Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስና የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የዕለተ ረቡዕ ይፋዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የዕለተ ረቡዕ ይፋዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ

19/10/2017 09:25

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ክርስቲያናዊ ተስፋ ርእስ ዙሪያ የጀመሩትን ይፋዊ የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል፡ በዚህ ከውጭና ከውስጥ የመጡት በብዙ ሺሕ የሚገመቱ ምእመናን በተገኙበት በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም. በጌታ ስም የሚሞቱት በሚል ንእሱ ርእስ ሥር ከመጀመራቸው በፊት በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ለተሰበሰቡት ምእመን እየተዘዋወሩ ሰላምታ አቅርበው አስተምህሮው ወደ ሚለግሱበት መንበረ ር.ሊ.ጳጳሳት ደርሰው፥

የተወደዳችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ እንደምን አደራችሁ በማለት ልሙድ ሰላታቸውን ካቀረቡ በኋላ፥

በዛሬው የትምህርተ ክርስቶስ ትምህርታችን ክርስቲያናዊ ተስፋ ከዚያ የዘመናችን ሥልጣኔ ሊደባብቀውና ሊሰርዘው ከሚሻው ከሞት እውነታ ጋር ለማነጻጸር እወዳለሁ። እንግዳው ሞት ለእነዚያ ለእኛ ቅርብ ለሆኑትና ወይንም ወደ እኛም ሲመጣ ሳንዘጋጅ ሲደቀንብን በዚህ ምስጢር ዙሪያ በስነ ቃላት ፍንጭ ወይንም አስተዋጽኦ ለመተንተን ተራ ፊደል የሌላቸው ሆነን ሳንዘጋጅ እንቀራለን። ሆኖም እውነታው እንዳለ ነው፡ የመጀመሪያዎቹ ሰብአዊ ሥልጣኔዎች ሁሉ በዚህ ምሥጢራዊ ሁኔታ ውስጥ አልፈዋል። ሰው ከሙታን አምልኮ ጋር አብሮ የተወለድ ነው ለማለትም እንችላለን።

ከእኛ በፊት የነበሩት ሌሎች ሥልጣኔዎች ሞትን ፊት ለፊት ለመመልከት ድፍረት ነበራቸው። አዛውንቱ ለአዲስ ትውልድ ስለዚህ አልቀሬውና የማይታበል ተጨባጭ ክስተት ለአንድ ልዑል ለሆነ ዓላማ ለመኖር ግድ የሚል መሆኑ በሚገልጥ ቃላት ይተርኩታል። ሟችነትህ  በዚህ ዓለም ሕይወትህ ላንድ ትልቅ ዓላማ ታውለው ዘንድ ዓቢይ ምክንያታዊ ግፊት ነው። መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 90፡ 12 “ጥበበኞች ለመሆን እንድንችል፡ ዕድሜአችን ምን ያህል አጭር እንደሆነ አስተምረን” በማለት ያንን በውስጣችን ያለውን የፍጹም ኃያልነት ቅዥት ይገስጻል። ባዶ ወይንም ኢምንት ነን የሚልም በመዝሙረ ዳዊት ምዕ, 88 እና ምዕ.48 ዘንድ ተጽፎ እናገኛለን። ቀናቶቻችን መቶ ዓመታትም ይድረስ በፊታችን በፍጥነት የሚያልፍ ነው። አላፊ ነው። በመጨረሻም ሁሉ አንደ እስትንፋስ በኖ የሚሄድ መሆኑ ይሰማናል።

ስለዚህ ይኽ ተጨባጭ እውነት የሆነው እርሱም ሞት ሕይወታችንን እርቃኑን ያስቀረዋል። ያንን ትዕቢታችንን ቁጣችንን ጥላቻ ሁሉ ከንቱ መሆኑ ያስገነዝበናል። በብቃት አለ ማፍቀራችንን ማፍቅር በሕይወታች ያለው ጥልቅ ሥፍራ ዘንግተን ይኸንን እግጅ አስፈላጊ የሆነውን ነገር አለ መሻት የኖሩ በመሆናችን ቅር እንድንሰኝ ያደርገናል። ምን እንደዘራን ግልጥ አድርጎ ያሳየናል።

ኢየሱስ የሞትን ምሥጢር ግልጥ አድርጎ አብራርቶልናል። በዕለታዊ የኑሮው ሂደት አማካኝነት አንድ ውዳችንን ሲለየን ሃዘን እንዲሰማን ስልጣን ሰጥቶናል። በወዳጁ አልዓዛር መቃብር ፊት ሆኖ በጥልቀት ተረብሾ አነባ (ዮሐ. 11,35) በዚህ ኢየሱስ ባሳየው ጠባይ ምንኛ ለእኛ ቅርብና ወንድማችን እንደሆነም ይሰማናል።

ስለዚህ ኢየሱስ ወደ ሕይወት ምንጭ ወደ ሆነው አብ ይጸልያል፤ አልዓዛርንም ከመቃብር እንዲወጣ ያዛል። እንዳዘዘውም ሆነ። ክርስቲያናዊ ተስፋ ከዚህ ኢየሱስ በሰው ሞት ፊት ካሳየው ጠባይ ኃይል ያገኛል። ፍጥረት ሞትን በውስጥ ህልው ቢሆንበትም ሞት የእግዚአብሔርን የፍቀር እቅድን የሚጎዳ አደናቃፊ በመሆኑን ኢየሱስ ባዳኝነቱ ሊፈውሰው ይፈልጋል።

ወንጌላውያን ሌላ አንድ ልጁ በጣም ስለ ታመመበት አባት ጉዳይ ይተርካሉ። ይኽ አባት ልጁ እንዲድንለትም ኢየሱስን ይማጠናል (ማር. 5,21-24፡ 35-43 ተመል.) አንድ ልጁ የታመመበት አባት ወይንም ልጇ የታመመባታ እናት ከማየት በላይ ልብን በሐዘን የሚነካ ተምሳሌት ሊኖር አይችልም፡ ከዚህ በላይ ልብን የሚነካ ነገር ያለ አይመስለኝም። ኢየሱስ ከዚያ ኢያኢሮስ ከተባለው ልጁ ከታመመበት አባት ጋር ይጓዛል። ሆኖም ግን አንድ ሰው ወደ ኢያኢሮስ ይመጣና ልጅህ ሞታለች እንግዲህ ስለምን መምህሩን ታደክመዋለህ በማለት ያረዳዋል። “እመን ብቻ እንጂ አትፍራ (ማር. 5,36) ሲል ኢየሱስ ልጁ ለሞተችበት አባት በንዴት አንድ ነገር ሊፈጽም ይችላል ብሎ ከወዲሁ ያንን በውስጡ ያለቸው ትንሽ የእምነት ነበልባል እንዳያጠፋ እትፍራ ሲል ያንን የእምነት ትንሿን ነበልባል እንዳትጠፋ ተንከባከባት ይለዋል። የልጅቷ ሬሳ ወደ ተቀመጠበት ቤት ይገባናል ልጅቷን ከሞት ያሥነሳታል ወዲያውኑም ህያው የሆነችውን ልጅ መልሶ ለውዶቿ ያስረክባታል።

ኢየሱስ እንዲህ በማለትም እምነት ላይ እንድናተኩር ያነቃቃናል። ማርታ ወንድሟ አልዓዛር በመሞቱ ምክንያት  ያንን የዓንቀጸ እምነት ብርሃን የሆነውን “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚያምን ቢሞትም እንኳ በሕይወት ይኖራል፤ በሕይወት የሚኖርና በእኔም የሚያምን ሁሉ ከቶ አይሞትም” (ዮሐ. 11,25026) የሚለውን በመቃወም ስታለቅስ ለነበረቸውን ማርታንም በዚያ ክቡር በሆነው እምነት ላይ ታተኵር ዘንድ ይደግፍታል። ያንን የሕይወትና ከውዶቻችን ጋር ያለንን የፍቅር ትስስር ሁሉ የሚበጣጥሰው ሞት በመጣ ጊዜ  ኢየሱስ ለእያንዳንዳችን የሚጠይቀን ስለ ማመናችንን ነው፡ እመን ነው የሚለን። መላ ሕይወታችን በእምነትና በፍርሃት መካከል የተወጠረ ነው፡ “እኔ ሞት ሳይሆን ትንሣኤና ሕይወት ነኝ። በዚህ ታምናለህን? ታምኚያለሽን?

ሁላችን በሞት ምሥጢር ፊት አቅመ ቢሶችና ኢምንት ነን። ይሁን እንጂ በዚህ ሁነት ውስጥ በልባችን ያንን የእምነት ነበልባል አቅበን መኖር መቻል ትልቅ ጸጋ ነው። ኢየሱስ ልክ ከኢያኢሮስ ጋር እንዳደረገውም እጆቻችንን ይዞ “ታሊታ ኵም እንቺ ልጅ ተነሽ!” (ማር. 5,41) አንተ ልጅ ተነስ ይለናል። ለሁላችን ለእያንዳንዳችን የሚለው ነው፡ ተነሽ! ተነስ!

ከሞት ፊት ወይንም በሞት ፊት ተስፋችን እርሱ ነው። ለሚያምን ሁሉ ሙሉ በሙሉ የሚከፈት በር ነው። ለሚጠራጠር ግን ትንሽ የብርሃን ጭላንጭ እንዲታይ የሚያደርግ ስንጣቅ ያለበት ሆኖ ሙሉ በሙሉ የማይዘጋ ነው፡ ይህ ብርሃን የበሩ ሲያደርገን ለሁላችን ጸጋ ይሆንልናል በማለት የለገሱት ይፋዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አጠናቀው ለሁሉም ሰላምታን አቅርበው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው የቅድስት መንበር የዜናና ህትመት ክፍል መግልጫ አስታወቀ።

19/10/2017 09:25