2017-10-05 09:50:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይፍዊ የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ


ቅዱስ አባታችን እ.ኤ.አ. ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም. ክርስቲያናዊ ተስፋ ርእስ ዙሪያ የጀመሩትን ይፋዊ የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል፡ በዚህ ከውጭና ከውስጥ የጡት በብዙ ሺሕ የሚገመቱ ምእመናን በተገኙበት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተስፋ ልኡካን ዛሬ ንኡስ ርእስ ዙሪያ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምሆርውን ከመጀመራቸው በፊት በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ለተሰበሰቡት ምእመን እየተዘዋወሩ ሰላምታን አቅርበው አስተምህሮው ወደ ሚለግሱበት መንበረ ር.ሊ.ጳጳሳት ደርሰው፥

የተወደዳችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ እንደምን አደራችሁ የሚል ልሙድ ሰላታቸውን አቅርበው፥

በዚህ ዛሬ በማቀርበው የትምህርተ ክርስቶስ አስተህሮ የተስፋ ልኡካን ዛሬ በሚል ርእስ ዙሪያ ላይ ያጠነጠነ ይሆናል። ይኸንን በዚህ ቤተ ክርስቲያን እ.ኤ.አ. ወርሃ ጥቅምት ለየት ባለ መልኩ ለወንጌላዊ ልኡክነትየተወከፈ በመሆኑና እንዲሁም በላቲን ሥርዓት ጥቅምት 4 ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያንን የተስፋ ልኡክ የሆነው ቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘአሲዚ ዓመታዊ በዓል በምትዘክርበት ዕለት የተስፋ ልኡካን ዛሬ በሚል ርእስ ዙሪያ ትምህርተ ክርስቶስ ሳቀርብ ደስታ ይሰማኛል።

በእርግጥ ክርስቲያን የመከራ ነቢይ አይደለም። የተልእኮው ቅዉም ነገሩ ኢየሱስ ስለ ፍቅር ሞተ፡ እግዚአብሔርም በፋሲካ ማለዳ ከሞት አሥነሳው የሚለው እውነታ ነው። ስለዚህ የመከራ ወይንም የስቃይ ነቢይ አይደለም። ይኽ ለክርስትናው እምነት ብሥራትም ማእከል ነው። አራቱ ወንጌላውያን በኢየሱስ መቀበር ዙሪያ የታጠሩ ቢሆኑ ኖሮ የኢየሱስ ታሪክ ልክ ስለ አንድ የከበረ ዓለማ ገዛ እራሳቸውን መስዋዕት እስከ ማድረግ እንደ ታገሉት ሁሉ አንዱ ሆኖ እንዲሁም ወንጌል የሚያንጽ የሚያጽናና ተራ መጽሓፍ እንጂ የተስፋ ብስራት ሳይሆን በቀረ ነበር።

እራቱ ወንጌሎች በአርብ ስቅለት የማይዘጉ ናቸው። ዓርብ ስቅለትን ይሻገራሉ፡ እናም ይኽ ከእርብ ስቅለት ተሻግረው የሚያቀቡት ብስራት ሕይወታችንን የሚለውጥ ሁነት ነው። የኢየሱስ ክርስቶ ደቀ መዛሙር ኢየሱስ ከተሰቀለበት ዕለተ ዓርብ ቀጥሎ ባለው ዕለተ ቅዳሜ ገዛ እራሳቸው ልክ እንደዚያ ትልቁ የኢየሱ መቃብር በር የዘጋው ድንጋይ የእነርሱም ሕይወት በተመሳሳይ መልኩ ተትልቅ ድንጋይ እንደ ተዘጋ አበቃልን ብለው ተስፋቆጠት ፍርሃት ተከናንቦአቸው ኢየሩሳሌምን ለቀው ለመውጣት ፍላጎት እንዲኖራቸውም እድርጓል።

ነገር ግን ኢየሱስ ከሙታን ተነስቷል። ይኽ ያልተጠበቀው ክውንነት የደቀ መዛሙር አእምሮንና ልብን ይቀይራል፡ ይለውጣል። ምክንያቱን ኢየሱስ የሚነሣው ለገዛ እራሱ ሲል ስለ ገዛ እራሱ ብሎ ብቻ ሳይሆን፡ ዕርገቱንም ወደ አባቱ በማረግ ሁሉም የሰው ዘር የትንሣኤው ተካፋይ በማድረጉ ነው። ሁሉም ፍጥረት ወደ ሰማየ ሰማይ ይማርካል። በጴጥተቆስጠ ቀን ደቀ መዛሙርት በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ ይለወጣሉ። ስለዚህ ለሰው ዘር ሁሉ መልካም ብስራት ብቻ ለማቅረብ ሳይሆን ቀድመው ከነበሩበት ሁነት የተለወጡ ዳግም በአዲስ ሕይወት የተወለዱ ሆነው ይገኛሉ። በዚህ አዲስ ሕይወት መልካም ዜናን ያበስራሉ።

በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባርና በተጨባጭ የሕይወት ምስክርነት አማካኝነት የኢየሱን ትንሣሴ ማበሰር መቻል እንዴት ውብ ነው። ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ የተማሩትን ሁሉ ልክ እንደ ቀመር የሸመደዱትን ደግመው የሚያስተጋቡት ሳይሆን እርሱ የሚሻው፡ ተስፋን በደስታ በሚያሳዩት ሌላውን በመቀበል መንፈስ በማፍቀርም እንዲያበስሩ ነው። ከሁሉም በላይ ፍቅር። ምክንያቱ የትንሣሴ ኃይል ክርስቲያኖች የፍቅር አመክንዮው የጠፋባቸው ቢመስሉም እንኳ የማፍቅር ብቃት እንዲኖራቸው ያደርጋል። ክርስትስያን ክርስቲያን የሚያሰኘው ባለው የመንፈስ ጽናትና መልካምን ይሆናል የሚል አወንታዊ እሳቤ ያለው ልክ ከራስ በላይ ገነት ያረፈበትና ሌላው ሊያስተውለው በማይችለው ህላዌ የሚሸን በመሆኑ አይደለም።

ስለዚህ በዚህ ዓለም የክርስቲያኖች ተግባር ወይንም ኃላፊነት ልክ ሌላው አበቃለት ሕይወት ሊዘራ አይችልም ተብሎ ለታሰበው ሕይወት እንዲኖው ለማድረግ እንደሚችለው እንደ ሚራባው ህዋስ ለድኅነት ቦታዎችን ክፍት እንዲሆኑ የሚያደርግ ነው፡ ሰማዩ በደመና የተከበበ ቢመስልም ያንን ደመና ሰንጥቆ ስለ ጸሓይ የሚናገር ቡራኬ ይኖራ። እውነተኛው ክርስቲያን ይህ ነው።  የማያማርር ቁጡ ገንፈልተኛ ያልሆነ በትንሣሴ ኃይል ማቆሚያ የሌለ ምንም ዓይነት ክፋት እንደሌለ። የማይነጋ ሌሊት እንደሌለ ከስሀተት የማይመለስ ሰው እንደሌለ በፍቅር የማይሸነፍ የጥላቻ መንፈስ እንደሌለ የሚያምን ነው።

እርግጥ ነው አንዳንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርት ለዚያ ከኢየሱስ ስለ ተሰጣቸው ተስፋ አቢይ መስዋዕትነት እንዲከፍሉ አድርገዋቸዋል። አነዚያን ስደትና መከራ ሲያጋጥማቸው ሕዝቦቻቸውን ጥለው ያልሸሹት ክርስቲያኖችን እናስብ። በዚያ ነገ በሕይወት መኖር ይቻላል ብሎ ለማመን ያዳግታል የሚል አስተሳሰብ በስፋት ይታይበት በነበረው ክስተት ሳይደናገጡ አብረው ከሕባቸው ጋር የቀሩ። በእግዚአብሔር ላይ ተስፋቸውን በማኖር የታመኑ። የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣሴ የተቀበለ ተስፋ በሚያስቆርጥ ሁነት ውስጥ ተስፋ የሚያደርግ ነው። በሁሉም ጊዚያት የሚኖሩ የደም ሰማዕታት ኢፍትሓዊነት የሕይወት የመደምደሚያ ቃል እንዳልሆነ የሚያምኑ ናቸው። ሕይወት በኢፍትሓዊነት አይደመደምም ብለው በእርግጠኝነት የሚያምኑ ናቸው። ስቃይና መከራ ባለበት ሁሉ ጸንተው ይኖራሉ። ከሌሎች ይልቅ ተፅዕኖ ቢደርስባቸውም ኢየሱስ አብሮአቸው እንዳለ የሚያምኑ ናቸው።  ክርስቶ በውስጡ ያለው ሰው እውነት ነው አይፈራም። ለዚህም ነው ክርስቲያኖች ቀላል ሕይወት ወይንም ልደር ባይነትን የማይለማመዱ።  ደግና የዋህ መሆኑ በእራስ ላይ አለ መተማመን ችላ ባይ መሆን ማለት አይደለም።  ቅዱስ ጳዎሎስ ለጢሞቲዮስ በጻፈውበ ሁለተኛው መልእክቱ ላይ ምክንያቱም እግዚአብሔር የሰጠን የኀይልና የቅር ራስንም የመግዛ መንፈስ እንጂ የርሃት መንፈስ አይደለም” (2ጢሞ. 1, 7) ሲል እንደጻፈው ነው። አዎ ክርስቲያን ይወድቃል ነገር ግን ይነሣል፡ ዘወትር የሚነሣ ነው።

ለዚህ ነው ክርስቲያን የተስፋ ልኡክ ወይንም መልእክተኛ የሚባለው። በብቃቱ ሳይሆን በዚያ እንደ “የስንዴ ቅንጣት በመሬት ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀረለች፡ ከሞተች ግን ብዙ ታፈራለች (ዮሓ. 12,24) ሲል ይኸንን እውነት በሕይውቱ በገለጠልን በኢየሱስ ጸጋ ነው።

በማለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የለገሱትን የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አጠናቀው አስተምህሮውን ለመቀበል ለተገኙትን ሁሉ ደግመው ሰላምታ አቅርበው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ሁሉንም ወደ መጡበት ማሰናበታቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.