2017-10-14 10:29:00

ቅዱስ አባታችን፥ የቤተ ክርስቲያን ጠመቅ ትምህርት የተባይ ማጥፍያ መድሃኒት በመርጨት ወደ ፊት እንዳይል የሚታጎር አይደለም


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ የእምነት ርስት ከአበው የተቀበልነውን እውነት በማቀብ ወቅታዊ ሁነት የሚያመላክተውን መንገድ ግምት በመስጠት የሐዋርያዊ የግብረ ኖልዎ የአገልግሎት ኃላፊነት በሐሴትና በምሕረት ለህዝበ እግዚአብሔር ጸጋና ተልእኮ መሆኑ ታምኖ የሚከወን የቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት ነው ከሚል ቅድመ ሁኔታ ላይ በመንደርደር እ.ኤ.አ. ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የእምነት አቃቢ ሐዋርያዊ ሕግ ፊርማቸው በማኖር ያንን የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ ሰነድ በሙላት የሚሸኝ ያጸደቁት ሕግ ዝክረ 25ኛው ዓመት ምክንያት በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ ሥልጣናዊ ምዕዳን መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጋብርኤላ ቸራዞ ገለጡ።

ይኽ 25ኛው ዓመት ሕትመቱን እየተዘከረ ያለው ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ያጸደቁት የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ከጥንት ጀምሮ ከሚሰጠው ትምህርተ እምነት ጋር በማቆራኘት እምነትን ለመረዳት የሚደግፍ እንዲሁም ከእምነት የሚመነጨውን የሰው ልጅ የሚያቀርባቸው ጥያቄዎችን መልስ በመስጠት ወቅታዊውን ሰው ወደ እምነት እንዲቀርብ የሚያደርግ መሆን አለበት እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጋብርኤላ ቸራዞ ገለጡ።

ቅዱስነታቸው፥

ያንን ንብሩ ስለ ሆነው እምነት ጉዳይ ለመናገር አዲስ ቋንቋ መፈለጉ ለብቻው በቂ አይሆንም ስለዚህ ለሰው ልጅ የተጋረጠበትን ወቅታዊ ፈተናዎችና የሚጠብቀው ተስፋው አንጻር ቤተ ክርስቲያን በእግዚአብሔር ቃል የሚጠቃለለው የክርስቶስ ወንጌል ቀጣይ ሕዳሴውን ለማቅረብ ያልተቻለ ይመስላል።

ግን መላው የጠመቁ ትምህርትና የተላለፈው ትምህርተ እምነት ቅዉም ነገሩ ይልሉ ቅዱስነታቸው፥ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ዋቢ በማድረግ  በዚያ ማለቂያ በማይኖረው በግብረ ሠናይ ማመስረቅ ነው፡ ሁልጊዜ እና በሁሉም አጽንዖት ሊሰጥበት የሚገባው የጌታችን ፍቅር ነው፡ በእንደዚህ ዓይነቱ እይታ ወይንም አድማስ  በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ውስጥ በቂና ወጥ የሆነ ቦታ ማግኘት ያለበት የሞት ፍርድ የሚለው ጉዳይ ሊስተዋል ይገባዋል።

ከዚህ ችግር አንጻር ባለፉት የመጨረሻ አርእስት ሊቃነ ጳጳሳት የተላለፈው ትምህርትና እንዲሁም ማኅበረ ክርስቲያን ጭምር የሞት ፍርድ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር የሚጻረር መሆኑ የተደረሰው ግንዛቤ የጠመቅ ትምህርት ተራምዶነቱን የሚያመላክት ነው።

         የሞት ፍርድ የሰውን ልጅ ሰብአዊነትን ኢሰብአዊ የሚያደርግ እርምጃ በመሆኑ፡ በጽናት ሊኮነን የሚገባው ፍርድ ነው።

ሕይወት በማንም ሊቀጭ የማይገባው በዚያ የመጨረሻ እውነተኛ ዳኛ በሆነው በእግዚአብሔር ፊት ዘወትር ቅዱስ ነው። ስለዚህ  ገዳይ እንኳ ሳይቀር ማንም ሰው ሰብአዊ ክብሩ በምንም መንገድ ማጣት አይገባውም (ለዓለም አቀፍ የጸረ ሞት ድርገት እ.ኤ.አ. መጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት መልእክት ተመ.) ምክንያቱም እግዚአብሔር ዘወትር ይቅርታን ለመጠየቅ እና አዲስ ሕይወት ለመጀመር በመሻት ወደ አብ የሚለውን የልጁን መመለስን የሚጠብቅ አባት ነው፡ ስለዚህ ማንም ሕይወት ሊነጠቅ ይቅርና ግብረ ገባዊ መሻሻልና ለማኅበረሰቡ የሚበጅ ነው ብሎ እንዲጠፋ መደረግ የለበትም።

ቅዱስነታቸው እንዳመለከቱትም ከዚህ በፊት ያንን የመጨረሻና የከፋው ኢሰብአዊ ድርጊት የሆነውን የሞት ፍርድ አንደ መፍትሔ መጠቀም የተመረጠው በዚያ ማኅበራዊ ብስለት እና በቂ የመከላከያ ስልቶች በሌሉበት ወቅት ፍትሕ  የሚያረጋግጥ የአንድ አመክንዮ ውጤት እንደሆነ ታምኖበት እግብር ላይ የዋለና እንዳውም በታሪክ እንደሚዘከረውም ምሕረት በፍትሕ ላይ ቅዳሚነት ያለው መሆኑ ተዘንግቶም በአገረ ቫቲካን ሳይቀር እንደ መፍትሔ እንደ አንድ የፍትህ ማስፈጸሚያ ውሳኔ ተብሎ ይተገበር ነበር።

ባለፈው ታሪክ ስለ ተፈጸመው ሁሉ ተጠያቂነት እንዳለብን ታምነን የሞት ፍርድ ምርጫ የክርስቲያናዊ አመለካከት ምርጫ ሳይሆን ቅጥ የለሽ የሕግ አጥባቂነት ዝንባሌ ውጤት ነው፡ የዚህ ዓይነቱ ቅጥ የለሽ ይሕግ አጥባቂነት ዝንባሌ ወንጌል በመረዳቱ ሂደት ወደ ጥልቀት እንዲገባ አላገዘም። ዛሬም ቢሆን በሞት ፍርድ ትግበራ ምክንያት የሚፍጸመው ያንን የሰውን ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ጥሰት በመቃወም ለሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ መከበር ነቅቶ ከማንቃት ይልቅ ገለልተኛ ሆነን ብንገኝ የጥፋተኝነት ስሜት ያድርብናል። በተካፋይነትም ያስጠይቀናል።

የሞት ፍርድ መቃወም ከቀድሞው የቤተ ክርስቲያን ጠመቅ ትምህርት ጋር ተቃርኖ የለውም። ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን ዘወትር ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባሕርያዊ ሞት ድረስ ስለ ሰው ልጅ ሕይወት ጥበቃ የቆመች ነች። በህሉም ደረጃ ሕይወት እንዲከበር የሚተላለፈው ጥሪ አዲስ ትምህርት አድርጎ ማሰቡ የቤተ ክርስቲያን ጠመቅ ትምህርት በሙላት ያለ ማወቅ ውጤት ነው፡ የሞት ፍርድ መቃወም የቤተ ክርስቲያን ጠመቅ ትምህርት ጋር የማይጻረር እድገቱን የሚያረጋግጥ ተጨባጭ ሁነት ነው፡ በመሆኑም እውነትን በአዲስ ሓሳብ የሚያቀርብ ነው፡ የሞት ፍርድ ለመከላከል ለሚቃጥው ክርስቲያንም በቂ መልስ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው፥ የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ህያው ተጨባጭ በመሆኑ የቤተ ክርስቲያን እምነት አቃቢነቷን አይለወጤ ነገር አድርጎ ማሰቡ ትውፊቱን በሙላት ያለ መመልከቱ ምርጫ የሚያሳይ ይሆናል። መንፈስ ቅዱስ በቤተ ክርስቲያን በተስፈኛነት እያደገች ትሄድም ዘንድ በቀጣይነት ይናገራል። ስለዚህ ይኸንን በሃይማኖታዊ መንፈስ ማዳመጥ ይበጃል።

የእግዚአብሔር ቃል ልክ እንደ አንድ እሮጌ ብርድ ልብስ በተባዮች እንዳይበጣጠስ የተባይ መድሃኒት ረጭቶ ማስቀመጥ ሳይሆን ተንቀሳቃሽ ዘወትር ህያው የሚያድግና ያንን ሰዎች ሊያቆሙት የማይቻላቸውን ፍጻሜ ዘንድ በመሸኘቱ ሂደት የሚያድግ ነው ይኽ ደግሞ ቅዱስ ቪንቸንዞ ዘ ለሪንስ እንደሚለው፥ እድሜህን ጠብቀህ በእድሜ ማደግ ነው፡ የተገለጸው እውነት በገዛ እራሱና በቤተ ክርስቲያን አማካኝነት ሲተላለፈ የቤተ ክርስቲያን ጠመቁ ትምህርት መቀየር ማለት ሳይሆን የተገለጸው እውነት የመለያ ባህርዩ ነው።

በሚል ሃሳብ ያስደመጡት ሥልጣናዊ ቃል ማጠቃለላቸው ቸራዞ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.