Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስና የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይፋዊ የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይፋዊ የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ

25/10/2017 14:23

ክርስቲያናዊ ተስፋ፥ 38ኛው ክፍለ ትምህርተ ክርስቶስ፡ መንግሥተ ሰማይ የተስፋችን ግብ ነው

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ክርስቲያናዊ ተስፋ ርእስ ዙሪያ ሁሌ ረቡዕ በተከታታይ የጀመሩትን ይፋዊ የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል፡ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም. 38ኛውን የመጭረሻውን ክፍለ ትምህርቱን፥ ገነት የተስፋችን ግብ ነው በሚል ንእሱ ርእስ ሥር የሚያቀርቡትን ከመለገሳቸው ቀደም በማድረግ በዚህ ከውጭና ከውስጥ በመጡት በብዙ ሺሕ የሚገመቱ ምእመናን ባጥለቀለቀው በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ እየተዘዋወሩ ሰላምታ አቅርበው አስተምህሮው ወደ ሚለግሱበት መንበረ ር.ሊ.ጳጳሳት ደርሰው፥

የተወደዳችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ እንደምን አደራችሁ በማለት ልሙድ ሰላታቸውን ካቀረቡ በኋላ፥ ትምህርተ ክርስቶስ ከመለገሳቸው በፊት የዛሬው ትምህርታቸው መሠረት የሚያደርጉበት ከአዲስ ኪዳን የተወሰደው

ሉቃስ ወንጌል ምዕ. 23፡ 33, 38-43 መሆኑ ሲገለጥ

ቀራንዮ የተባለ ቦታ በደረሱ ጊዜ ሰቀሉት፤ ወንጀለኞቹንም አንዱን በቀኙ ሌላውን በግራው ሰቀሏቸው። […] ከራሱም በላይ (ኢየሱስ) ይህ የአይሁድ ንጉሥ ነው የሚል ጽሑፍ ነበር። ከተሰቀሉት ወንጀለኞችም አንዱ የስድብ ናዳ እያወረደበት፤ አንተ ክርስቶስ አይደለህንም? እስቲ ራስህንም እኛንም አድን ይለው ነበር። ሌላኛው ወንጀለኛ ግን እንዲህ ሲል ገሠጸው፥ ተመሳሳይ ፍርድ እየትቀበልህ ሳለህ፤ ከቶ እግዚአብሔር አትፈራምን? እኛ ላደረግነው ነገር ቅጣት እየትቀበልን ስለ ሆነ፥ ተገቢ ፍርድ ላይ ነን፥ ይህ ሰው ግን አንዳች ክፉ ነገር አላደረገም። ደግሞም ኢየሱስ ሆይ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ አለው። ኢየሱስም፥ እውነተ እልሃለሁ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው።

የሚለው ወንገልዊ ምንባብ ተነቦ እንዳበቃ ቅዱስነታቸው በቀጥታ የተወደዳችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ እንደምን አደራችሁ በማለት ልሙድ ሰላታቸውን ካቀረቡ በኋላ፥

ዛሬ ገነት የተስፋችን ግብ ነው በሚል ንእሱ ርእስ ሥር የሚሰጡት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ያንን ክርስቲያናዊ ተስፋ በሚል ጠቅላይ ርእስ ሥር የጀመሩት አስተምህሮ ማጠቃለያ እንደሚሆን ገልጠው።

ገነት የሚለው ቃል ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሆኖ ከተናገራቸው የመጨረሻ ቃላቶች ውስጥ አንዱ፡ ያንን ለደጉ ፈያታዊ (ክፉ አድራጊ) የተናገረው ነው። ቆም ብለን እናስታውስ። ኢየሱስ በመስቀል ላይ ብቻውን አይደለም። በቀኙና በግራው የተሰቀሉ ሌሎች ሁለት ክፉ-አድራጊያን (በደለኞች) አብረዉት ናቸው። ምናልባት በጎልጎታው በዚያ በተሸለጉት ሦስት መስቀሎች ፊት የሚያልፍ ሰው፥ እንዲህ ባለ መልኩ የተገደሉትን በማየት ፍትሕ ተሰጠ ብሎ እፎይታ የሚሰማው ሊኖር ይችላል።

በኢየሱስ አጠገብ ለተሰጠው ፍርድ የተገባሁኝ ነኝ ብሎ የተቀበለ አንድ በደለኛነቱን የታመነ ሰው አለ። ደጉ ፈያታዊ-ሌባ ያ በዚያ ኢየሱስ በተሰቀበለበት መስቀል በስተ ግራ የነበረውን፥ “እኛ ላደረግነው ነገር ቅጣት የተቀበልን ስን ሆነ ተገቢ ፍርድ ላይ ነን” (ሉቃ. 23,41) ሲል ለዚያ በኢየሱስ ላይ የስድብ ናዳ ያወርድ ለነበረው በኢየሱስ በስተ ግራ ለተሰቀለው ይመልስለታል።

ኢየሱስ በቀራንዮ በዚያ ዕለት አሳዛኝና ቅዱስ ዕለተ ዓርብ ትስብእቱን (ሰው ሆኖ መምጣቱን) እጅግ ወሳኝ የሆነው የመጨርሻውን ሁነቱን አጥብቆ ከእኛ ሐጢአተኞች ጋር በማገናኘት ይኖራል፡ ቅርበቱንና ድጋፉን ይገልጥልናል። በዚህ አኳኃን ኢሳያስ ነብይ በምዕራፍ 53 ቁ. 12 “ … ሕይወቱን አሳልፎ በመስጠቱ ከክፉ አድራጊዎችም ጋር ተቆጠረ” ሉቃስም በምዕራፍ 22 ቁ. 37 “ከዐመጽኞች ጋር ተቆጠረ ተብሎ የተጻፈው በእኔ መፈጸመ አለበት” ሲል ስለ ኢየሱስ እንደተናገረው ይሆናል።

በዚያ በቀራንዮ ኢየሱስ ኃጢአተኛውን የመንግሥተ ሰማይ በሮች ወለል ብሎ እንደሚከፈትለት በእርገኝነት ለዚያ ኃጢአተኛ ነኝ ላለው ደጉ ፈያታዊ (ክፉ አድራጊ) ቃል ሲገባለት፡ ገነት የሚል ቃል መጠቀሙን ወንጌላውያን ለመጀመሪያ ጊዜ ያረጋግጡልናል። ኢየሱስ ይኸንን ቃል ለዚያ በገዛ እጁ መከራ ለደረሰበት ኢየሱስ ሆይ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ (ሉቃ. 23,42) ሲል እውነተኛ ትህትና ይኖር የነበረው ሰው እራሱን ዝቅ በማድረግ ለተማጠነው ደጉ ፈያታዊ ቃል ሲገባለት የተጠቀመበት ቃል ነው። ይኽ በደለኛው ሰው ገዛ እራሱን በደስታ የሚገልጥበት የሰራው መልካም ነገር የሌለው እራሱን ለዚያ አንዳችም ክፉ ነገር አለ ማድረጉ ለታመነበት ኢየሱስ አነሆኝ ሲል ያወክፋል። የዚህ ሰው ትሁታን ቃላቶችና እውነተኛው ትህትና የተሞላው ጸጸቱ አማካኝነት የኢየሱስ ልብ ለመንካት በቅቷል። የኢየሱስ ልብም ይነካል።

ደጉ ፈያታዊ (መላካሙ ክፉ እድራጊው) በእግዚአብሔር ፊት እኛ ያለንበትና የእኛን እውነተኛውን ሁኔታ ይገልጥልናል (እንድናስታውስ ያደርገናል) ልጆቹ መሆናችንን ስለ እኛ እንደሚያስብና እንደሚራራ ያረጋግጥልናል። የእርሱ ፍቅር የምንናፍቅ መሆናችን በምንገልጥበት ወቅት እርሱ ቁጣውን ያርቃል፡ ልቡ ይነካል፡ መራራትን እንጂ ቁጣን የማያውቅ ይሆናል። ይኽ ተመክሮ በበርካታ ማከሚያ ቤቶች ወይንም በወህን ቤቶች ውስጥ ብዙ ጊዜ የሚከሰት ነው። ማንም ሰው፡ ምንም ቢሆን መጥፎ ከፋት የተሞላው ቢመስልም’ኳ ተስፋ የመቆረጥ ሁኔታ ብቻ ቢደቀንበትም’ ለጸጋ የተነፈገ ሊሆን አይችልም፡ ለጸጋ ያልተገባ ብሎ በእንቅጩ መፍረድ አይቻልም። ለእግዚአብሔር ጸጋ የተከለከለ ነው ብሎ መናገር አይቻልም። በእግዚአብሔር ፊት ሁላችን ባዶ እጃችን ነን፡ ልክ እንደዚያ በርቀት ቆሞ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ ማየት እንኳ ያልደፈረው፡ የተገባ አለ መሆኑ ታምኖ ነገር ግን ደረቱን አየደቃ እግዚአብሔር ሆይ እኔን ኀጢአተኛውን ማረኝ ይል እንደነበረው ቀረጥ ሰብሳቢው ሰው (ሉቃ. 18,13 ተመል.) ነው። አንድ ሰው ሕይወቱን መለስ ብሎ በጥልቀት ለመመልከት የመጨረሻው የሕሊና ምርመራ ሲያደርግ፡ አነዚያ ከሳሪያን በመልካም ምግባር እጅግ እንደሚበልጡት ቢገነዘብም’ኳ ተስፋ ሳይቆርጥ ለእግዚአብሔር ምሕረት እራሱን ማወከፍና በዚህ ምሕረት መታመን ይገባዋል። እግዚአብሔር እስከ መጨረሻው ድረስ መመለሳችንን የሚጠባበቅ አባት ነው። ያንን ስላ ተላለፈው ክፋትና ኃጢአት ሁሉ ለመናዘዝ ገና አፉን ከፈት ሲያደርግ በእቅፉ በማኖር አፉን በእቅፉ የሚከድንና ገና ለመናገር ሲጀምር አቅፎ የሚስም አባት ነው (ሉቃ. 15,20 ተመል.)። እግዚአብሔር እንዲህ ነው የሚያፈቅረን።

ምድረ ገነት ወይንም መንግሥተ ሰማይ አፈ ታሪክ ወይንም ልብን የሚያነሆልል ሁለመናን እንደ አስማት እንደሚማርክ መናፈሻ ወይንም የእትክልት ሥፍራ አይደለም። ገነት በእግዚአብሔር እቅፍ ውስጥ መሆን ማለት ነው፡ በእግዚአብሔር መታቀፍ። ስለ እኛ ብሎ በመስቀል ሞታችንን ለሞተው ኢየሱስ ምስጋና ይሁንና በዚያ ማለቂያ በሌለው በእግዚአብሔር ፍቅር መታቀፍ ማለት ነው። ኢየሱስ ባለበት ምህረት እና ደስታ አለ። አለ እርሱ ቍር እና ጭለማም ነው። በሞታችን ሰዓት ክርስቲያን ኢየሱስ ሆይ አስበኝ የሚለው ቃል የሚደግም ነው፡ ምንም’ኳ አንድም አስታዋሽ የሌለን ሆነን ብንገኝም’ኳ ኢየሱስ አጠገባችን ነው፡ በዚያ በሕይወታችን በፈጸምነው ጥቂት መልካም ነገር ምክንያትም ይሁን ወደ እዚያ ተምሳያና ተወዳዳሪ ወደ ሌለው ውብ ወደ ሆነው ሥፍራ ሊወስደን ይፈልጋል። መልካም የሰራነው ጥቂት ቢሆንም’ኳ ባክኖ አይቀርም፡ ያንን ከባርነት ቀንበር መላቀቅ ያለበትን ሕይወታችን ሁሉ እንከን እና ስህተት የተሞላ ቢሆንም ቅሉ ከእኛ ጨርሶ እንዲወገድ ለማድረግም ወደ አብ ቤት ይወስደናል። የህልውናችን ግብ እርሱ ነው፡ ሁሉም እንዲፈጸም እና ወደ ፍቅር መቀየርን ነው።

ይኸንን ያመንን ከሆን በዚህ እውነት ላይ ብንተማመን ሟቾች መሆናችን የሚያሳድርብን ፍርሃት ጨርሶ ይወገዳል። ፍርሃት በእኛ ላይ ምንም ኃይል አይኖረውም። ከዚህ ዓለም የምንለይበት ቀንና ሰዓት በተስፋ መመልከት እንጀምራል። ኢየሱስን ያወቀና ከኢየሱስ ጋር የተገናኘ አይፋራም። ልክ እንደ አረጋዊ ስምዖን ክዚያ መላ ሕይወትን ኢየሱስን በመጠባበቅ የኖረ በመጨረሻ ከክርስቶስ ጋር በመገናኘት የተባረከው፥ “ጌታ ሆይ፤ ቃል በገባኸው መሰረት አሁን ባሪያህን በሰላም አሰናብተው፤ አይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን፤ ማዳንህን አይተዋልና።። … ።” (ሉቃ. 15,29-30) ሲል በቀጥታ ይኸንን ተመክሮ በመኖር የተናገረው ቃል የክርስትናው ተስፋችን ግብ ነው።

በመጨረሻም ምንም ተጨማሪ ነገር አያስፈልገንም፡ ደንገዝጋዛ ማየት በእኛ ውስጥ አይኖርም በከንቱ ማንባት ሁሉ ቀርቷል። ምክንያቱም ሁሉም ተፈጽሟልና። ትንቢትም እወቀትም ሁሉ አብቅቶለታል። ፍቅር ከቶ አይወድቅም ነገር ግን ትንቢት ቢሆን ይሻራል። ልሳንም ቢሆን ይቀራል እወቅትም ቢሆን ይሻራል (1ቆሮ. 13,8 ተመል)፡ ፍቅር ከቶ አይወድቅም በማለት የለገስት የዕለተ ረቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አጠናቀው ደግመው በማኅበር ሰብ ደረጃ ለታቀፉት ከተለያዩ ክውጭና ከውስጥ ከሚገኙት ቁምስናዎች ለተወጣቱ ማሕበረ ምእመናን ሰላምታን እቅርበው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ሁሉንም ወደ መጡበት ማሰናበታቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ። 

25/10/2017 14:23