2017-10-14 10:32:00

ብፁዕ ካርዲናል ሾንቦርን፥ የሚለወጡት እኛ እንጂ ወንጌል አይደለም


የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የእምነት አቃቢ በሚል የሐዋርያዊ ሕግ ውሳኔ ፊርማቸው በማኖር ይፋ ያደረጉበት ዝክረ 25ኛው ዓመት ምክንያት ያንን ለህትመት የበቃው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ለማሰናዳት ተቋቁሞ ለነበረው የብፁዓን ካርዲናላትና ጳጳሳት ድርገት ዋና ጸሓፊ በመሆን ያገለገሉት ለዝክረ 25ኛው ዓመት እ,ኤ.አ. በአገረ ቫቲካን በሲኖዶስ የጉባኤ አዳራሽ በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ በመገኘት ንግግር ያስደመጡት በኦስትሪያ የቪየና ሊቀ ጳጳሳት ብፅዕ ካርዲናል ክሪስቶፍ ሾንበርን ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልስል፡ መለስ ብለው ያንን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ ትምህርተ መዝገብ እንዲያሰናዳ ተቋቁሞ ለነበረው የብፁዓን ካርዲናላትና ጳጳሳት ድርገት ውስጥ ማለትም እ.ኤ.አ. ከ 1987 እስከ 1992 ዓ.ም. የተኖረው ተመክሮ በሕይወታቸው ዓቢይ ሥፍራ ያለው ብቻ ሳይሆን ጸጋም መሆኑ አስታውሰው፡ የእምነት ሱታፌ የተኖረበትና የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት እየቆነጸብክ ከማቅረብ አደጋ ተላቆ በሙላት በጥልቀት የሚያብራራ የሚያስረዳ በአንድ ወጥ ለማቅረብ አቢይ ጥረት የተደረገበት ወቅት እንደነበርም ጠቅሰው፡ በዚህ ድርገትና በወቅቱ የአንቀጸ እምነት ኅይንተ በነበሩት በብፁዕ ካርዲናል ራትዚንገር ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ16ኛ ሊቀ መንበርነት ሥር ታቅፎ ማገልገሉ ትልቅና ጥልቅ የሕይወት ተመክሮ ነው ብለዋል።

በርግጥ ያ እ.ኤ.አ. በ 1992 ዓ.ም. ይፋ ይየሆነው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ቤተ ክርስቲያን የምትራመድ ወደ ፊት የምትሄድ እንጂ የምትለወጥ እንዳልሆነች ይኽም ዘወትር የክርቶስ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን መሆንዋ የሚያረጋግጥ ነው። ወንጌል ሳይሆን እኛ ነን የምንለወጠው። ይኽ የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ 25ኛ ዓመቱ ሲያስቆጥር ከዚህ መዝገብ በፊት የነበረው የትሬንቶ ጉባኤ ውጤት የሆነው የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ 400ኛ ዓመቱን አስቆጥሯል። ይኽ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ወደ ፊት መሄድን ነው የሚያረጋግጠው፡ የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ለክርስቲያናዊ ሕይወት እጅግ አንገብጋቢና አስፈላጊ የእምነት መረጃ ነው። የእምነትን ውህበትንና ውበትን እንድትኖር የሚያግዝ ጸጋ ነው። የቅድስት ሥላሴ፡ የፍጥረትና ተፈጥሮ ባጠቃላይ የድኽነት ወዘተ. ሚሥጢራት ግንዛቤ እንዲኖርህ ይከንን ግንዛቤ በእምነት በግልና በማኅበር እንዲትኖር የሚደግፍ መሣሪያ ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል።      








All the contents on this site are copyrighted ©.