Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ንግግሮች

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ እግዚአብሔር ለካህናት ሕንጸት ታጋሽ ጥቢብ ነው

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ እግዚአብሔር ለካህናት ሕንጸት ታጋሽ ጥቢብ ነው

11/10/2017 09:55

የካህናት ጉዳይ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር “Ratio fundamentalis – መሠረታዊ  አመክንዮ በሚል ርእስ ሥር በካህናት ሕንጸት ዙሪያ የሚያትተው ሰነድ ዙሪያ እንዲመክር በጠራው ዓውደ ጥናት ለሚሳተፉት ካህናት ባስተላለፉት መልእክት፥ በሚነዙት አስፈሪ ደወሎች የማይደናገጥ የጋራ ምርጫ በማከናወን ተገቢነት ያለው ብቁ የካህናት ሕንጸት መርሓ ግብር ማነቃቃትና ለካህናት ሕንጸት አገልግሎት ብቃት ያላቸው ሐናጽያን ካህናት ማሰናዳት ወሳኝ መሆኑ አስገንዝበው፡ በካህናት ሕንጸት ዙሪያ ያለው ችግር ለመቅረፍ አንዳንድ ባህላዊ ማሻሻያዎች እንዲሁም አልፎ ኣአልፎ ቀጣይነት የሌለው ባካባቢ በሚገኙት አቢያተ ክርስቲያን አነሳሽነት የሚካሄዱት ማሻሻያዎች በቂ አይደለም። ልክ እንደ አንድ ሸክላ ሠሪ እግዚአብሔርም እንዲሁ የእጁ ሥራ የሆነውን ሸክላ ይንከባከባል፡ ጌታ ተገቢ ቅርጽ እንደሚሰጥ ሁሉ ሕንጸት ይኸንን አብነት የሚከተል መሆን አለበት። ማሰሮው ጥሩ ሆኖ ካልወጣ ለዚያ ተገቢ ቅርጽ ለሚሰጠው መሐሪ ለሆነው እግዚአብሔር ዳግም ማስረከብ ነው የሚበጀው፡ እርሱ ለሁሉም የተገባውን ቅርጽ ይሰጣል፡ በማለት የሚያንጸው እግዚአብሔር መሆኑ በጥልቅ የሚያመለክት ህሳብ ማስተላለፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞናኰ ገለጡ።

            እግዚአብሔር የእኛ የክህነታዊ ሕንጸት ታጋሽ ርህሩህና መሓሪው ጠቢብ ነው

ነገር ግን በጌታ ለመቀረጽና ለመለወጥ ተደጋጋሚና ደርቅ በሆኑት ስልቶች ላይ ተማምኖ የማንጸው እኔ ነኝ በሚል ትዕቢት መመራት አቢይ ጥፋት ነው።

በየቀኑ በጌታ ለመታነጽ ካልፈቀድክ፡ በወንጌል ላይ ምንም ጉጉትና ተካፋይነትም ሳይኖርህ እንዲሁ ለሕዝበ እግዚአብሔር ጭምር ምንም ስሜት ሳይሆርንህ ብርሃኑ የጨለመበት ካህን ሆነህ ትቀራለህ።

በጌታ ህላዌ ፊት እራስክን ማስገኘት ማለት ሊቀረጽ የሚቻል የሸክላ አፈር ሆኖ መገኘትና በትዕግስት የእግዚአብሔርን ቃል መኖር ማለት ነው፡

ካህን ዕለት በዕለት ካለ ማቋረጥ ገዛ እራሱን እንደ የሸክላ አፈር በሸክላው ሠሪ በሆነው የዚያ ወንጌልን በትኩስ ኃይልና በደስታ የሚቀበለውና የሰዎችን ልብ ሊነካ የሚችሉ ቃላት የማቅረብ ብቃት እንዲኖር ለሚያደርገው ለእግዚአብሔር እጅ የሚያስረክብ መሆን አለበት።

እያንዳንዱ ካህን የሸካል አፈር ብቻ ሳይሆን የዚያ የሸክላው ሠሪ ረዳትና የጸጋው ተባባሪም ጭምር ነው፡ በሸክላው ሠሪ ሕንፃ ካህን በቋሚና ቀጣይ ሕንጸት ዙሪያ ለማገልገል በዋነኛነት ተቀዳሚ ኃላፊነት የለው፡ የሚያንጽ ካህንና ብፁዓን ጳጳሳትም ጭምር በሸክላው ሠሪ ሕንጻ ውስጥ መሠረታዊ ኃላፊነት ያላቸው ናቸው። 

ወደ ሕዝበ እግዚአብሔር ስንሄድ እርሱ የሚጠብቀው ሆነን ማለትም የሕዝቡን ቁስል የሚነኩ በሕዝቡ ፊት በመሆን የሚመሩ፡  ገዛ እራሳችንን በእርሱ(በሕዝበ እግዚአብሔር) ለመቀረጽ እንፈቅዳለን። እንዲህ ሆነን ስንገኝ እግዚአብሔር ሕይወታችንን እንደሚለውጥ እንረዳለን። ለእረኛው አንዱን የሕዝብ ክፍል በአደራ የተሰጠ ከሆነ በትክክል ለዚያ የሕዝብ ክፍል ጭምር አንድ ካህን ተሰጥቷል ማለት ነው።

ቅዱስ አባታችን አያይዘው፥ ካህን በኢየሱስና በሕዝቡ መካከል መሆን አለበት፡ በተራራው ላይ ከጌታ ጋር በምድሪቱም ከሕዝቡ ጋር። ስጋትን ጭርሶ መፍራት የሌለበት፡ የሌሎች ፍርድ የማያስፈራው ወይንም ምን ይሉኛል የማይል። ከዚያ አልቦ አካል ከሆነው መንፈሳዊነትና ከዚያ አልቦ እግዚአብሔር ከሆነው ዓለም ገዛ እራሱን የሚያገል መሆን አለበት፡ እያንዳንዱ ካህን ከዚያ መለኮታዊ ሸኽላ ሠሪ ጋር እንዲተባበር የተጠራ ነው፡ በሸክላ ሠሪው ሕንፃ እንዲያገለግል የተጠራ ነው፡ እንዲህ በመሆኑም ገዛ እራሳችንን፥

ምን ዓይነት ካህን መሆን እፈልጋለሁ። የእልፍኝ ካህን፡ ሁሉም ስለ ተመቻቸለት የተረጋጋ ወይንም ልቡ በዚያ ለመምህሩና ለሕዝበ እግዚአብሔር ባለው ፍቅር የሚቃጠል? ችግር የሚርቅ ከሁሉም ወጣ ውረድ የተገለለ ለብ ያለ ሁነት የሚመርጥ ወይንም በህዝብ ልብ ውስጥ በኑባሬ ያለው እግዚአብሔር የመፈለግ ባህርይ የሚያነቃቃ ነቢይ የሆነ ካህን ነው ለመሆን የምፈልገው? 

የሚል ጥያቄ ለሁሉም ለኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ካህናት በእያንዳንዱ የዓውደ ጉባኤ ተሳታፍያን ካህናት እማካኝነት በማቅረብ የለገሱት ሥልጣናዊ ምዕዳን ማጠቃለላቸው የቫቲካንር ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሎሞናኮ ገለጡ። 

11/10/2017 09:55