Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ቤተ ክርስትያን \ ውይይት

ካርዲናል ፓሮሊን: - የሰሜን ኮሪያን ቀውስ ኅብረ ግብረ መልስ የሚያፈልገው መላ ዓለም የሚመለከት ጥያቄ ነው

ካርዲናል ፓሮሊን: - የሰሜን ኮሪያን ቀውስ ኅብረ ግብረ መልስ የሚያፈልገው መላ ዓለም የሚመለከት ጥያቄ ነው - AFP

26/09/2017 08:56

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ሚና ለይቶ የሚያሳይ “Il Vaticano nella famiglia delle nazioni - ቫቲካን በአህጉራት ቤተሰብ ውስጥ” በሚል ርእስ ሥር በብፁ አቡነ ቶማዚ የተደረሰው በካብሪድጅ መንበረ ጥበብ ማተሚያ ቤት ታትሞ በተባበሩት መንግሥታ ድርጅት የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ሕንፃ እ.ኤ.አ. መስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም. በይፋ ለንባብ ለማብቃት በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ የድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲና ፒየትሮ ፓሮሊን፥ የቅድስት መንበር የሐዋርያዊ ልኡክነት መለያ ለሰላምና ለሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ ለህዝቦች እድገት አገልግሎት የሚል የሚል ሃሳብ ያማከለ ንግግር ማስደመጣቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገለጡ።

ብፁዕ ካርዲና ፓሮሊን  ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በስልክ ባካሄዱት ቃለ ምጠይቅም፥ ብፁዕ አቡነ ቶማዚ ለረዥም ዓመታት በተባበሩት መንሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ሓዋርያዊ ልኡክ በመሆን ያገለገሉ። በዚህ ተልእኮ ማለትም በሐዋርያዊ ልኡክነት ቅድስት መንበርን በተለያዩ አገሮች ያገለሉም ናቸው፡ ስለዚህ ከዚህ ካላቸው ተመኩሮ በመንደርደር በደረሱት መጽሓፍ የቅድስት መንበር ሓዋርያዊ ልኡክነት ሚና ግልጥ አድርገው እንዳብራሩና በተለይ ደግሞ በዓለማችን ክልሎች ለተቀሰቀሱት ግጭቶችም ሆነ መሳይ ቀውሶች እያንዳዱ አገር በተናጥል ብቃቱን ኃሉም አለኝ ብሎ ለብቻው መፍትሔ አመጣለሁ ብሎ የሚያደርገው አሃዳዊ ጣልቃ ገብነት ቀውሱን እንደሚያባብሰው ብፁዕ አቡነ ቶማዚ ካላቸው ተክሮ በጥቅል ተትነዉታል። ስለዚህ መፍትሔው  ኅብረ ግብረ መልስ መሆኑ አስረግጠው አብነትም በማስቀመጥ ያብራሩታል። ቅድስት መንበር የምታመላክተው መንገድም እርሱ ነው ብሏል።

ማንኛውም ችግር መፈታት ያለበት በዓለም አቀፍ ደረጃ ነው፡ እርሱም ተገቢ በሆነው መቀመጫው በዚያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መሆን አለበት፡ የቅድስት መንበር አመለካከትም እርሱ ነው፡ ሁሉም ለሰዎች ክብር መከበር ሁሉም የመብቱ ተጠቃሚ እንዲሆን በዓለም ሰላም እንዲረጋገጥ ሰላማዊ የጋራ ኑሮ ባጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን የማኅበራዊ ጠመቅ ትምህርት መሠረት በማረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትንቀሳቀሳለች፡ ይኽንን በሐዋያዊ ልኡካኖችዋ አማካኝነት ታስተጋባለች፡ መጽሓፉም ይኸንን የሚያስገነዝብ ነው ብሏል።

በአሁኑ ሰዓት በዓለማችን የሚከሰቱ ችግሮችም ይሁን የተለያዩ ቀውሶች ባስቸኳይ መፍትሔ እንዳያገኙ ምክንያት ሆኖ ያለው የአህጉራት መድብላዊ አሠራር መቃወስ ነው፡ ለዚህም እንደ አብነት የሰሜን ኮሪያ ወቅታዊው ቀውስ ጠቅሰው ሲያስረዱ፡  የዚህ ቀውስ ተገቢ ምላሽ ለመስጠት የሚደረገው ጥረት መድብላዊ ስልት የሚከተል መሆን አለበት። ለየብቻህ መልስ ለመስጠት መምኮረ ያስከተለው ችግር ምንኛ አስከፊ መሆኑ ታሪካዊ ሐቅ ነው፡ በመካሂድ ያለው በዚህ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተጠራው 72ኛው ዓለም አቀፍ የመሪዎች ጉባኤ መክፈቻ ወቅት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ትዊተር በተሰየመው ማኅበራዊ መረብት ባለው የግል አድራሻቸው አማካኝነት ባስተላለፉ መልእክት፥ ለጉባኤ ቅርብ መሆናቸው በማረጋገጥ የዓለም መሪዎች ስለ ሰላምና እንዲሁም የጦር መሣሪያ ትጥቅ በመፍታቱ ረገድ አጥበቀው እንዲተጉ አሳስቧል፡ የቅድስት መንበር ሓዋርያዊ ልኡክ አማካኝነትም ጎልቶ የተንጸባረቀ ሃሳብ እርሱ ነው። ቅዱስ አባታችን ያስተላለፉት መልእክት መንግሥታት የሕዝቦች ዕጣ ዕድል በተመለከተ ዓቢይ ኃላፊነት ስላለባቸ ከዚህ ኃላፊነት ጋር የሚመጣጠን ተግባር እንዲፈጽሙና ብቃቱም እንዲኖራቸው የሚያሳስብና ሁሉም በጋራ ሰላም ብልጽግና በመሻትና የተናቁት የተረሱት ድኾች ወገኖችን በመደገፍ ጎዳና አብሮ እንዲጓዝ የሚደገፍ ፖለቲካ እንዲከውኑ አደራ የሚልም ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል። 

26/09/2017 08:56