2017-10-14 10:08:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይፍዊ የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ክርስቲያናዊ ተስፋ ርእስ ዙሪያ የጀመሩትን ይፋዊ የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል፡ በዚህ ከውጭና ከውስጥ የመጡት በብዙ ሺሕ የሚገመቱ ምእመናን በተገኙበት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም. ንቁ ጥበቃ በሚል ንእሱ ርእስ ሥር ከመጀመራቸው በፊት በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ለተሰበሰቡት ምእመን እየተዘዋወሩ ሰላምታን አቅርበው አስተምህሮው ወደ ሚለግሱበት መንበረ ር.ሊ.ጳጳሳት ደርሰው፥

የተወደዳችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ እንደምን አደራችሁ በማለት ልሙድ ሰላታቸውን አቅርበው፥

ዛሬ የማቀርበው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በዚያ የተስፋ ልኬት በሆነው የነቃ ጥበቃ ወይንም ነቅቶ መጠበቅ በሚለው ርእስ ላይ ያነጣጠረ ይሆናል። ንቃታዊነት የተሰኘው ሃሳብ የአዲስ ኪዳን ዋነኛ ጉዳዮች ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ነው፤ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ፥ “ባጭር ታጥቃችሁ ሁልጊዜ ለሥራ ተዘጋጁ፡ መብራታችሁ የበራ ይሁን፡ በዚህም አኳኋን ጌታቸው ከሠርግ መመለሱን የሚጠባበቁ አገልጋዮችን ምሰሉ፤ እነርሱ ጌታቸው በድንገት መጥቶ በሩን በሚያንኳኳበት ጊዜ ፈጥነው ለመክፈት ዝግጁዎች ናቸው” (ሉቃ. 12፡ 35-36) ሲል ይናገራቿል። ጊዜው ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ በኋላ ተከትሎ የመጣ በመሆኑም የአለ መረጋጋትና የመጨነቅ መንፈስ የሚፈራረቅበት ሁነት የተገልጠ ጉዳይ ነው፡ ነገር ግን ክርስትያኖች ፈጽመው ተስፋን አይቆርጡም። ክዚያ ጭንቀትና አለ መረጋጋት ከሚታይበት ሁነት ጋር ተመሳስለው አይኖሩም። የተነበበው ወንጌል ባለ ቤቱ ተመልሶ እንስከሚመጣ ድረስ ለመተኛት ፈጽመው እንደማይሄዱ፡ ሁሌ ነቅተው እንደሚጠባበቁ አገልጋዮች መሆን እንደሚያስፈልግ ይመክራል። ይኽ ዓለም ከእኛ የሚጠይቀው ኃላፊነት ነው፡ እኛም በፍቅር ካለ ምንም ማቅማማት ኃላፊነታችንን በተጠያቂነት መንፈስ እንቀበላለን። ኢየሱስ የሚጠይቀን ጉዳይ ቢኖር አንገታችንን ሳናቀረቅር ያንን ከእግዚአብሔር የሚጸገወልንን እያንዳንዱን አዲስ ቀን በአመስጋኝ  በግርሞት መንፈስ እንድንቀበል ታታሪ መሆንን ነው፡፡ እያንዳንዱ ማለዳ ክርስቲያኖች በመልካም ምግባር የሚቀልሙት እንደ ነጭ ሉክ ባዶ ገጽ ነው። በኢየሱስ የተዋጀን ነን። ነገር ግን ይህ አሁን መዳናችን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጌትነቱን በሙላት የሚገለጥበትን፡ “ሁሉ ነገር በክርስቶስ ሥልጣን ሥር ከሆነ በኋላ፥ እግዚአብሔ አብ በሁሉ ላይ ሥልጣን እንዲኖረው፥ ወልድ ራሱ፥ ሁሉን ነገር በሥልጣኑ ሥር በአደረገለት በእግዚአብሔር አብ ሥልጣን ሥር ይሆናል” (1ቆር. 15,28) ይኽም እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉም የሚሆንበት ሰዓት እንጠበበቃለን ማለት ነው። እርግጠኛ የሆነ ምንም ነገር የለም። በክርስትናው እምነት አገላለጥም የቀጠሮ ቀን ነው። ያ ቀን ሲደርስ እኛ ክርስቲያኖች እንደነዚያ ሌሊቱን ሁሉ ሽንጣቸውን ቀጥ አድርገው መብራታቸውን ይዘው ይጠባበቁ እንደነበሩ አገልጋዮች ሆኖ መገኘት እንፈልጋለን። ከሚመጣው ድኅህነት(መዳን) ጋር ለመገናኘት ዝግጅዎች መሆን አለብን።

ክርስትና ትዕግሥት እንጂ መሰላቸትና ድንዛዜ ማለት አይደለም። የመሰላቸት መንፈስ የሚኖርበተ አይደለም። ምንም’ኳ ዕለታዊ ኑሮ ተደጋጋሚነት የሚታይበት የሚያሰልች ቢሆንም’ኳ በዚህ ተደጋጋሚነትና በአንድ ዓይነተኛው ኑሮ የጸጋ ምስጢር ያለበት መሆኑ የተረጋገጠ ነው። አንዳንድ ሰዎች በፍቅር ጸንተው ለመተላለፊያ መስኖውን እንደሚቀድ የጥልቅ ጉድጓድ ምንጭ ውኃ ሆነው ይገኛሉ። ምክንያት የሌለው ክስተት በጭራሽ የለም። ምንም ነገር አይከስምም፥ ክርስቲያን የሚገኝበት በእያንዳንዱ ነጠላ ሁነትለፍቅር የሚለግም ደንዳና በፍቅር የማይድን ሊሆን አይችልም። የማለዳው ሠርቀ ፀሓይን(ምሥራቀ ፀሐይ) የሚፈጥረው የደስታ ስሜት እንዲረሳ የሚያደርግ አንድም ሌሊት አይኖርም። ሌሊቱ በጥልቀት እየጨለመ ሲሄድ የሚቀድ ጎሕ ለመቃረቡ ምልክት ነው፡ የጨለማው እጅግ ድንቅድቅ መሆን ለንጋት ፀሐይ መቃረብ ምልክት ነው፡ ከኢየሱስ ጋር አንድ ሆነን ከቀጠልን ችግርና ስቃይ የሚያስከትለው ብርዳማነት ፈጽሞ ሸባዎች አይደርገንም እናም መላ ዓለም በድፍኑ ቀቢጸ ተስፋነትን መጻኢው ድንቅድቅ ያለ ደማናማ ይሆናል ብሎ ቢሰብክ’ኳ ክርስቲያን ጨለማ ይሆናል ብሎ ዓለም በሚስከው መጻኢ የክርስቶስ መመለስ እንደሚኖርበት ያምናል። ማንም የክርስቶስ መመለስ ቀኑና ሰዓቱን የማወቅ ብቃት የሌለው ቢሆን፡ በታሪካችን ፍጻሜ መሐሪው ኢየሱስ እንደሚኖር በርግጠኛነት እናውቃለን። እምነቱ ብቻ ይኑረን። ሕይወትን አንርገም። ሁሉም ይድናል። እንሰቃያለን ቁጣ ንዴት የሚያስከትልብንም ቢሆንም በሚኖረን ስለ ክርስቶት ጥዑም ኃይለ ዝካሬው ያንን ሁሉ ሕይወትን የሚያጥላላ ትርጉም የለውም የሚለው ፈተና ይገሰጻል።

ኢየሱስን ካወቅን በኋላ በእርግጠኝነት ታሪክን በእማኔና በተስፋ ከመፈተሽ በስተቀረ ሌላ ምንም ማድረግ አንችልም። ኢየሱስ ልክ እንደ አንድ ቤት ነው፥ እኛ በውስጡ እንኖራለን በዚያ በምንኖርበት ኢየሱስ በሆነው ቤት ዘንድ ባሉት መስኮቶች አማካኝነት ዓለምን እንመለከታለን። ስለዚህ በእራሳችን ውስጥ አደራ አንዘጋ። በናፍቆት ያንን ያለፈውን ወርቃማው ጊዜ ማሰቡን ትተን ወደ ፊት እንመልከት። ያ የእኛ ጥበብ ውጤት ወይንም የእጆቻችን ሥራ ውጤት ብቻ ያልሆነው እንዳውም የእግዚአብሔር አሳቢነት ዘወትር በየዋህነት የሚመለከት ነው፡ ያ ዛሬ ድንግዝግዝ የሚመስለው ሁሉ አንድ ቀን ቦግ ብሎ ይበራል።

እግዚአብሔር ገዛ እራሱን እንደማይክድ ስናስብ። ፈጽሞ እንደማያደናግር እናስተውላለን። በእኛ ላይ የእርሱ ፈቃድ ጭጋግ ሳይሆን በደንብ የተረጋገጠ የድሕነት እቅድ ነው፥ “ምክንያቱም የእግዚአብሔር ፈቃድ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን እንዲያውቁ ነው” (1ጢሞ. 2,4)። ስለሆነም ታሪክ ልክ እንደ አንድ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ባቡር ተመስሎ ቢታሰብም’ኳ የሚከሰቱት የሁነቶች ሁሉ በጨለምተኛነት መንፈስ አንመለከትም። ምንም ነገር ማድረግ አልችልም ብሎ እጅን አጣጥፎ መቀመጥ ክርስቲያናዊ መልካም ምግባር አይደለም። በዚያ አይቀሬ ነው ብለን በምናስበው ዕጣ ፈንታ ፊት ወይንም ለማምለጥ የማይቻልበት ፍርድ ነው ብለን በምናስበወ ነገረ ፊት ሁሉ በማን አለብኝነት ደረትን መንፋት ወይንም አንገትን ማቀርቀር ክርስቲያናዊ ተግባር አይደለም።

ወደ ዓለም ተስፋ የሚያደርስ ሰው ፈጽሞ ለገምተና ሰው ሊሆን አይችልም። ኢየሱስ እጆቻችን አቆላልፈን እንድንጠባበቀው አላዘዘንም፥ “እነዚያ ጌታቸው ድንገት በመጣ ጊዜ ነቅተው ሲጠብቁ የሚያገኛቸው አገልጋዮች እንዴት የተመሰገኑ ናቸው በእውነት እላችኋለሁ እርሱ ባጭር ታጥቆ በማእድ ያሰቀምጣቸዋል በማስተናበርም ያገለግላቸዋል” (ሉቃ. 12,37)፡ የሌሎችን ችግር የገዛ እራሱ በማድረግ የገዛ እራሱን ሰላም ለአደጋ ያላጋለጠ ሰላም ገንቢ የሆነ ሰው ሊኖር አይችልም። ችላ ባይ የሰላም ገንቢ ሳይሆን ሰነፍ ሰው ነው። ተደላድሎና ተመቻችቶ መኖር የሚፈልግ ነው። ባንጻሩ ክርስቲያን ግን ሕይወቱን ለአደጋ ሲያጋልጥ ነው የሰላም ገንቢ የሚሆነው። መልካምን ማድረግ ኢየሱስ የሰጠንን መልካም ነገር ሁሉ ለሌሎች ለማካፋል የማይፈራ ቆራጥ ሰው ማለት ነው።

በዕለታዊ ሕይወታችን ያንን ቀደምት የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ይናገሩት በነበረው በአራማይኛ ቋንቋ ይደግሙት የነበረው በመጨረሻው የቅዱስ መጽሓፍ መደምደሚያ ቃል በዮሓንስ ራእይ ምዕ. 22,20 የሚገኘው ማራና ታ “ጌታ ሆይ ና” የሚለው የልመና ጸሎታቸውን እንድገም፡ ይኽ የሁሉም ክርስቲያን የሕይወት አዝማች መሆን አለበት፡ በዚህ ዓለም የክርስቶስ እርግጠኛነት በስተቀረ ሌላ የሚያስፈልገን ምንም ነገር ሊኖር አይችልም። በማንኛው የሕይወት ደረጃ ውስጥ ብንገኝም እርሱ “እነሆ እኔ በቶሎ እመጣለሁ” (ዮሓን ራእይ. 22,7) በሚለው ቃሉ መልስና ዋስትናውን ሰጥቶናል በማለት የለገሱት ይፋዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አጠናቀው እ.ኤ.አ. ጥቅምት 13 ቀን ዓለም አቀፍ የምኅዳር ብከላ ቅነሳ የሚታሰብበት ዕለት መሆኑ በማስታወስ ፍጥረትንና ተፍጥርኖን እንድንንከባከብ ጥሪ አቅርበው ለሁሉም ሰላምታን አቅርበው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው የቅድስት መንበር የዜናና ህትመት ክፍል መግልጫ አስታወቀ። 








All the contents on this site are copyrighted ©.