያ ተከስቶ በነበረው ርእደ መሬት የተጎዳው በክልሉ የሚገኘው ባዚሊካ የንዝረቱ ኃይለኛነት ማረጋገጫ ቢሆንም የክልሉ ሕዝብ በዳግመ ግንባታው ተጠምዶ እያሳየው ያለው ትጋት በሰው ኃይል ብቻ ሳይሆን በዚያ ሁሉን ቻይ በሆነው ኃይል ተማምኖ ወደ እርሱ እራስን ቀና በማድረግ የሚጸገው መሆኑና የእግዚአብሔር ኃይል የላሸቀውን ዕለታዊ ኑሮና ማኅበራዊና ሰብአዊ ሕይወት ሁሉ የሚቀናው እያንዳንዱ ስለ ሁሉ ሁሉም፡ ሁሉም ስለ እያንዳንዱ በመኖርና እርስ በእርስ በመደጋገፍ በተስፋ ወደ ፊት እንዲባል የሚመራና የሚያበረታታ ሁሉም በዳግም ግንባታው ዓቅሙን ችሎታውን በለጋስነት አዋህዶ እንዲያቀርብ ድጋፍ ነው እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጉወራ አያይዘው፥ የዕለቱ (እ.ኤ.አ. ሰንበት ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም.) ከማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 22 ከቍ.34-40 የተወሰደውን፥

እግዚአብሔር እምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህ በፍጹም አሳብህ ውደድ የሚለው ከሁሉም በላይ የሆነው ቀዳሚው ትእዛዝ ቀጥሎም ይኽ ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር የምንገልጥበት የምንኖርበት ሰውህ ሁሉ እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ

በማለት የሚገልጠውን ትምህርት ላይ ተንተርሰው፡ በመካከላችን እርስ በእርሳችን የምንገላለጠው ፍቅር ለዚያ ለምናመልከው ለምንቀድሰው እግዚአብሔር ያለን ፍቅር መመዘኛ ነው፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ሳናፈቅር ወድማችንን ለማፍቅር የማይቻል መሆኑ ማወቅ ይኖብናል። ይኽ ደግሞ እናንተ በርእደ መሬት ከተጠቃው ክልል የመጣችሁ ወድሞቻችንና እህቶቻችን በቃልና በግብር ስትምሰክሩት አይተናል። ለእኛም አብነት ሆናችኋል እንዳሉ ገልጠዋል።

እግዚአብሔርን ሳናፈቅር ለሌላው ሰው ያለን ፍቅር መረዳቱ ያዳግታል። ያዳግታልም ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን ሳናፈቅር የምናሳየው ፍቅር ፍጹማን ባለ መሆናችን በተለያየ ምክንያት ለፈተና የሚጋለጥ አቀላሉ የሚፈርስ ይሆናል። ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር ከሌላው የሚነጥለን የሚያገለን ከሆነ በትክክል እግዚአብሔርን ማፍቅር ሳይሆን መካድ ነው የሚሆነው፡ ቅዱስ ሐዋርያው ያዕቆብ፥ በምዕ. 2 ከቁ. 14-17 ስለ እምነትና ሥራ ሲናገር፥

ወንድሞቼ ሆይ! ሰው እምነት አለኝ ቢል ነገር ግን እምነቱን በመልካም ሥራ ባይገጥ ምን ይጠቅመዋ? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን? ለምሳሌ የሚለብሱትና የሚጠጡት የሌላቸው ወንድሞችና እኅቶች ቢኖሩ እናንተ ለኑሮአቸው የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሳትሰጡአቸው በሰላም ሂዱ፤ ይሙቃችሁ ጥገቡ ብትሉአቸው ምን ይጠቅማቸዋል? ከመልካም ሥራ የአለየእምነት የሞተ ነው”

የሚለውጥ ጠቅሰው አክለውም ቅዱስ ዮሓውሐንስ አፈወርቅ፥ "የክርስቶስን አካል ለማክበር ትፈልጋላችሁን? አካሉ በሆኑት ዘንድ ላይ ሊፈጸም የሚችለውን ንቀት እርሱም ብድኽነት የሚሰቃዩትን የሚለብሱት በማጣት የሚሰቃዩት እንዳይኖሩ አድርጉ (ድኻን ከድህነቱ በማላቀቅ ዕርቃኑን የሆነው በማልበስ ግለጡት) “ ካሉ በኋላ አክለው፥ ፈሪሳውያን ልባቸው የደነደነባቸው ለምሉእ ፍጻሜ ለሆነው እውነት ገዛ እራሳችውን የቆለፉ ይባስ ብለውም በራሳችው ሕግ ፈጻሚነት በመተማመን እውነት የሆነውን ኢየሱስ ለመፈታተን ባላቸው የሙሴ ሕግ ልሂቅነት ተንተርሰው ትሉቁ ሕግ የትኛው ነው በማለት ይጠይቁታል። አምናለሁኝ የሚለውን እምነቱን በግብረ ምሕረት በመልካም ምግባር በየዋህነት ሌላውን ሰው በማፍቅር በተለይ ደግሞ እጅግ የተናቁትን በማፍቅር እምነቱን ያጽና በማለት ህሊናን በመስታወት ፊት የሚያቆም መልስ ኢየሱስ ይሰጣቸዋል።

በኖርቺያ የተከሰተው አደጋ በዚያኑ ልክ ሳይሆን ከዛም በበለጠ የብዙዎች ድጋፍ ቅርበትና እርዳታን አነቃቅተዋል። እምነትን በተግባር የተመሰከረበት ሁነት ነበር። በተለይ ደግሞ ያንን በርእደ መሬት የተጠቃውን ሕዝብ ከአደጋው ለማትረፍ የተረባረቡት የእሳት አደጋ የመከላከያ ኃይል አባላት በአደጋ ቅወቅት የፈጥኖ ደራሽ ኃይል አባላት ሁሉ በማሰብ ለስፖለቶና ኖርቺያ ሰበካ ክልል በተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ ለተጎዳው ህዝብ የሰጡት መስዋዕትነት የሚጠይቀው አገልግሎት እንዲሁም ከቅዱስ አባታችን ከሁሉም ሰበካዎችና ከቅድስት መንበር የቀረበላቸው ድጋፍ ሁሉ ለእግዚአብሔር ያለህ ፍቅር የሚመሰክር ተግባር ነው እንዳሉ ጉወራ አስታወቁ።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን መስዋዕተ ቅዳሴ ከመጀመራቸው ቀደም በማድረግ የስፖለቶ ኖርቺያ ሰበካ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ኣቡነ ረናቶ ቦካርዶ በቅዱስ አባታችን ስም ለተገኙት ለብፁዕነታቸውን ካርዲናል ፓሮሊን በሰበካቸውና በምእመናኖቻቸው ስም ምስጋናን አቅርበው ቅዱስ አባታችን ያስተላለፉትን መልእክት ማንበባቸውንም ልኡክ ጋዜጠኛ ጉወራ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

30/10/2017 16:52