Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ንግግሮች

ቅዱስ አባታችን፥ የመላ ዓለም ሕፃናት ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ

ቅዱስ አባታችን፥ የመላ ዓለም ሕፃናት ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ - ANSA

11/10/2017 09:51

የሕጻናት ዜጎች ሰብአዊ መብትና ክብር በዚህ በሥነ አኃዝ በተራቀቀው ዕደ ጥበባዊ ዓለም La dignità del minore nel mondo digitale በሚል ዋና ርእስ ተመርቶ በጳጳሳዊ ግሬጎሪያና መንበረ ጥበብ፥ የተለያዩ ሃይማኖቶች መሪዎች የፖለቲካ አካላት የሕጻናት ጉዳይ የሚከታተለው የጸጥታ ኃይል ጥበቃ አባላት ምሁራንና ሊቃውንት በጠቅላላ 140 ተጋባእያን ያሳተፈ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ዓለም አቀፋዊ ዓውደ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ተጋባእያኑን በአገረ ቫቲካን ቀለመንጦስ የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው በለገሱት ሥልጣናዊ ምዕዳን መጠናቀቁ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ስኬታማ የሕጻናት ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ ለምንኖርበት ዓለም አስቸኳይና እንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡ ይኽ ደግሞ በዚህ ባለንበት ዓለም በሕፃናት ላይ የሚፈጸመው ጾታዊ ጥቃት ወይንም ዓመጽ ጸረ ሰብአዊና የክፋት ተግባር የሚያሳስበው እውነት ነው፡ የዚህ ዓይነቱ ዘግናኝ የሆነውን የክፋት ተግባር ለማስወገድ የሕጻናት ጉዳይ የሚመለከታቸው አካላት በብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ደረጃ ተደራጅተው መሥራት ይገባቸዋል እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥

የሕፃናት ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ በቆራጥ ውሳኔና በተጋ አገልግሎት፡ እነዚያ በዓለም የሚወለዱት ሕጻናት በየዋህነትና በርህራሄ መንፈስ በመመልከት ስለ እነርሱ በመቆምና በመጣበቅ ያላቸውን አስደናቂ የሆነውን እምቅ ኃይላቸውን ዓቢይ ግምት በሚሰጥ ፍቅርና እንክብቤ ባጣመረ መንፈስ መረጋገጥ ይኖርበታል።

በወንጌል እየሱስ ሕፃናትን በፍቅር አስተንግዶ በእቅፉ በማኖር ይናገራቸውና ይባርካቸውም እንደነበር ተጽፎ እናገኛለን

በመላው ወንጌል ኢየሱስ በኃለኛ ቃል እጅግ የከፋ ኃጢአት ነው ብሎ የገለጠው ክፋት ቢኖር፡ ታናናሾችን የማሰናከል ተግባር ነው፡  ኢየሱስበእኔ ከሚያምኑት ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሰው። ከባድ የወፍጮ ድንጋይ በዐንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር ተጥሎ ቢሰጥም ይሻለዋል (ማቴ. 18,6) በማለት የኃጢኣቱ ክብደትና ፍጻሜውም ምን እንደምሆን በትክክል ገልጦታል፡ ይኽ የኢየሱስ ቃል እጅግ ጠንካራ ቃል ነው፡ ስለዚህ ያንን ሰብአዊ ፍጡርን እንደ ጥራጊ የሚመለከ በተለይ ሕፃናት ገዛ እራሳቸውን የመከላከልም ሆነ የመጠበቅ ብቃትም አቅምም የሌላቸውን የሚያሰቃይ ባህል በቆራጥነት ሕፃናትን በመከባከቡ ጽናት ባለው ተግባር አማካኝነት ልንቃወመው ይገባል። ታናናሾችን በመደል መዘዙ እጅግ መዋጣጫ የሌለው ከባድ ፍርድ መሆኑ ኢየሱስ ገልጦታ።

ይኽ በሥነ አኃዝ በተራቅቀው ዕደ ጥበባዊ ዓለም አግሮሞት ቢሆንም የሚያስፈራም ጭምር ነው፡ ከባለፉት አስር ዓመታት ወዲህ የምንኖርበት አካባባቢ የአኗኗር ስልት እንዲለወጥ ተጽእኖ አድርገዋል። እንደሚነገረም 800 ሚሊዮን ሕፃናት የመረብት - Internet ተጠቃሚ ናቸው፡ በዚህ መረብት ውስጥ ምንድር ነው የሚያገኙት? የሚል ጥያቄ ያነሱት ቅዱስ አባታችን፥

ልናየውና ልሰማይ የማንፈልገው እውነት እንዳናይ ከመሞከር እራሳችንን ከመደበቅ ይልቅ የተከፈቱ ዓይኖች ሊኖረን ይገባል። ያ በሕፃናት ላይ የሚፈጸመው የሚሰቀጥጥ እጅግ ከባድ የሁሉም ክፋቶች ምንጭ የሆነው በሕፃናት ላይ የሚፈጸም ዓመጽ መኖሩ እያወቅን እንዳላወቅን እያየን እንዳላየን ሆነን የምንኖር እንዳንሆን?

         በመረብት እጅግ አደገኛ ክስተቶች በዚያ በጨለማው መንፈስ አማካኝነት ሲስፋፉ ይታያል። እንደ አብነትም ጸያፍ ስእሎች ጸያፍ ጽሑፎች ጸያፍ ፊልሞች ለመጥቀስ ይቻላል። ይክ በመረብት የሚነዛው ጸያፍ ፍኖት በመረብት ተጠቃሚው ላይ የወሲብ ፍላጎቱን ከቁጥትር ውጭ ወደ ሚያደርግ ጠርዝ ሊያደርስ የሚችልና በወጣቶች መካከል ፆታዊ ስሜት ከቁጥጥር ውጭ የሚያደግ ነው፡ ይባስም ይኸንን ዓይነቱ ተግባር የወንጀል ቡድኖች በመጠቀም ለገቢ ምንጭ መጠቀሚያ በማድረግ ብዙ ሕፃናት የሚኙባቸው የኅብረተሰብ አባላት እያጠመዱ ለወሲብ ንግድ ብሎም በማስፈራት ለተለያዩ ክብር ሰራዥ ተግባር ሲዳርጉበት ይታያል።

መረብት ሰብአዊ ፍጡር ለንግድ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ለሚረግጡ ነውረኛ ተግባራት፡ ለውስጥ የሰውነት አካል ንግድ ሕጻናትን ለተለያዩ አደጋዎች የሚያጋልጥ ሆነዋ። በዚህ በሚታየው ጸያፍ ተግባር ፊት ተደናግጠንና ግራ ተጋብተን እንቀራለን። ምክንያቱም በሥነ አኃዝ የተራቀቀው ዕደ ጥበባዊው ዓለም በእድሜ የገፉትን የሚያገል በመሆኑ በወላጆችና በልጆቾ መካከል ግኑኝነትንና ውይይት እንዳይኖር የሚያደርግ አጋጣሚ ስለ ሆነም ነው። ሰብአዊ ግኑኝነት የሚያኮላሽ ሆኖዋል። አንድ አገርና አንድ መንግሥት ይኸንን በሥነ አኃዝ በተራቀቀው ዕደ ጥበብ አማካኝነት የሚከሰተው ሕጸጽ ሁሉ ለብቻው ሊወጣውና መፍትሔ ሊያሰጠው የሚቻለው አይደለም።

በፍርሃት አንገዛ፡ እንዲህ ባለው የክፋት መንፈስ ፊት ምንም ነገር ለማድረግ አንችልም ብለን ኃይሉም የለንም ብለን ዝምንታን መርጠን እጃቻንን አጣጥፈት ዘጭ ብለን አንኑር። ባንጻሩ ተከስቶ ያለውን ሰብአዊ ቀውስ በኅብረት ገጥመን በቁጥጥር ውስጥ ለማስገባት የሚያስችለንን የተገባ ብቃት ያለው መልስ ማቅረብ ይጠበቅብናል።

ቅዱስ አባታችን አያይዘው ይሴባሕ በሚል ርእስ ሥር የደረሱትን ዓዋዲ መልእክት ዋቢ በማድረግ ያለንን ራእይ ማስፋፋት እንደምንችል ታምነን የሰው ልጅ ነጻነት ያንን በሥነ አኃዝ የተራቀቀውን ዕደ ጥበባዊ ዓለም ስርዓት ጠበቅ እንዲሆን ወሰን እንዲኖረውና አስመስርቀን ለመላ ሰው ልጅና ኅብረተሰብ ለተሟላ እድገት አገልግሎት እንዲውል ለማድረግ ብቃቱ እንዳለን ተገንዝበን ስኬታማና ብቃት ያለው ጥረት ማድረግ አለብን። የተሳሳተ ትዕይንት ማረም አስፈላጊ መሆኑ ሲገልጡ እንደ አብነት በሕፃናት ላይ የሚያስከትለውን ዘርፈ ብዙ ችግር አሳንሰን መመልከት እንደማይገባ አብራርተው። መፍትሔው ዕደ ጥበባዊ ብቻ ነው ብለን ዝም አንበል። ለዚህ በሥነ አኃዝ ለተራቀቀው ዕደ ጥበብ ልንሰጥበት የሚገባንን ትኵረት በርዕዮተ ዓለም ሥር ሳንመዝን ሥርዓት እንዲኖረው ማድረግ የእኛ ኃላፊነት ነው፡ ጥንቃቄ ማድረግ የሰው ልጅ ነጻነት መገደብ ማለት አይደለም።

የሕፃናት ሰብአዊ መብትና ክብር ለመንከባከብና ለመጠበቅ በሚደረግ ጥረት በቤተ ክርስቲያን እንደ ተጠበቀው ሳይከናወን መቅረቱ ቤተ ክርስቲያን ተገንዝባዋለች። እንዲህ መሆኑም፥

አቢይት ወንጀሎች መፈጸማቸው ታውቋል። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለተፈጸመው የዚህ ዓይነቱ ከባድ ወንጀል በእግዚአብሔር ፊትና እንዲሁም የዚህ አሰቃቂ ዓመጽ ሰለባ በሆኑት ፊት በተጨማሪም በማኅበራዊ አስተያየት ፊት ተገኝታ መለወጥና መንጻት ያለው አንገብጋቢነት ታምና ለሕፃናት ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ በሚደረገው ጥረት ሁሉ ቀዳሜ በመሆን አቢይ አስተዋጽኦ በመስጠት ላይ ትገኛለች። ከሁሉም በዚያ በሕፃናት ሰብአዊ መብትና ጥበቃ ዘርፍ ከተሰማሩት መንግሥታውያንን መንግሥታውያን ካልሆኑት ማኅበራት ጋር በመተባበር ላይ ትገኛለች።

በሕፃናት ዓይን መታየት የሁላችን ተመክሮ ነው፡ ልብንና ሕሊናን የሚነካ እይታም ነው። ሕፃናትን በፈገግታ እንዲመለከቱን ምን ማድረግ ይጠበቅብናል? እይታቸው ድንጉጥ እንዳይሆን ከምግባረ ብልሽውና ጋር እንዳይገናኝ ስለ እነርሱ ምን እያደርግን እንገኛለን? በርግጥ በዚህ በሥነ አኃዝ በተራቀቀው ዕደ ጥበባዊ ዓለም ውስጥ የተወለዱ ናቸው ይኸንን ባህል እንዴት መግጠምና ሊገናኙት እንደሚገባቸው መደገፉ የሁላችን ኃላፊነት ነው። ለሕፃናት የተገባ ዓለም በማሰናዳቱ ዘርፍ ልንጠመድና ሕፃናት በደስታ የሚመለከቱን አንዲሁ ለንጹሕ እይታቸው የተገባን ሆነን እንገኝም ዘንድ ስለ እነርሱ ክብር ካለ መታከት ልናገለግል ይገባናል።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም ከዚያ ከተካሄደው ዓውደ ጉባኤ የጸደቀው የውሳኔ ሰነድ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የመላ ዓለም ሕፃናት በወከለቸው የ16 ዓመት እድሜ ባላት የአየር ላንድ ተወላጅ ታዳጊ ወጣት መሰጠቱ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ሕፃናት ከዚያ ከተለያየው ዓመጽ ለማላቀቅ ሁሉም እንደየ ኃላፊነቱ በሕፃናት ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ እንዲተጋ አሳስበው የለገሱት ሥልጣናዊ ምዕዳን ማጠቃለላቸው አስታውቋል።

11/10/2017 09:51