2017-10-06 09:01:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የድምጸ ርእየት መልእክት፥ በሠራተኞች ላይ የሚፈጸመ የመብት ጥሰት አወገዙ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ዘወትር ካለ ማቋረጥ የሠራተኛው ሰብአዊ መብትና ክብር ማስታወስ የሚል ሃሳብ ያማከለ እ.ኤ.አ. በዚህ በተገባው ጥቅምት ወር መላይቱ ለካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የጸሎት ሃሳብ እንዲሆን መወሰናቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስነታቸው በዚህ ባስተላለፉት የድምጸ እይታ መልእክት አዳዲስ ነገሮች በሚል ርእስ ሥር ር.ሊ.ጳ. ሊዮነ 13ኛ የደረሱት ዓዋዲ መልእክት ዝክረ  90 ዓመት ምክንያ እ.ኤ.አ. በ 1981 ዓ.ም. Laborem Exercens - ሠራተኛው በሚል ርእስ ሥር ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የደረሱት ዓዋዲ መልእክት ዋቢ በማድረግ፡ እውነተኛ የሰብ ልጅና የኅብረተሰብ እድገት እንዲረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የሠራተኛው መብትና ክብር ጥሰት በመቃወምና በማውገዝ ሁሉም በየፊናው የራሱን ሚና ሊጫወት ይገባዋል እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ለሁሉም የሰብአዊ መብትና ክብር አክብሮትና ጥበቃ በማረጋገጥ በሥራ አጥነት ለሚሰቃየው ሁሉ የሥራ እድል ተፈጥርሎለት ሁሉም ለማኅበራዊ ጥቅም መገንባት የራሱን አስተዋጽኦ አበርካች ለማድረግ ስለ የሥራው የሠራተኛው ዓለም እንዲጸለይም ማሳሰባቸውንም ገልጦ፡ ቅዱስ አባታችን እ.ኤ.አ. ጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም. በቦሎኛ ሐውጾተ ኖልዎ በፈጸሙበት ዕለት ሠራተኛውን ክፉኛ እየጎዳ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ ለማሸነፍ የጋራ ውይይትና ሁሉም የኤኮኖሚያዊ ዋስትና እንዲኖረው ያስፈልጋል በማለት ያሰመሩበትን ሃሳብ በማስታወስ ያመልክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.